አዲሱ የፖሊስ አባላት ምልመላ አዲስ አበባን በነዋሪዎቿ እጅ ለማስገባት የመጀመሪያው አጋጣሚ ነው...

አዲሱ የፖሊስ አባላት ምልመላ አዲስ አበባን በነዋሪዎቿ እጅ ለማስገባት የመጀመሪያው አጋጣሚ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዲስ አበባ መስተዳደር ፓሊስ ኮሚሽን አዲስ የፓሊስ አባላትን ለመመልመል ማስታወቂያ አስነግሯል። ምዝገባ የሚካሄደው በከተማዋ ሁሉም ወረዳዎች በሚገኙ ፓሊስ ጣቢያዎች ሲሆን፣ ስልጠናውም በአዲስ አበባ ከተማ ይሆናል ተብሏል።

የአዲስ አበባን ተወላጅ አርቆ ራሱን “የአዲስ አበባ ፖሊስ” እያለ የሚጠራው አካል ላይ በተደጋጋሚ የሚቀርቡት ወቀሳዎችን ተከትሎ ፖሊስ ኮሚሽኑ አዲስ ምዝገባ ጀምሯል፡፡

የአዲስ አበባ ወጣት በየወረዳው በመመዝገብ የሥራ እድሉን ከማግኘት ባሻገር፣ የከተማችን ፓሊስ አባላት ነዋሪውን የሚወክሉ፣ የሚያውቁና፣ አደስ አበቤን መረዳት፣ መርዳትና መጠበቅ የሚችሉ እንዲሆኑ የበኩላቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ የሚያስችል ወርቃማ ዕድል መሆኑ ከወዲሁ ተገልጿል::

በተለይም ካለፉት አስራ ሁለት ወራት ወዲህ የአዲስ አበባ ፖሊስን ከበላይ አዛዦች አንስቶ እስከ ተራ ፖሊስ ድረስ በኦሮሚያ ተወላጆች የማጥለቅለቁን ስራ የተያያዙ አካላት ጉዳይ በህብረተሰቡ ዝንድ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ ሰንብቷል::

በአሁኑ ሰአት በስልጣን ላይ የሚገኙ እነኝህ የፖሊስ ባለስልጣናት ማስታወቂያውን ለአዲስ አበባ ወጣት ለይስሙላ በአደባባይ አውጥተው፣ ለቅጥር የሚመጣውን ወጣት በተለያየ ሰበብ በመጣል ሊያርቁት ይችላሉ የሚል ፍራቻን በብዙዎች ዘንድ አሳድሯል፡፡

በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ በትኩረት የሚሰራው የባልደራሱ ባላደራ ምክር ቤት አዲሱን የፖሊስ ቅጥር አስመልክቶ ምንም አይነት መግልጫ ባያወጣም ሂደቱን በጥንቃቄ እየተከታተለ መሆኑን የአዲስ አበባ ዘጋቢያችን ግልጿል::

LEAVE A REPLY