ገንዘቤ ዲባባን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም መድረኮች ደመቁ

ገንዘቤ ዲባባን ጨምሮ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በዓለም መድረኮች ደመቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ትናንት ምሽት በሞሮኮ በተካሄደ የዳይመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ገንዘቤ ዲባባ አሸናፊ ሆናለች። ወጣቷ አትሌት ገንዘቤ በ1 ሺህ 500 ሜትር የአመቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ጭምር ነው አሸናፊ ለመሆን የቻለችው፡፡

ቀድሞ ወደነበራት አስተማማኝ ብቃት የተመለሰቸው ገንዘቤ ዲባባ ርቀቱን 3 ደቂቃ ከ55 ሰከንድ ከ47 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት ነው ያሸነፈችው። ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ደግሞ 3 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ 40 ማይክሮ ሰኮንድ በመግባት 3ኛ በመሆን ውድድሯን አጠናቃለች።

በወንዶች 3 ሺህ ሜትር ደግሞ የዳይመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ጌትነት ዋለ 8 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ ከ01 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሆኗል። እሱን በመከተል አትሌት ጫላ በዮ 8 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ ከ48 ማይክሮ ሰከንድ በመግባት 2ኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።

በሌሎች የተለያዩ የዓለም ክፍሎች በተደረጉ ውድድሮች ኢትዮጵያዊያን በድል ከመንበሽበሻቸው በተጨማሪ አዳዲስ አትሌቶችም ብቅ ማለት ጀምረዋል፡፡

በፈረንሳይ ኖርማንዲ በተካሄደ የማራቶን ውድድር በወንዶች አትሌት የፀዳው በሌ 2 ሰዓት ከ23 ደቂቃ ከ22ሰከንድ በመግባት ሲያሸንፍ፤ በኔዘርላንድስ በተካሄደ ግማሽ ማራቶን ውድድር ደግሞ አትሌት ሄቨን ሃይሉ 1 ሰዓት ከ09 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ በመግባት 2ኛ ሆና በመጨረስ ተስፈኛነቷን አረጋግጣለች፡፡ በተመሳሳይ በፖላንድ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ጌታዬ ገላው 1 ሰዓት ከ04 ደቂቃ ከ38 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸናፊ ሆኗል።

LEAVE A REPLY