በኦሮሚያ ክልል በሩብ አመት ውስጥ 165 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል ማግኘታቸው ተገለጸ

በኦሮሚያ ክልል በሩብ አመት ውስጥ 165 ሺህ ወጣቶች የስራ እድል ማግኘታቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኦሮሚያ ክልል ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በአራተኛው ሩብ አመት ከ165 ሺህ በላይ ለሆኑ ወጣቶች የስራ እድል ፈጥሪያለሁ አለ፡፡

የቢሮው የእቅድ እና በጀት ዳይሬክተር አቶ ስለሺ ፉፋ በበጀት አመቱ መጨረሻ ሩብ አመት፣ ክልሉ ልዩ እቅድ በማውጣት ስራ አጦችን ለመቀነስ በትጋት እንደሰራ፣ በግንባታ፣ ንግድ፣ አገልግሎት፣ ግብርና እና ማምረቻ ዘርፎች 165 ሺህ 173 ስራ አጥ ወጣቶችን ወደ ስራ በማስገባት ውጤታማ ሊሆን እንደቻለ ለፋና ገልጸዋል:: ይህንንም አሃዝ በቀጣይ 80ሺህ ለማድረስ ዕቅድ መያዙን አስረድተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለተመረቁ እና ለሚመረቁ ተማሪዎች ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ሲሆን በቀታይ ዓመት ለ1 ነጥብ 1 ሚሊየን ዜጎች ቋሚ እና ጊዜያዊ ስራ እንዲፈጠርላቸው ክልሉ ይሰራል ተብሏል፡፡

LEAVE A REPLY