ዜና ኢትዮጵያ ነገ || ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ ምክንያት በአንድዓመት 95 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ማጣቷን ጥናቷ ተሰምቷል፡፡ ከዚህ ውስጥ ኢንዱስትሪዎችና የንግድ ኩባንያዎች 17 ነጥብ24 ቢሊዮን ብር አጥተዋል።
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የሃይልመቋረጥ በኢንዱስትሪዎችና የንግድ ኩባንያዎች ላይያስከተለውን ጉዳት አስመልክቶ ያስጠናውን ጥናት አስመልክቶ በአዝማን ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ጥናቱን ያቀረቡት አቶ ፍቅረማሪያም ይፍሩ በ2010 ዓ.ም ብቻ በሀገርአቀፍ ደረጃ 259 ጊዜ ሃይል ሲቆራረጥ፤ ከ212 ሰዓት በላይ የኤሌክትሪክ አገልግሎት እንዳልነበር ገልጸው በዚህም መሰረት የኢንዱስትሪዎችና የንግድ ኩባንያዎች በአንድ ዓመት 95 ነጥብ5 ቢሊዮን ብር በኤሌክትሪክ ሃይል መቋረጥ ምክንያት እንዳጡ አስታውቀዋል፡፡