ዜና ኢትዮጵያ ነገ || ከተመን በላይ በመሸጥ፣ ያለ ንግድ ፍቃድ በመንቀሳቀስ እና በሚበሉ ነገሮች ላይ “ባዕድ” ነገሮችን ሲቀላቅሉ የተገኙ 37 የንግድ ድርጅቶች ሙሉ ለሙሉ ታሽገዋል፡፡
የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ መስተዳድር በስሩ በሚገኙ 316 የንግድ ድርጅቶች ላይ ባደረገው ድንገተኛ ምርመራ 37 ድርጅቶችን ያሸገ ሲሆን፣ ለ101 ድርጅቶች ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ዛሬ ባዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል፡፡
የክፍለከተማው የንግድ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀብተየስ ዲሮ እንዳሉት፤ ከኑሮ ውድነት ጋር በተያያዘ በንግድ ድርጅቶች ላይልዩ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ እየሰራ ሲሆን፣ በዚህ መሰረት ለአምስት ቀናት በተደረገ ድንገተኛ አሰሳ፣ የንግድ ድርጅቶቹ መንግስት ከተመነላቸው ዋጋ በላይ በመሸጥ፣ ያለ ንግድ ፍቃድ በመንቀሳቀስና በሚበሉ ነገሮች ላይ ባዕድ ነገሮችን በመቀላቀላቸው ምክንያት እርምጃ ሊወሰድባቸው ችሏል፡፡
መንግስት በድጎማ የሚያቀርባቸው እቃዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የክትትልስራ እየተሰራ መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊውበዋናነትም በዳቦ ቤት፣ ስጋ ቤት፣አትክልትና ፍራፍሬ ቤቶች ላይጥብቅ ቁጥጥር መደረጉን ገልፀዋል፡፡የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለከተማ ንግድ ፅ/ቤት ከፍተኛ የገቢ ንግድ ቁጥጥር ባለሙያ አቶዳንኤል ስሜ በበኩላቸው፣ በወረዳ አራት፣ ወረዳ ሰባትና ስድስትከሚገኙ አስር ዳቦ ቤቶች ውስጥ ሰባቱ የመጨረሻማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው፣ ሁለት የሞባይል መሸጫሱቆች፣ አንድ ስጋ ቤት እና አንድ ዳቦ ቤት ደግሞ ያለ ንግድ ፍቃድሰባት ወር ሲነግዱ በመቆየታቸው መታሸጋቸውን ተናግረዋል፡፡