ከ29ኙ ተጠርጣሪዎች ውጪ፣ የመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊዎች ተለቀዋል
ማክሰኞ ዕለት የተካሄደውና በውዝግብ የተሞላው የኢትዮጲያ ቡና ጨዋታ፣ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ከተጠናቀቀ በኋላ የተከሰተው የጋለ እሳት እስካሁን ድረስ እንዳልበረደ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ከኳሱ ይልቅ ፖለቲካዊ አጀንዳ የነገሰበት፣ ስታዲየሙ የብሔር ፖለቲከኞችና የዜግነት ፖለቲካ አቀንቃኞች የታደሙበት አዳራሽ የመሰለበት የአዲስ አበባ ስታዲየም አንድም ጎል ባያስተናግድም፣ የከተማዋ አውራ ጎዳናዎች ግን እጅግ አሳዛኝና አሳፋሪ የሆኑ የደጋፊዎችን እንቅስቃሴ አሳይተውናል፡፡
የመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊዎች ከጨዋታው በኋላ ወደ መጡበት ሲመለሱ፣ በተለያየ ግሩፕ በመከፋፈል፣ ከስፖርታዊ ጨዋነት ውጪ በሆነ መልኩ ሌላውን የሕብረተሰብ ክፍል ለግጭት የሚያነሳሳ፣ ፖለቲካዊ አጀንዳ ያለበት ቃላትን ተጠቅመው ከስታዲየም እስከ 22 ማዞሪያ ድረስ ያለውን አካባቢ ሲበጠብጡና ግጭት ለመፍጠር ሲሞክሩ ታይተዋል፡፡
በዚህ መሰረት የመቐለ 70 እንደርታ ደጋፊዎችን ከጅምሩ በመከታተል፣ ሌላው ሕብረተሰብ በስሜታዊነት ወደ ግጭት እንዳይገባ ፖሊስ ብልጠት የተሞላበት ዕርምጃ በመውሰድ 500 የሚሆኑ ደጋፊዎችን በቁጥጥር ስር አድርጓል፡፡ ደጋፊዎቹ በብዛት ምሽት ላይ የተለቀቁ ሲሆን፣ ደጋፊነታቸው የሚያጠራጥርና እንዲቀሰቀስ የተፈለገውን አመጽ ለመቀስቀስ ሆን ብለው ሲሰሩ ነበር ያላቸውን 29 ወጣቶች ግን በቂ ምርመራ እያደረገ ለመልቀቅ ለጊዜው ማቆየቱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡
ለወትሮው ስማቸው በክፉ የሚነሳው የኢትዮጵያ ቡና ደጋፊዎች ከስታዲየም ውጪ የቀረበባቸውን የጸብ ትንኮሳ በትዕግስት በማለፍ የወሰዱት ዕርምጃ ሊደነቅ የሚገባው ተግባር ሲሆን፣ በአንጻሩ 22 ማዞሪያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዱላ የያዙ፣ የመቐለ 70 እንደርታን ማልያ የለበሱ በርካታ ወጣቶች፣ አንድ የቡና ክለብ ማሊያን የለበሰ ወጣትን ወደ መኪና በመወርወር፣ እንዲገጭ ያደረጉበት ሂደት በርካቶችን አሳዝኗል፤አስቆጥቷል፡፡ እነዚህ ወጣቶች በርካታ እግረኛ መንገደኞችን (የዕድሜ ባለጸጋ የሆኑ እናቶችን ጭምር) ሲደበደቡ፣ ሕዝብ ወደለየለት ጸብ እንዲገባ ሲሞክሩ፣ ጎላጎል ህንፃ ፊት ለፊት መኪና ላይ የነበሩ በርካታ የፌደራል እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ጉዳዩን በዝምታ ሲመለከቱ መቆየታቸው አሁንም የጸጥታ ኃይሉ ሙሉ ለሙሉ ያልጸዳ መሆኑን ያመላክታል፡፡
በአዲስ አበባ ከሰኔ30 ጀምሮ ሞተር ሳይክሎች ሊከለከሉ ነው
በአዲስ አበባ ከተማ ከሰኔ 30 ጀምሮ ፍቃድ ካላቸውኤምባሲዎችና ፖስታ ቤቶች ውጭ ምንም አይነት ሞተር በከተማዋ እንዳይንቀሳቀስ መወሰኑን ምክትል ከንቲባ ኢንጅነርታከለ ኡማ ይፋ አድርገዋል፡፡
ምክትል ከንቲባው በዛሬው ዕለት በሰጡት መግለጫ ከፀጥታአካላት ጋር ለአንድ ሳምንት ጥናት መካሄዱን ተከትሎ ውሳኔውሊተላለፍ እንደቻለ አስታውቀዋል፡፡
በከተማዋ በሞተር የሚካሄዱ ዘረፋዎችና አስከፊ ወንጀሎችከጊዜ ወደ ጊዜ አድማሳቸውን እያሰፉ በመምጣታቸው የሚደርሰውን ጥፋት ለማስቀረት ሲባል ከዚህ ውሳኔ ላይ እንደተደረሰ ም/ከንቲባው ገልጸዋል፡፡
በመርሳ 667 ህገወጥ የመትረየስ ጥይት ተያዘ
በሰሜን ወሎ ዞን መርሳ ከተማ በህገ–ወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረ፣ 667 የመትረየስ ጥይት መያዙን የከተማው ፖሊስጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የከተማዋ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ይርጋጌታቸው እንደገለጹት የመትረየስ ጥይቱ የተያዘው ትናንት ምሽት በመርሳ ከተማ ቀበሌ 03 ክልል ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ግብይት ሊፈፀም እንቅስቃሴ እየተደረገ ባለበት ወቅትነው፡፡ ግለሰቡ ህገ ወጥ ጥይቱን ለመሸጥ ሲያስማማ እጅከፍንጅ ሊያዝ የቻለው ከህበረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረትነው ተብሏል ።
የኢትዮጵያ መዳኛ አብሮነት ብቻ ነው ተባለ
የኢትዮጵያ መዳኛ መንገድ የኢትዮጵያውያን የኖረየዴሞክራሲ እሴት እና አብሮነት መሆኑን ፕሮፌሰር ኤፍሬምይስሃቅ ገለፁ፡፡ ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲ ጉዞ በሚል ርእስ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ባለበት ወቅትነው ፕሮፌሰሩ ይሄንን ያሉት፡፡
የሰላም እና ልማት ማእከል የተሰኘ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅትባዘጋጀው መድረክ ምሁራን፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች እናየውጭ ሀገር ተጋባዥ እንግዶች የተሳተፉ ሲሆን፣ በመድረኩ ላይየመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የታሪክ ተመራማሪው ፕሮፌሰርኤፍሬም ይስሃቅ “ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ እሳቤን በማንፀባረቅእና በመተግበር የረዥም የዘመን ታሪክ ባለቤት ሀገር ናት፡፡ የህዝቦቿ የአብሮነት ታሪክም ዘመናትን የተሻገረ ነው፡፡ ኢትዮጵያአሁን ካለችበት ችግር መውጣት የምትችልበት አንዱ መንገድ ኢትዮጵያውያን ይሄን የኖረ የሰላም እና አብሮነት እሴትን መተግበር ሲቻል ነው” ብለዋል።
በህዝቦች ግንኙነት ሁለት አይነት መቀራረብ እንዳለየ ጠቆሙት ፕሮፌሰሩ እነሱም የልብ እና የአእምሮ መሆናቸውን ገልፀዋል።
ለእኛ የሚሆነው መቀራረብ የልብ ነው፤ ይህም መቀራረብ የፍቅር፣ የይቅርታ እና መዋወደድ ነው ሲሉም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ኢትዮጵያዊቷ ፌበን ኤልያስ አሸነፈች
የአፍሪካን ዲጂታል የፈጠራ ሥራዎች ለማረበታታት በተጀመረው የዲጂታል ላብ አፍሪካ ውድድር፤ ኢትዮጵያዊቷ ፌበን ኤልያስ አሸናፊ መሆኗ ተሰምቷል፡፡
ውድድሩ የተካሄደው በአኒሜሽን እና መሰል የዲጂታል ፈጠራሥራዎች ነው። ፌበን “ድንቢጥ” በተሰኘው የአኒሜሽን ሥራዋ እንዳሸነፈች ለቢቢሲ ገልጻለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሮቴስታንት ክርስቲያኖች ጋር ተወያዩ
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ 400 ከሚሆኑየፕሮቴስታንት ክርስቲያኖች ጋር ሐሙስ ሰኔ 13ቀን 2011 ዓ.ም ሰፋ ያለ ውይት አካሂደዋል፡፡ የፕሮቴስታንት ክርስቲያኖቹ ፣በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ካደረጉት ውይይት በተጨማሪ በቤተመንግስቱ የጉብኝት ሥነ ሥርዓትአካሂደዋል።
ቀደም ባሉት ጊዜያት ጠቅላይ ሚንስትሩ ከተለያዩ የህብረተሰብክፍሎችና የዕምነት ተቋማት ጋር ውይይት ማድረጋቸውይታወሳል፡፡ ለሁለት ተከፍሎ ከ25 ዓመት በላይ የቆየውን ሲኖዶስ ወደ አንድነት የሚመጡበትን መንገድ ያመቻቹ ሲሆን፣ የሙስሊም አፈላላጊ ኮሚቴን ከእስልምና ጉዳዮች አመራር ጋር ዕርቅ እንዲፈጠር በማድረግ ታላቅ ስራ መስራታቸው ይታወቃል፡፡
የተመድ ዋና ፀሓፊ በጥላቻ ንግግር ላይ ጦርነት ማወጃቸውን ገለጹ
የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በጥላቻንግግር ላይ ጦርነት አውጀዋል፡፡ ” እርስ በእርስ በመተያየት የተሻለ ማድረግ አለብን፡፡ የጥላቻ ንግግር ስር ሰዶ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን አሁን ትኩረት አግኝቷል” ያሉት የተባበሩት አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጥላቻ ንግግር ላይስትራቴጂ እና እቅድ መንደፉን ገልጸዋል፡፡
“ትግላችንን አናቆምም” ሲሉ የተደመጡት ዋና ጸሐፊ ምንምእንኳን ስትራቴጂው እና የትግበራ ዕቅዱ አዲስ ቢሆንምመድልዎን በማስወገድ የሁሉንም ሰብአዊ መብት ለማክበርመሰረት ያደረገ እንደሆነ አመላክተዋል፡፡
የመንግስታቱ ድርጅት ቻርተር የረቀቀው በአይሁዶች ላይበተነሳ የጥላቻ ንግግር በሆሎኮስት የተደረገውን የዘርጭፍጨፋ ተከትሎ እንደሆነ እየተነገረ ነው፡፡ ይህ ጥ ቃት ከተፈጸመ 75 ዓመታት በኋላ፤ ጉቴሬዝ በኒውዮርክ በሚገኘውየመንግስታቱ ድርጅት ዋና መሥሪያ ቤት ተሰብስበው ለነበሩትልዑካን “ይህን ትምህርት ከረሳን አደጋ ላይ እንወድቃለን” ብለዋል፡፡
የጥላቻ ንግግሮችና አፍራሽ አስተሳሰቦች በዲጂታልቴክኖሎጂ በኩል በስፋት እየተሰራጩ መሆኑን የገለጹት ዋናጸሓፊው ” አክራሪዎች ኦንላይን ተሰባስበው የአዳዲስአክራሪዎች ምልመላን ያደርጋሉ፣ ይህ የጥላቻ ንግግር ደግሞ የሰብአዊ መብት ጥሰት ከመፈጸምም በተጨማሪ የማህበራዊትስስርንና የጋራ እሴቶችን በመሸርሸር ለግጭት ይዳርጋል”ይላሉ፡፡
የጥላቻ ንግግር በሩዋንዳ፣ በቦስኒያ፣ በካምቦዲያ በተፈጸመውየዘር ጭፍጨፋ፣ እንዲሁም በቅርቡ በሲሪላንካ፣ በኒው ዚላንድእና በአሜሪካ በአምልኮ ቦታዎች ላይ የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ መነሻ ምክንያት እንደሆነም ዋና ጸሓፊው አጽንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ የጥላቻ ንግግር አዋጅን ለማጽደቅ የሚያስችል የባለድርሻ አካላት ውይይት ከአንድ ሳምንት በፊት ማካሄዷ ይታወሳል፡፡
በአፍ የሚወሰድ የኮሌራ ወረርሽኝ ክትባት መሰጠት ተጀመረ
አዲስ አበባን ጨምሮ በአራት ክልሎች በአሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኘውን የኮሌራ በሽታ ለመከላከል፣ በአፍ የሚወሰድ የኮሌራ ክትባት መሰጠት ተጀመረ፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን በአፍ የሚወሰደውን የኮሌራ ወረርሽኝ ክትባት መስጠት የተጀመረው በኮሌራ በሽታተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች በሽታው እንዳይስፋፋ ታስቦ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በሀገሪቱ በሚገኙ አራት ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ 614 ሰዎች በኮሌራ መያዛቸውን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ማስታወቁ አይዘነጋም፡፡
የኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ በኦሮሚያ፣በአማራ፣ በትግራይ፣ በሶማሌ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባና በድሬዳዋ ከተማ መከሰቱንተከትሎ
እስካሁን፣ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን አምስት ወረዳዎች፣ እንዲሁም በፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሰንዳፋከተማ በአጠቃላይ 294 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል። በአማራ ክልል በበሽታው ከተያዙት 198 ሰዎች የ14ቱ ህይወት ሲያልፍ፣ በተመሳሳይ በሶማሌ ክልል 33 ሰዎች፣ በትግራይ ክልል 18 ሰዎች፣በአዲስ አበባ በተለያዩ 9 ክፍለ ከተሞች 70 ሰዎች በኮሌራ ወረርሽኝ በሽታ መያዛቸው ተረጋግጧል።
የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ምክር ቤት በመቐለ ከተማመካሄድ ተጀመረ
የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ምክር ቤት የዘጠኝ ወራት እቅድአፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ዛሬ በመቐለ ከተማ ሲካሄድ፣በምክርቤቱ የመክፈቻ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የኢህአዴግናየሕወሓት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳወጣቶች በሚኖራቸው የምክር ቤት ስብሰባ ጊዜ እንደ ሀገርየተጀመሩ መልካም ስራዎችን የማስቀጠል ሙሉ ኃላፊነትእንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡
“ወጣቶች ለኢህአዴግ ብቻ ሳይሆን ለሀገርም ትልቅ አቅምናቸው” ያሉት አቶ ጌታቸው ሰላምን ለማረጋገጥና የህግየበላይነት ለማስጠበቅ የተደራጀ እንቅስቃሴ ማድረግእንደሚጠበቅባቸውና የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ የህዝቡንበተለይም የወጣቱን ሁለንተናዊ ልማት ለማረጋገጥ ትልቅተልዕኮ እንዳለው በመገንዘብ አደረጃጀቱን በየጊዜው እየፈተሸማስተካከል እንደሚኖርበትም አስረድተዋል፡፡
“ ወጣት ሊጉ ከእናት ድርጅቱ ድክመቱን ሳይሆን መልካሙንበመውሰድ፣ የተሻለ ስራ መስራት ይጠበቅበታል” ያሉት አቶ ጌታቸው በመቐለ ተሰብሳቢዎቹ ለሚኖራቸው የአራት ቀናት ቆይታ መልካሙን ሁሉ ተመኝተዋል፡፡