ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በኢሳይያስ አፈወርቂ የሚመራው የኤርትራ መንግስት የተለያዩ ኃይማኖቶችን በሚከተሉ ዜጎቹ ላይ የሚያደርሰው በደልና እስራት መቀጠሉን የተለያዩ የእምነትና የመብት ተሟጋቾች አስታውቀዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በኤርትራ ያለውንና ከዚህ ቀደም የተከናወነውን የሰብዓዊ መብት አያያዝ እያጠኑ ያሉት የተመድ ልዩ ሪፖርተር ወ/ሮ ዳንኤላ ራቪትስ ዓመታዊ ጥናታቸውን ጄኔቫ ለሚገኘው የድርጅቱ የሰብዓዊ ም/ቤት በዝርዝር አሰምተዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ም/ቤት በቅርቡ አባል ለመሆን የቻለችውን ኤርትራ ከኃይማኖት ጋር በተያያዘ እምነቶቹን በሚከተሉ ዜጎቿ ላይ እየፈፀመች ባለችው አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የተነሳ ም/ቤቱ ድርጊቱን ለማስቆም ጠንከር ያለ ዕርምጃ ሊወስድ
ይቻላል ተብሎ ተገምቷል፡፡