የህዳሴው ግድብ 11 ኃይል ማመንጫ ዩኒቶች ግንባታ በመስከረም ይጀመራል

የህዳሴው ግድብ 11 ኃይል ማመንጫ ዩኒቶች ግንባታ በመስከረም ይጀመራል

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የታላቁ ህዳሴ ግድብ አስራ አንድ የኃይል ማመንጫ ዩኒቶች ተከላ በሚቀጥለው መስከረም ወር 2012 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል፡፡

ከአባይ ውሃ የመጀመሪያውን የኤሌትሪክ ኃይል የሚሰጡ ሁለት የቅድመ የኃይል ማመንጫ ተከላ የተጀመረው ከአራት ዓመት በፊት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት የውሃ ማንደርደረያ ወይንም ስፓይራል ገጠማና የብየዳ ስራ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ይህንን ስራ እያካሄደ የሚገኘው ደግሞ የፈረንሳይ ኩባንያ የሆነው አልስቶን ፍራንስ ነው፡፡ ቀደም ሲል የተጀመረው የቅድመ ኃይል ማመንጫ ስራ የተለያዩ ችግሮች የነበሩበት ከመሆኑ አኳያ መቀጠል የሚችሉትን በማስተካከል፣ አዳዲስ መፍትሄዎችንም በመስጠት ግንባታው እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር አብርሃም በላይ ተናግረዋል፡፡
ከዚህ ቀደም በነበሩት ጊዜያት ሲቪል ወርኩ የተወሰነ ስራ ከመስራት ውጪ መሉ በሙሉ ቆሞ ነበር የሚሉት ዶ/ር አብርሃም፣ ሲቪል ወርኩ መፍትሄ አግኝቶ ስራዎችን በተፋጠነ መልኩ እንዲካሄድ እያደረ ይገኛልም ብለዋል፡፡
ከእነዚህ ሁለት የቅድመ ኃይል ማመንጫ ገጠማዎች ውጭ የሌሎቹ እስካሁን ድረስ አልተጀመረም፡፡ በግድቡ የመጀመሪያ ዲዛይን መሰረት 16 የነበረው የኃይል ማመንጫዎች፣ ለመንግስት በቀረበ ጥናት የሚመነጨውን ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል መጠን ሳይቀንስ፤ የማመንጫዎቹን ቁጥር ለማሳነስ፣ ተቀባይነት ካገኘ ደግሞ የማመንጫዎቹን ቁጥር አስራ ሶስት ለማድረስ ታስቧል፡፡ በዚህ መሰረት የአስራ አንዱ ኃይል ማመንጫዎች ተከላ ከዚህ በኋላ የሚሰራ ይሆናል፡፡
ከውሃ ማንደርደሪያ (ስፓይሬል) እስከ ኃይል ማመንጫ ተከላ፣ የብረታ ብረት ገጠማ የሚሰራባቸው የግድቡ ክፍሎች ክፍት ሆነው የሚገጠምባቸውን ብረት እየጠበቁ ይገኛሉ፡፡ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ክፍሌ ሆሮ ከሁለቱ የቅድመ ኃይል ማመንጫ ክፍል ውጭ ያሉት ጣቢያዎች ተከላ ስራውን በወሰደው የውጭ ተቋራጭ አማካይነት በሚቀጥለው ዓመት መስከረም ወር ይጀመራልም ብለዋል፡፡

LEAVE A REPLY