11/11/11 ኢጄቶና መከላከያን በሃዋሳ ሲያጋጭየዋለው የአሳዛኝ ታሪክ ቀጠሮ || ሮቤል ምትኩ

11/11/11 ኢጄቶና መከላከያን በሃዋሳ ሲያጋጭየዋለው የአሳዛኝ ታሪክ ቀጠሮ || ሮቤል ምትኩ

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ከሚለው የጋራ መታወቂያ ይልቅ ራሱን የቻለ የክልልነት መጠሪያ ይኑረን የሚል አቋም በመያዝ  ጥያቄውን ከአንድ ዓመት በይፋ ያቀረቡት የሲዳማ ብሔር ተወላጆች ሲሆኑ፣ በቅርቡ በሐዋሳ ከተማ ባደረጓቸው ተደጋጋሚ ህዝባዊ ሰልፎችየክልል እንሁንጥያቄያቸው በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጠውና ክልል የመሆን መብታቸው እንዲከበር በአደባባይ ጠይቀው ነበር፡፡

   እነሱን ተከትለው ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጉራጌ እና ሌሎች የክልሉ ብሔሮች ዘንድ ተመሣሣይ ፍላጎት መኖሩን የሚያንፀባርቁ አቋሞች በይፋ መታየት ከጀመሩም ሰነባብተዋል ፡፡ የብሔሮቹ የክልልነት ጥያቄ ህገ መንግሥታዊ ድጋፍ ያለው የመብት ጥያቄ ቢሆንም፤ ሀገሪቱ በተለያዩ ችግሮች እንደ ባላ ተወጥራ ባለችበት፣ የለውጥ ብርሃንን ፈንጥቋል የሚባለው የጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግስት በሁለት እግሩ ባልቆመበት ወቅት መስተጋባቱ ብዙኃኑን አሳዝኗል፡፡

 “ክልል ካልሆንንእያሉ አብዝተው ከሚጠይቁት አስራ አንድ የደቡብ ክልል ዞኖች መሀልፊታውራሪሆኖ እንቅስቃሴውን የሚመራውና በሲዳማ ወጣቶች ስብስብ የተዋቀረውኢጄቶየሚባለው ቡድን ከላይ በተጠቀሱት  ሁለንተናዊ ችግሮች የተጠመደውን የፌደራል መንግስት ከማገዝናታገሱየሚለውን ምላሽ  ከመቀበል ይልቅ፤ የሲዳማ ክልል የመሆን መብትን ህዝቡ በራሱ  11/11/11 (ሐምሌ 11 ቀን 2011 .) ጀምሮ የሲዳማ ሕዝብ ሲዳማ ክልልን በራሱ መንገድ እንደሚመሰርት አሳውቆ ነበር፡፡

 ለምለሟና ሰፊዋ ደቡብ ቁጥራቸው 53 የሚደርስ ብሔሮችና ብሔረሰቦች በአንድ ላይ ተሳስበው በጋራ የኖሩባት ክልል ነች፡፡ የደቡባዊቷ ኢትዮጵያ አጠቃላይ የሕዝብ ቁጥር 15 ሚሊዮን በላይ እንደሆነ ይገመታል፡፡  7.6 በላይ የሚሆነው ወንድ፣ 7.4 በላይ የሚገመቱት ደግሞ ሴቶች እንደሆኑም መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከጠቅላላ የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር አንፃር  16 በመቶ አካባቢ የሚሸፍን የህዝብ ቁጥር ያለው ደቡብ ክልል፤ 105.887.18(አንድ መቶ አምስት ሚሊዮን ስምንት መቶ ሰማኒያሰባት ነጥብ አስራ ስምንት) ስኩዌር ኪሎ ሜትር ስፋትንይዟል፡፡ አብላጫውን የህዝብ ቁጥርና የቆዳ ስፋት የሚይዙት ሲዳማ፣ ወላይታ፣ ሀድያ፣ ጉራጌ፣ ጋሞ፣ ከፊቾና ስልጤ እንደሆኑ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ መረጃ በግልጽ ያስቀምጣል፡፡

ከአጠቃላይ የክልሉ ሕዝብ   20% የሚጠጋውን የህዝብ ቁጥር የሚሸፍነው የሲዳማ ልዩ ዞን በብሔሩ ተወላጆች በኩል የክልልእንሁን ጥያቄን ሲያነሳ የቆየው ከብዙ ዓመታት በፊት እንደነበርአይዘነጋም፡፡

 19 70 . የተመሰረተው የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን) ሊቀመንበር  አቶ ዱካሌ ለሚሶ  የሲዳማ ሕዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ  41 ዓመት  እንደሞላውና  በኮለኔልመንግስቱ /ማሪያም የስልጣን ዘመን የሲዳሞ አካባቢ አስተዳደር፣ የጋሞ አስተዳደር፣ ሀይቆች፣ ቡታጅራ፣ የካፋ አካባቢ አስተዳደር ናቸው በሚል  አንድ ላይ እንዲጨፈለቁ የተደረገ መሆኑን በሰሞነኛ መግለጫቸው መናገራቸው ይታወሳል

የሲዳማ ንቅናቄው መሪ የጠቀሷቸው ችግሮችና የመብትጥያቄዎች፣ ዛሬ ላይ የዞኑን የክልልነት ጥያቄ እየመራና አመጹንእያቀጣጠለ ባለው የወጣቶቹ ኤጄቶ በስፋት  ይስተጋባል፡፡

የብሔሩ ተወላጆች የመብት ጥያቄ የሆነው የክልል እንሁን አጀንዳ በተነሳባቸው መድረኮችና አጋጣሚዎች በምክንያትነት የሚቀርቡ መሠረታዊ ነጥቦች የሲአን ሊቀመንበሩ ካነሷቸውጋር ተመሳሳይ ናቸው፡፡ በዞኑ ህዝብ ጥያቄ ‹‹ አጣብቂኝ ውስጥገብተዋል ›› የሚባሉት የደቡብ ክልል አስተዳደርና ማዕከላዊውመንግስትም ለጥያቄው አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ሀገራዊሁኔታዎች ምቹ አለመሆናቸውን በምክንያትነት ቢያነሱምበሲዳማ ተወላጆች የመብት ጥያቄ ተገቢነት ላይ ግን የጋራዕምነት እንዳላቸው እግረ መንገድ ማስታወስም ግድ ይላል፡፡

ኢጀቶ 11/11/11 የሲዳማ ነፃነት ቀን መሆኑንና ህዝቡ በራሱመብቱን የሚያረጋግጥበት ዕለት መሆኑን ይፋ ካደረገ በኋላየክልሉ መንግሥት የሚመራው የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦችዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደህዴን) በጉዳዩ ላይ ለቀናት ውይይትሲያደርግበት ቆይቶ ሐምሌ 8 ቀን 2011 . አመሻሽ ላይ ባወጣው መግለጫ  “ ደኢህዴን የክልል እንሁን ጥያቄዎች ህገመንግሥታዊና የዜጎች መብት መሆኑን ቢያምንም ጥያቄውንበአፋጣኝ ለመመለስ ግን አሁን ያሉ ሀገራዊ ሁኔታዎች ምቹአይደሉምማለቱም ይታወሳል፡፡

 በክልሉ እና በማዕከላዊ መንግሥቱ በኩል የተያዙት አቋሞች፣ለጥያቄዎቹ በጊዜያዊነት የተሰጡ ምላሾች እንዲህ ዓይነትናቅርጽ ቢኖራቸውም፤ ኢጄቶ እና ቀጥራቸው አስር የሚደርሱበሲዳሞ ዞን የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ግንለጥያቄያቸው የመንግሥትን አዎንታዊ ምላሽ ከመጠበቅ ይልቅህዝቡ በራሱ ክልሉን የመመስረት መብቱን እንደሚጠቀምሲቀሰቅሱ ሰንብተዋል፡፡ ይህ ሁኔታ መብቴ ነውበሚለውህዝብናህጋዊውን ሂደት መከተል አለብንበሚለውየመንግሥት አካል መካከል ልዩነቱ እንዲሰፋ አይነተኛ ሚናተጫውቷል፡፡

  ከሐምሌ 8 ቀን አንስቶ በሃዋሳ ከተማ የነበረው ድባብመልካም አልነበረም፡፡ በሁሉም የከተማዋ አቅጣጫ በርካታቁጥር ያላቸው የሲዳማ ተወላጆች በእግር፣ በሞተር ሳይክል፣በባጃጅ እና በልዩ ልዩ ተሸከርካሪዎች (የመንግሥት ታርጋባላቸው መኪኖች ጭምር) ሆነው በአደባባይ ያሰሙት የደስታመግለጫ ሰልፍእንኳን ደስ ያለን ሲዳማ ክልል መሆኑተረጋጠየሚል መንፈስ ያለው ሲሆን ከሰልፉ በኋላ ጦርመሳሪያ የወደሩ የክልሉ ልዩ ሃይል አባላትና አልፎ አልፎ ባለቀይቆቡ የመከላከያ ሀይል በከተማዋ ጎዳናዎች መታየታቸው ሂደቶቹአስፈሪ መልክ እንዲኖራቸው አድርጓል፡፡

ኢጄቶ 11/11/11 የሲዳማ ነፃነት ቀን ብሎ ያወጀውንናመንግሥት ህገወጥ ያለውን እንቅስቃሴ ህዝቡ በራሱ እውንያደርገዋል እያሉ በስፋት እየሰበኩ ያሉ የዞኑ የፖለቲካ ሀይሎችየነገሮችን አቅጣጫ ተገንዝበው ህዝቡን ከማረጋጋትናመንግሥትም ለሀይል ዕርምጃ እንዳይቸኩል ከማሳሰብ ይልቅየእልሁን መንገድ መርጠው መታየታቸው በራሱ ግራ አጋቢ ነበርማለት ይቻላል፡፡ ሕወሓት ሰሞኑን ባወጣው ድርጅታዊ የአቋምመግለጫ የሲዳማን የክልልነት ጥያቄ በአዎንታዊ ጎኑ ጠቅሶመንግሥት በአፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥበት መጠየቁ ደግሞ ከዚህ የእልህና የብጥብጥ ጉዞ ጀርባየሕወሓት እጅሳይኖርበት አይቀር የሚል መላ ምት አሰንዝሯል፡

 በኢጄቶ የሚመራው የሲዳማ ብሔሮች እንቅስቃሴ ግን ለዚህየመንግሥት መግለጫና ማሳሰቢያ ቦታ የሰጠ አይመስልም፡፡እንደውም በተቃራኒው የሐዋሳ ከተማንና የዞኑን አንዳንድከተሞች በፖስተሮችና ነፃነትን በሚያበስሩ ባነሮችማጥለቅለቅን ስራዬ ብለው ተያይዘውታል፡፡ በተለይም ካለፈውረቡዕ አመሻሽ ጀምሮ በሐዋሳና አከባቢዋ የታየው ሲዳማ ክልልመሆኗን በራስ ፈቃድ የማረጋገጥ ማሳያ የሆነው በፖስተር እናባነር የማጥለቅለቅ እንቅስቃሴ በዞኑ በሚኖሩ የሌላ ብሔርተወላጆች ላይ የደህንነት ስጋት እንዲፈጠር አድርጎ አካባቢውንለቀው እንዲወጡ አስገድዷቸዋል፡፡

የአካባቢው ምንጮቻችን እንደገለፁት በክልሉ ርዕሰ ከተማሀዋሳና በአብዛኛው የዞኑ ከተሞች ሲዳማ ክልል መሆኗንየሚያረጋግጡ ፖስተሮች ከመሰቀላቸው ባሻገር ህዝቡምደስታውን በተለያየ መንገድ እየገለፀ ነው፡፡ በሌሎች ብሔሮችተወላጆች ላይ የተፈጠረውን የደህንነት ሥጋት ለማረጋጋትየተወሰደ እርምጃ ባለመኖሩ ግን ብዙ ዜጎች ለከፍተኛ እንግልትተዳርገዋል፡፡ የትራንስፖት ዋጋም ከእጥፍ በላይ መጨመሩተነግሯል፡፡ በዞኑ ከተሞች በተለይም በሐዋሳና አዋሳኝአከባቢዎች ያለው እንቅስቃሴ ማህበራዊ ቀውስን የማስከተልአቅም እንዳለውም አስተያየት እየተሰጠበት ነው፡፡

የሲዳማ ብሔር ዘመን መለወጫ በዓል (ጨምበላላ) በየዓመቱበድምቀት በሚከበርበት ጉዱማሌ በተባለው ቦታ ማክሰኞ ዕለትኢጄቶ እና ደጋፊዎቹ ህዝባዊ ስብሰባ ያካሄዱ ሲሆንበስብሰባው ላይ የሲዳማ ሐርነት ቀን ብለው ያስቀመጡትን11/11/11 መርሃ ግብር እንደሚቀጥሉበትና ከመንግሥትናከክልሉ /ቤት የሚሰጡ መግለጫዎችን እንደማይቀበሉ የጋራአቋም አንፀባርቀዋል፡፡ የዕለቱን ስብሰባ ሲያጠናቅቁም የሲዳማአባቶች ምረቃ እና ቡራኬ እንዲያቀር ተደርጎ ያዘጋጇቸው ሶስትትላልቅ ነፃነትን የሚያውጁ ባነሮች ተመርቀውበተመረጠላቸው እንዲሰቀሉ ወደማድረግ እንቅስቃሴተሻግረው ነበር፡፡ ይሁንና ገና የመጀመሪያውን ባነር በተለምዶጥቁር ውሃ በሚባለው የሐዋሳ ከተማ መግቢያ ድንበር ላይእንደሰቀሉ የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ ፀጥታ ሃይሎችበቦታው ደርሰው ሰልፉን በመበተን ባነሩ ከተሰቀለበትእንዲወርድ አድርገዋል፡፡

ወደ ሲዳማ ክልላዊ መንግስት እንኳን ደህና መጡየሚልፅሁፍ በጉልህ የሚነበብቸው ፖስተሮች እያንዳንዳቸው በግምትእስከ 30 ሜትር ርዝማኔ ያላቸው እንደነበሩ የገለፀው የሐዋሳምንጫችን የተቀሩት ፖስተሮች በሐዋሳ ከተማ ከንቲባ /ቤትእና በሲዳማ ዞን አስተዳደር /ቤት ህንፃዎች ላይ እንዲቀላቀሉዕቅድ ተይዞላቸው እንደነበር አስረድቷል፡፡ ለህትመትእስከገባንበት ሐሙስ (11/11/11) ዕለት ረፋዱ ድረስ ሐዋሳከተማና የተቀሩት የሲዳማ ዞን አካባዎች በክልሉ ልዩ ኃይልበፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሰራዊት የታገዘ ጥብቅ ጥበቃእየተደረገባቸው በመሆኑ የየከተሞቹ የወትሮ እንቅስቃሴተዳክሞና መንገዶችም ከወትሮው በተለየ ጭር ብለውእንደሚታዩ ለማወቅም ችለናል፡፡

ሀሙስ ሐምሌ11/112011 ሃዋሳ ምን ትመስል ነበር?

በዚህ ቀንነጻነታችንን እናውጃለንእያለ ሲፎክር የነበረውኢጄቶ በሃዋሳ ከተማ የሐይቅ ዳር ክፍለ ከተማ ቀበሌ 05 በሚገኘው የስብሰባ ሜዳ በከተማዋ ዙሪያ ያሉ ወጣቶችንማሰባሰብ የጀመረው ገና ከማለዳው ነበር፡፡ እነዚህ ሁሉን ነገርበኃይል ለመፈጸም የሚሯሯጡት ወጣቶች፤ እንቅስቃሴውንለመቆጣጠር ከመጣው የመከላከያ ሰራዊት ጋር ግጭት ውስጥየገቡትና የሠራዊቱ አባላት ላይ ጉዳት ማድረስ የጀመሩትከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ እንደሆነ ምንጮቻችን ይናገራሉ፡፡

በተደራጀ ሁኔታ የመከላከያ ሠራዊት አባላቱ ላይ ጥቃትያደረሱትን የሲዳማ ወጣቶችን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠርናአጸፋዊ ምላሽ ለመስጠት የተገደደው መከላከያ ዕርምጃበመውሰዱ፤ሎቄተብሎ ከሚጠራው ቦታ አንስቶ ግጭቱእስከተፈጠረበትጉዱማሌድረስ ለበርካታ ሰዓታት ያልተቋረጠየተኩስ ድምጽ ሲሰማ ነበር፡፡

በዚህ መልክ የተቀጣጠለው የኢጄቶ አመጽ እኩለ ቀን ላይአድማሱን በማስፋትና ዓላማውን በመቀየር ወደለየለት የዘረፋተግባር መሸጋገሩ እየተሰማ ነው፡፡ ከሲዳማ ተወላጆች ውጪየሆኑ የተለያዩ ሰዎች ንብረትና ቤት የተቃጠለበትም ሁኔታተከስቷል፡፡ አስቀያሚ ድብደባዎችም በኢጄቶ አማካይነትሲካሄድ በየመንደሩ ህግን እንዲያስከብሩ የተመደቡ የከተማዋፖሊሶች በጠቅላላ የሲዳማ ተወላጆች መሆናቸውን ተከትሎአጥፊዎቹን ከመያዝ ይልቅ ከአካባቢው ዞር እንዲሉ ሲመክሩመታየታቸውን ከደረሱን የአይን እማኝ ምስክሮች መረዳትተችሏል፡፡

አሁን ያለው የሃዋሳ እንቅስቃሴና የከተማዋ ፖሊስ እየወሰደያለውን ፍትሃዊ ያልሆነ ዕርምጃ ተከትሎ የከተማዋ ነዋሪዎችትልቅ ስጋት ውስጥ ወድቀዋል፡፡ የፖሊሱን የስራ ድርሻ ፌደራልፖሊስና መከላከያ እንዲይዘው የብዙዎች ምኞት መሆኑንለማወቅ ችለናል፡፡ በክልሉ የአስቸኳይ ጊዜ  አዋጅ ይታወጃልተብሎም ተገምቷል፡፡

ከከሰዓት በኋላ በሲዳማ ዞን ጨኮ፣ወንዶ እና ሌሎችወረዳዎችም ሁከትና ብጥብጡ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡በእነዚህም ቦታዎች በሌሎች ብሔር ተወላጆች ላይየሚደረገው ዝርፊያና ድብደባ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ለማወቅችለናል፡፡ ወደ ሃዋሳ የሚደረግ ማንኛውም ዓይነትየትራንስፖርት አገልግሎት ሙሉ ለሙሉ ተቋርጧል፡፡ ሱቆችናአገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ተዘግተው ውለዋል፡፡          

በአዲሱ ከቀረጥ ነፃ አዋጅ 31 የመንግስት ተቋማት ተቀናሽ ይሆናሉ

  በተሻሻለ መንገድ እየተረቀቀ ባለው አዲስ የቀረጥ ነፃ አዋጅ ፀድቅና ተግባራዊ ሲሆን መንግስት በየዓመቱ ሰጥ ከቆየው የቀረጥ ነፃ ማበረታቻ 20 ቢልዮን ብር ለማዳን ታስቧል፡፡ በረቂቅ አዋጁ መሠረት ለ35 የመንግስት አካላት (ተቋማት) ሲሰጥ የነበረው የቀረጥ ነፃ ማበረታቻ ወደ አራት ዝቅ እንዲል ከማድረግ ባሻገር በግልፅ ሲታዩ የቆዩ ክፍተቶችንም ይሞላል ተብሏል፡፡

  ሰላሳ አንድ የመንግስት ተቋማትን እስከዛሬ ከቆዩበት የቀረጥ ነፃ ማበረታቻ ወጪ የሚያደርገው አዲስ አሰራር ጤናማ የንግድ ዕቅድ ይዘው ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ የውጭ ባለሀብቶች እንዲሁም የአገር ውስጥ አልሚዎች ከቀረጥ ነፃ ማበረታቻዎች ይልቅ የገበያ ፍላጎ እና አቅርቦት ላይ ይበልጥ ትኩረት እንዲያደርጉ ያስገድዳል፡፡ በአዲሱ አዋጅ የቀረጥ ነፃ ተጠቃሚዎችን ከማሻሻል ባሻገር መብቶቹ ከተሰጡ በኋላ በትክክል ለተባላቸው ዓላማ መዋላቸውን ወይም አለመዋላቸውን ለመከታተል የሚያግዝ ስርዓትም ይዘረጋል፡፡

LEAVE A REPLY