የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ሐምሌ 29 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ሐምሌ 29 ቀን 2011 ዓ.ም

ኮማንድ ፖስቱ በመተከልና አዊ ዞኖች ዙሪያ ዕርምጃ መውሰድ ጀመረ

ከወራት በፊት በአማራና በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ መተከልና አዊ ዞን አዋሳኝ አባቢዎች የተከሰተውን የፀጥታ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት፤ ጠንካራ ዕርምጃዎችን መውሰድ ጀምሯል፡፡ ግጭት ቀስቅሰዋል፣ በግጭቱም ተሳታፊ ሆነዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎችን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር ለማዋል እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

በዚህ መልኩ ዕርምጃውን የጀመረው ኮማንድ ፖስቱ፣ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ወንጀሎ የሚጠረጠሩ 145 ግለሰቦችን ይዞ ምርመራ እያካሄደባቸው ይገኛል፡፡

በአማራ ተወላጆች ላይ ዘግናኝ የሆነ በደል የተፈፀመበት የቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አድሊ ሀሰን እና በርካታ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመተከልና የአዊ ዞን ኮማንድ ፖስት የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡ ኮማንድ ፖስቱ በሁለቱም ዞን አካባቢዎች በመዟዟር ነው የህዝብ ውይይት መድረኮችን ያዘጋጀው፡፡

በጠተቀሱት ስፍራዎች ኮማንድ ፖስቱ ተጠርጣሪ ግለሰቦችን በሕግ ጥላ ሥር ከማዋል ባሻገር እስካሁን ድረስ ባደረገው ክትትል 785 ቀስት፣ 4 ክላሽ 9 ሺህ 392 ጥይት እና 10 ሺህ ሀሰተኛ የብር ኖቶችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ተሰምቷል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን በአማራ ክልል አዊ አስተዳደር ዞን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር የሰው ሕይወት መጥፋቱና ከፍተኛ ንብረት መወደሙ የሚዘነጋ አይደለም፡፡

የሶማሌ እና ኦሮሞ ህዝቦች የውይይትመድረክ ጅጅጋ ላይ ተካሄደ

የኦሮሞ እና የሶማሌ ህዝቦችን የሚመለከት የምክክር መድረክ በጅግጅጋ ከተማ ተካሄደ፡፡ በዚህ የምክክር (ውይይት) መድረ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መድን ጨምሮ ከ750 በላይ የሚሆኑ ከሁለቱም ክልሎች  ዞኖች የተውጣጡ ልዑካኖች ተሳትፈዋል፡፡

የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መመድ የኦሮሞና የሶማሌ ህዝቦች በጋራ መስራት ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው አፍሪካ እንደሚተርፍ በመድረኩ ላይ ባሰሙት ንግግር ገልፀዋል፡፡ እነዚህ ለት ህዝቦች በባህል፣ በቋንቋ፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚና ሌሎች አጠቃላይ ማኅበራዊ ህይወታቸው የተሳሰሩ ንደሆኑም አረጋግጠዋል፡፡

ባለፉት አስራ ሁለት ወራት የለቱን ህዝቦች አንድነት ለማጠናከር እና የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ መኖሪያ ቀያቸው ለመመለስ በትኩረት እየተሰራ ነው ያሉት የለውጡ አስቀጣይ ሙስጠፌ መሐመድ አሁን በተጎራባች ነዋሪዎቹ መካከል እየታየ ያለው አንድነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አመራራቸው ቁርጠኛ እንደሆነ አስታውቀዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው ለቱ ህዝቦች በአንድ ትልም የተፈጠሩ፣ በአንድነት የኖሩ እና ወደፊትም አብረው የሚኖሩ መሆናቸውን ጠቁመው  በኦሮሞ ታሪክ ታዋቂ የሆኑ ጀግኖች የሶማሌ እናቶች ወተት አጠጥተው የሶማሌ አባቶች ምርቃት እና ድጋፍ አድርገውላቸው ለድል በቅተዋል ሲሉም ተሰምተዋል፡፡

በክልል እሳቤ ብቻ ታጥሮ መቀመጥ አይገባም ያሉት አቶ ሽመልስ አብዲሳ አሁን ላይ የተገኘው ድል እና ነፃነት ስር እንዲሰድ እያንዳንዱ ዜጋ በጋራ በመስራት ኢትዮጵያን ወደ ፊት ለማራመድ መትጋት እንደሚኖርበት አሳስበዋል፡፡

የጥላቻ ንግግርን የሚያስወግደው “ቴክቫህ”፣ በኢትዮጵያ 300 ሺህ ተጠቃሚዎች አሉት

በኢትዮጵያ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጩ የጥላቻ ንግግርንና ሰተኛ መረጃዎችን በግለሰብ፣ በተለያዩ ተቋማትና መንግሥት ደረጃ ለመቆጣጠር የተለያዩ ጥረቶች በሚደረግበት በዚህ ወቅት በወጣቶች የተቋቋመው “ቴክቫህ ኢትዮጵያ” አመርቂ ውጤት እያሳየ መሆኑ ታወቀ፡፡

የኤክትሪካል ምህንድስና እና ኮምፒውተር ተማሪ የነበረችው አቅሌሲያ በዩንቨርስቲ ውስጥ እያሉ እሷና ጓደኞቿ የሚያገኙት መረጃ ትክክለኛት ለማረጋገጥ በእጅጉ ይቸገሩ እንደነበር ትናገራለች፡፡ ከፌስ ቡክ ገ ቀጥሎ ብቅ ያለው ቴሌ ግራም የመረጃ ማቅረቡን መንበር ሲቀላቀል በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ያሰበችው አቅሌሲያ አስተማማኝነቱ የተወራለትን ቴክቫህን መጠቀም ከጀመረች በኋላ በመረጃ መዛባት ረገድ ችግር እየገጠማት አለመሆኑን በአዲሱ አፕልኬሽን ዙሪያ ለበቢሲ አስተያየቷን በሰጠችበት ወቅት ጠቁማለች፡፡

“ቴክቫህ ኢትዮጵያ” በአሁኑ ወቅት ከ320 ሺህ በላይ የቤተሰብ አባላት ያሉት እና ቴሌግራም በተሰኘው የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ላይ መረጃ የሚያቀብል ገፅ ነው፡፡ ገፁን የሚቀላቀሉት ሁሉ የቤተሰብ አባላት ተብለው እንደሚጠሩ የሚናገረው የቴክሻህ ኢትዮጵያ መስራች ፀጋአብ ቴሌግራምን በስልኩ ላይ ጭኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዚህ ገጽ አባል ያደረጋቸው ስልኩ ላይ የሚገኙ ከሀያ እስከ ሰላሳ የሚደርሱ ሰዎችን ብቻ እንደነበር አስታውሷል፡፡

ቀስ በቀስ አንዱ ሌላውን እሰበና ስለ መረጃው ትክክለኛት እየመሰከረ የገፁ ተከታዮች ዛሬ የደረሰበት ደረጃ ላይ ደርሷል ተብሏል፡፡ የቴክህ ቤተሰቦች “ሰብዓዊነት ይቅደም” በሚለው መርህ አንድ ሆነናል ይላሉ፡፡ የጥላቻ ንግግሮችን የሚያስወግደው አዲስ ፕሮግራም በዚህ ወቅት ላይ ያለውን የፌስ ቡክ አመፅ እንቅስቃሴና ፕሮፓጋንዳ ለማርገብ መፍትሔ መሆኑን መስራቹ ጠቁመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከጠባቂዎቻቸው ጋር ችግኝ ተከሉ

አራት ቢሊዮን ችግኙ እስኪተከል ድረስ ዕረፍት የሌላቸው የሚመስሉት ጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ከግል ጠባቂዎቻቸው (ከሪፐብሊካን ጋርዶች) ጋር በመሆን በአዲስ አበባ ችግኝ ተክለዋል፡፡

የዛሬ ሳምንውን በሆነውና ገሪቱን በለም የክብር መዝገብ ላይ አስፍሯታል በተባለው የ300 ሚሊዮ ችግኝ ተከላ ወቅት ከአዲስ በባ ይልቅ ወደ ወላይታና አርባ ምንጭ መጓዝን የመረጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይለቱ በነቂስ ወጥቶ ታማኝነቱን ላሳያቸው አዲስ አበቤ  ምላሽ የሆነ ድርጊት ፈፅመዋል፡፡

ብዙዎች በፍጥነቱና በአሃዙ መጠን ላይ ባይስማሙመበትም እስካሁን ድረስ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል ተብሏል፡፡

በትናንትናው ዕለት ታማኝ የግል ጠባቂዎቻቸውና ከወራት በፊት ከተመረቁት የሪፐብሊካን ጋርዶች መሀል የተወሰኑትን ቀላቅለው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በአዲስ አበባ ከተማ ደምበል አባቢ በሚገኝ ሥፍራ ችግኝ ተክለዋል፡፡

የ4 ቢሊዮን ችግኝ ተከላ ፕሮግራሙን ወሰን የገጠርና የከተማ የመሬት ገፅታን አረንጓዴ ማድረግን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ለመርሃ ግብሩ ከ11 ቢሊዮን ብር በላይ ተመድቧል፡፡ ይህ የሆነው 45 በመቶው የህዝብ ተሳትፎ በጉልበት አስተዋፅኦ ማድረግ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ እንደሆነም እየተነገረ ነው፡፡

        በሶማሌ ክልል በነፃነት መኖር እንደሚልና ለዚህም ላፊነት እንደሚወስዱ አቶ ሙስጠፌ ገለፁ

ባለፉት ሦስት ዓመታት በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ ሥፍራዎች ለተከሰቱ ግጭቶች ምክንያቱ የግጦሽ መሬት ወይም የድንበር ጉዳዮች ሳይሆኑ የመንግሥት መዋቅር ያለበት አሻጥር እንደሆነ የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ መመድ ተናገሩ፡፡

“የህዝቡ ችግር በዘላቂነት የሚፈታው በማካለል ወይም በድንበር አይደለም፡፡ ህዝቡ አብሮ እንዲኖር የአመለካከት ለውጥ በማምጣት እና ሁሉንም ከልማት ተጠቃሚ ማድረግ ነው ያሉት የሶማሌ ክልል ፕሬዚደንት በሞያሌ ከተማ ዙሪያ ስለተፈጠረው ችግር ከአባቢው ነዋሪዎች አሮሚያ እና ከፌደራል መንግሥት ጋር በመወያየት መፍትሄ ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን አስረድዋል፡፡

ጥቃቶች በክልላችን እንዳይከሰቱ ዋነኛ ትኩረታችን በመሆኑ ባለፈው አንድ ዓመት ሰዎች ምንም ዓይነት ችግር አልገጠማቸውም ያሉት ፕሬዝዳንቱ ማንኛውም ሰው፣ የየትኛውም እምነት ተከታይ ሆኖ በነፃነት መኖር ይላል፣ ለዚህም የክልሉ መንግስት ላፊነቱን ይወስዳል ብለዋል፡፡

ተደጋጋሚ የሰብዊ መብት ጥሰት እንደሚፈም ክስ ሲቀርብበት የነበረው የሶማሌ ክልል ልዩ ሃይል ፖሊስ የአደረጃጀት ለውጦች ተካሂዶበታል ያሉት አቶ ሙስጠፌ አሁን ባለው የገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ልዩ ኃይል የሚያከናውናቸው ቀልጠፋ ስራዎች  ስላሉ አደረጃጀቱ አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁመው፤ ወደፊት የክልል ልዩ ኃይሎች ከፌደራል የፀጥታ አካላት ጋር ስለሚኖራቸው ቁርኝት ሕዝባዊ ውይይቶች ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከባድ የጦር መሳሪያ ያዘዋወሩ ግለሰቦች ፍ/ቤት ቀረቡ

በአዲስ አበባ ከተማ ሽጉጦችን፣ ጥይቶችንና ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ሲያዘዋውሩ የነበሩ ግለሰቦች በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ክስ ተመስርቶበቸዋል፡፡

ሰኔ 24 ቀን 2011 ዓ.ም ከሌሊቱ 10 ሰዓት ሁለት ከባድ መትረየስ እና አራት ሺህ የማካሮቭ ሽጉጥ ጥይት ሲያዘዋውሩ አዲስ አበባ ላይ በፖሊስ በቁጥጥር ስር ውለዋል  የተባሉት ግለሰቦች እነ ገብረ እግዚአብሔር ወርቁ በሚል መዝገብ ክስ ፋይል ከፍቶባቸዋል፡፡

ሐምሌ 24 ቀን 2011 ዓ.ም የዋለው ችሎት በአዲስ አበባ ሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ ካባቢ የተያዙት ተጠርጣሪዎች ያቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ፍ/ቤቱ ተቀብሎ ፈቅዶ የነበረ ቢሆንም ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ በማለቱ ዋስትናው ታግዶ እንዲቆይ ተወስኗል፡፡

በሌላ በኩል “እነ አወቀ አስረስ” በሚል የክስ መዝገብ ጉዳያቸው የታየ ሁለት ግለሰቦች ከ8 ሺኅ በላይ የተለያዩ የሽጉጥ ጥይቶችን፣ ሁለት ብሬይል አንድ ማካሮቭ ሽጉጥ ሲያዘወወሩ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኔ 18 ቀን 2011 ዓ.ም ነበር በቁጥጥር ስር ያዋላቸው፡፡ዚህም ተከሳሾች በ50 ሺኅ ብር ዋስትና እንወጡ መጀመሪያ ፍርድ  ቤት መፍቀዱን ተከትሎ ዐቃቤ ሕግ በተመሳሳይ ይግባኝ በማለቱ ተከሳሾቹ በእስር እንዲቆዩ ተደርጓል፡፡

በተያያዘ ዜና “እነ በድሉ ተስፋዬ” በሚል የክስ መዝገብ ጉዳያቸው የታየ ሌሎች ተከሳሾች 16 ባለሰደፍ ክላሽንኮቭ፣ 11 ታጣፊ ክላሽ እንዲሁም ሁለት ሺኅ የክላሽ ጥይት በከተማው ውሥጥ ሲዘዋወሩ በቁጥጥር ሥር እንዋሉ ተነግሯል፡፡ የተያዙት መሣሪያዎች የቱርክ፣ የሶሪያ እና የግብፅ ስሪት መሆናቸው ታውቋል፡፤

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በገሪቱ የተለያዩዩ ስፍዎች የታየው የጦር መሳሪያዎች ዝውውር አዲስ አበባም በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሏል፡፡ መንግሥት ስርጭቱን ለመቆጣጠር የተለያዩ ዕርምጃዎችን እየወሰደ ሲሆን፣ መላላት ይታይበታል የሚባለውን  የጦር መሳሪያ ቁጥር አንቀፆች  የሚያጠናክር አዲስ አዋጅ ማርቀቁም አይዘነጋም፡፡

LEAVE A REPLY