የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ነሐሴ 3 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ነሐሴ 3 ቀን 2011 ዓ.ም

 በምዕራብ ሀረርጌ ታጣቂዎች በህዝብ ላይ ተኩስ ከፍተው 7 ሰው ገደሉ

በተወሰነ ደረጃ ተረጋግቶ የነበረው የምዕራብ ወለጋ የታጣቂዎች እንቅስቃሴ ፊቱን ወደምዕራብ ሀረርጌ እንዳዞረ የሚወጡ መረጃዎች እየጠቆሙ ናቸው፡፡

በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሀረርጌ ዞን ጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ በተፈተረ የፀጥታ ችግር የሰዎች ህይወት ማለፉ ተረጋግጧል፡፡ የክልሉ መንግስትም የተፈጠረውን ችግር አምኗል፡፡

ጉምቢ ቦርደዴ ወረዳ ጉምቢ ቀበሌ ግምጃ ቤት በተባለ አካባቢ ታጣቂዎቹ አደጋውን እንዳደረሱ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል፡፡

እነዚህ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ በሰው ህይወትና አካል ላይ ጉዳት የደረሰ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን እስካሁን 7 ሰዎች እንደሞቱና 3 ሰዎች እንደቆሰሉ የዞኑ ጸጥታ ቢሮ ዘግየት ብሎ ይፋ አድርጓል፡፡

በሰላማዊ ዜጎች ላይ ታጣቂዎች ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ መከላከያና ፌደራል ፖሊስ በአሁን ሰዓት ወደ ስፍራው ተጉዘዋል፡፡ በምዕራብ ሀረርጌ አካባቢ ቀደም ባሉት ወራት የኦነግ ባንዲራን በይፋ ይዘው የሚንቀሳቀሱ አካላት በስፋት መኖራቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ እስካሁን ጥቃቱን ያደረሰው አካል ማንነት በይፋ አልተነገረም። 

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጆሃንስበርግ የታሰሩ፣ ኢትዮጵያውያንን እየተከታተልኩ ነው አለ

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በደቡብ አፍሪካ፣ ጆሃንስበርግ ከተማ የታሰሩትን ኢትዮጵያውያን ጉዳይ በጥልቀት እየተከታተልኩ ነው ሲል ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡ መ/ቤቱ የታሰሩት ዜጎች ብዛትን ቢቢሲ ከዘገበው በግማሽ ያህል ቀንሶ 600 ብቻ ናቸው ሲል ተናግሯል፡

በጆሃንስበርግ አባቢ በሚገኝ የንግድ ማዕከል በተረገ ፍተሻና አለመግባባት 600 ኢትዮጵያውን ተይዘዋል ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነቢያት ጌታቸው ናቸው፡፡ ለጊዜው ጉዳያቸው ተጣርቶ የተለቀቁ ኢትዮጵያውያን ቁጥርን ለማወቅ ባይቻልም በጥቅሉ በደቡብ አፍሪቃ የፀጥታ አስከባሪዎች 150 ኢትዮጵያውያን መያዛቸውን የሚያሳይ መረጃ አለን ሲሉም የተምታታ መግለጫ ሲሰጡ ተሰምተዋል፡፡

ኢትዮጵያውያን በብዛት ኑሮአቸውን በመሰረቱበትና ሥራቸው በሚያካሄዱበት የጆሃንስበርግ የንግድ ማዕከል ከህግ አስፈፃሚዎች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት የተነሳ ሕጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ ያላቸው ጭምር በጅምላ ተይዘዋል ያሉት ቃል አቀባዩ በገበያ ማዕከሉ ከታክስ አከፋፈል ባልተፈቀዱ የንግድ አይነቶችና ከኮንትሮባንድ ንግድ ጋር በተገናኘ ምክንያት የተነሱ አለመግባባቶች ኢትዮጵያውያኑንና ፖሊሶቹን ሊያጋጫቸው እንደቻለ ጠቁመዋል፡፡

በገበያ ማዕከሉ ውስጥ የኢትዮጵያውያን ቁጥር ቢበዛም የሌሎች ገር ዜጎችም በፍተሻውና ባለመግባባቱ ምክንያት በደቡብ አፍሪ ፖሊስ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ያመላከቱት አቶ ነቢያት ጌታቸው ጉዳዩን በደቡብ አፍሪ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነም አረጋግጠዋል፡፡  

በሙሰኞች የተዘረፈ ከ 95 ሚሊዮን ብር በላይ ወደ መንግስት ካዝና ተመለሰ

በከባድ የሙስና ወንጀል ድርጊት ተጠርጥረው ክስ ከተመሰረተባቸው ተከሳሾች ላይ ያለ አግባብ የተዘረ ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ ወደ መንግሥት ካዝና እንገባ ማስቻሉን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ገልጿል፡፡

ያለአግባብ የተዘረፉ የመንግስትና የህዝብ ሀብት የሆኑ ንብረትና ገንዘቦችን ለማስመለስ ትኩረት ሰጥቶ በ2011 ዓ.ም የተንቀሳቀሰው ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በዚህ ዘርፍ ተሰማርተዋል ያላቸውን ግለሰቦች በሕግ ተጠያቂ ማድረጉ እንዳለ ሆኖ፣ በተከሳሾች በህገ – ወጥ መንገድ የተመዘበረ፣ ከ95 ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ወደ መንግሥት ተመላሽ እንዲሆን ማድረጉን የመ/ቤቱ የሕዝብ ግንኙነት ሐላፊ አቶ ዝናቡ ቱኑ አስታውቀዋል፡፡

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ሌሎች ያለ አግባብ የተዘረፉ የመንግሥትና የሕዝብ ንብረቶችንና ገንዘቦች ለማስመለስ ጠንካራ ክርክር እያደረገ መሆኑም ተነግሯል፡፡ በመንግሥት ተቋማት በከባድ የሙስና ወንጀል የተዘፈቁ አባላትን ተጠያቂ ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰራበትን አዲስ መንገድ ቀይሶ በከፍተኛ ደረጃ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነም ተነግሯል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርክ ሠራተኞች በደምወዝ ማነስ ምክንያት እየፈለሱ ነው

ከፍተኛ የሆነ የሠራተኛ ፍልሰት ይፈታተናቸዋል በሚባሉት የኢንዱስትሪ ፓርኮች የራ ሁኔታው የተረጋጋ እንን የተቀጣሪዎች ደመወዝ ሊታሰብበት ይገባል ተብሏል፡፡ ሠራተኞቹ ወደ ራ ከመግባታቸው በፊት የሕይወት ክህሎት ሥልጠና ቢወስዱ የሰራተኞቹን ፍልሰት መከላከል የፓርኮቹን ደህንነትም ማስጠበቅ እንደሚቻል ተጠቁሟል፡፡

በዛሬው ዕለት በጉዳዩ ላይ በሂልተን ሆቴል እየመከረ የሚገኘው የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ውይይት ላይ ባለሀብቶች የተለያዩ የልማት ድርጅቶች ጉዳዩ የሚያገባቸው ግለሰቦችና መንግሥታዊ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በአንዳንድ የኢንዱስትሪ ፓርኮች አካባቢ ሠራተኞች በደወዝ ማነስ ምክንያት ሥራቸውን በመልቀቅ ላይ ስለሆኑ፣ እነዚህ ራተኞች ተረጋግተው እንዲሰሩ ለራሳቸውና ለገራቸውም ለውጥ እንዲያመጡ የደምወዛቸው ነገር ቢታሰብበት መልካም ነው ሲሉ የውይይቱ ተሳታፊዎች ሳብ አቅርበዋል፡፡

የቅጥር ዕድሜ ክልል ከ18 እስከ 24 ከሚለ ተጨማሪ በሌላ የዕድሜ ደረጃ የሚገኙ ሠራተኖችንም ማቀላቀል ቢቻል መልካም እንደሆነም ከሚመለከታቸው አካላት በኩል ሀሳብ ቀርቧል፡፡

4 የሕክምና 1 የምግብ ፍተሻ ላብራቶሪዎች ዓለም አቀፍ እውቅና ተሰጣቸው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክሬዲቴሽን ጽሕፈት ቤት ለአራት የሕክምና እና ለአንድ የምግብ የፍተሻ ላብራቶሪዎች የላቀ ዕውቅና (አክሪዴቴሽን) ሰጠ፡፡

ለተቋማቱ ነሀሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ዕውቅና በተሰጠበት ወቅት የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ፍስሃ፤ የአክሬዲቴሽን ተጠቃሚ ለመሆን ለጽሕፈት ቤቱ ማመልከቻ ያቀረቡ በርካታ ድርጅቶች ቢኖሩም የተቀመጠውን ዓለም አቀፍና እና ብሔራዊ መስፈርቶችን አሟልተው ዕውቅናው የተሰጣቸው አራት የሕክምና አንድ ደግሞ የምግብ ፍተሻ ላብራቶሪዎች ብቻ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

አይ.ኤስ. 15189 በሕክምና ዘርፍ ላብራቶሪ አራት ተቋማት የአክሬዲቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ ሲሆኑ፣ እነዚህ ተቋማት አክሬዲሽን አገልግሎት ተጠቃሚ ለመሆን ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት በሰነዶቻቸውና በመስክ ተገምግመው ዓለም አቀፍ ዕውቅና ይገባቸዋል ተብሎ በጽሕፈት ቤቱ የአክሬዲቴሽን አጽዳቂ ኮሚቴ አክሬዴቴሽኑ” ፀድቆላቸዋል ተብሏል፡፡

በዚህም መሰረት የትግራይ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የሕብረተሰብ ጤና ላብራቶሪዎች የቲቢ በሽታን በጅን መመርመር የሚያስችል የፍተሻ ወሰን፣ነቀምት ሕብረተሰብ ጤና ምርምር ሪፈራል ላብራቶሪ በኤች.አይ. የፍተ ወሰን የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በማይክሮ ባዮሎጂና በክሊኒካል ኬሚስትሪ የፍተሻ ወሰን የአክሬዲቴሽን ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

አይ.ኤስ.ኤ / አይ.ኢ..ሲ 17025 በምግብ ፍተሻ ላብራቶሪ ብለስ አግሪ ፉድ ላብራቶሪ ሰርቪስ ሐላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባኒያ በማይክሮ ባዮሎጂና በኬሚካል የፍተሻ ወሰን የአክሬዲቴሽን አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሆነ ተረጋግጧል፡፡

በቀን 7ሺ 500 ኪሎ ግራም ቡና የሚያቀነባብር ፋብሪካ በአ/አ ተከፈተ

ቡና ኤክስፖርት ንግድ ዘርፍን ከፍ ሊያደርግ የሚችልና በቀን 7ሺህ 500 ኪሎ ግራም ቆልቶ ፈጭቶና አሽጎ የሚያቀርብ የቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በአዲስ አበባ ስራ ጀምሯል፡፡

በትውልድ ኢትዮጵያዊ በዜግነት ሆላንዳዊ በሆኑት በአቶ ሠለሞን ካሳና በወይዘሮ ሙሉ ለገሰ ባለቤትነት የተቋቋመው “ሜላንዥ ኮፊ ሮስተር” የተሰኘ ዘመናዊ የቡና ማቀናበበሪያ ትናንት ነሀሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም ተመርቋል፡፡

ፋብሪካገሪቱን የቡና ኤክስፖት ንግድ ዘርፍ ለማሳደግ ደረጃውን የጠበቀ ቡና ቆልቶ፣ ፈጭቶና አሽጎ፤ ለገር ውስጥና ለውጭ ገበያ እንደሚያቀርብ ታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY