የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ነሐሴ 5 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ነሐሴ 5 ቀን 2011 ዓ.ም

አዲስ አበባ የመሬት መንቀጥቀጥ (መንሸራተት) ያሰጋታል

የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ በዘንድሮው ክረምት ወራት እያጋጠመ ካለው ዝናብ ጋር ተያይዞ አዲሰ አበባ ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት እንደሚያጋጥማት ከወዲሁ አስታውቋል፡፡  

ከነሐሴ 1 እስከ 30 ድረስ ሊከሰት ይችላል የተባለው የመሬት መንሸራተት በክረምቱ ወራት   ዝናብ መጠን የሚያገኙ   የኢትዮጵያ ክፍሎች ውስጥ ያልታሰበ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት ሊከሰት እንደሚችል ኤጀንሲው አረጋግጧል፡፡

አዲስ አበባ በመሬት መንሸራተት ልትመታ ስለምትችል ነዋሪው ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንዲጀምር ከወዲሁ ያሳሰበው የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ከመዲናዋ አዲስአበባ በተጨማሪ የዝናብ ስርጭቱ በበርካታ አካባቢዎች ላይ ጎልቶ የሚታይ ከመሆኑ አኳያ ተመሳሳይ ችግር ሊከሰት የሚችልበት ሁኔታ መኖሩንም አመላክቷል፡፡

በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች የድንገተኛ ጎርፍና መሬት መንሸራተት ችግሮች ያጋጥማቸዋል በሚባሉት ቦታዎች የጎርፍ አደጋ፣ አደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን የቅድመ ጥንቃቄ ሥራ  እያከናወነ ይገኛል፡፡ ወንዝና ውሃ ዳር የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎችም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተጓዳኝ ሥራዎችን እያከናወንኩ ነውም ብሏልቢሮው፡፡

በተማሪም ኮሚሽኑ በአንፃሩ ውሃ አጠር ይሆናሉ ተብለው በተተነበዩት በምስራቅና ሰሜን አካባቢዎች ላይ ሊከሰት የሚችለውን የውሃ እጥረት ከግምት በማስገባት ከወዲሁ አስፈላጊውን ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡

መቀመጫውን መቀሌ ያደረገ የአየር ትራንስፖርት በ3.7 ቢሊዮን ብር ሊቋቋም ነው

ኑሮአቸውን በአሜሪካን ያደረጉ ትውልደ ኢትዮጵውያን መቀመጫውን በመቀሌ ያደረገ አዲስ የአየር ትራንስፖርት ለማቋቋም መሰናዶአቸውን እንዳጠናቀቁ ገለጹ፡፡

ኖርዝ ስታርየሚ ስያሜ የተሰጠው አዲሱ የአየር ትራንስፖርት በ3.7 ቢሊዮን እንደሚቋቋም ባለድርሻ አካላቱ በፕላኔት ሆቴል ባዘጋጁት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ገልጸዋል፡፡

የአየር ትራንስፖርት ኩባንያው መቀመጫውን በአሁኑ ሰዓት ከፌደራል መንግስቱ ትዕዛዝ እያፈነገጠች ነው በምትባለው የትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀሌ ያደረገውበአዲስ አበባ ያለውን የአየር መጨናነቅ በመሸሸ እንደሆነም በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡ ኩባንያው ባህርዳር እና ድሬደዋ ከተማን መቀመጫው ለማድረግ አስቦ ነበርም ተብሏል፡፡

በኢትዮጵያ እና በኤርትራ በኩል የተደረገውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የንግድ ማዕከል ልትሆን ትችላለች በሚል መቀሌን እንደመረጡ የጠቆሙት ኖርዝ ስታሮች ድርጅታቸው መቀመጫውን ከአዲስ አበባ ውጭ ያደረገ የመጀመሪያው አየርመንገድ እንደሆነ መስክረዋል፡፡

ከሦስት ዓመታት በኋላ መንገደኞችን ወደማጓጓዝ ሥራ ይገባል የተባለው ኩባንያ በቀጣይ በተለያዩ ደረጃዎች የእቃ ማመላለሻየባለሙያዎች ማሰልጠኛና የጥገና ክፍል እንደሚኖረውም ተወርቷል፡፡

መቀመጫው መቀሌ የሚሆነው የአየር ትራንስፖርት፤ ቅድሚ የኢትዮጵያ አየር መንገድ መዳረሻ ካደረጋቸው ሃገራት ውጪ ሥራውን ለመጀመር ዕቅድ ይዟል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ አየር መንገድን ጨምሮ አበርዲንአቢሲኒያኢስት አፍሪካናሽናል እና ትራንስ የተሰኙ ስድስት አየር መንገዶች እንዳሉ አይዘነጋም፡፡

ኢትዮጵያ ትልቁን የነዳጅ ማጠራቀሚያ (ዴፖ) ልትገነባ ነው

እስካሁን ድረስ በሃገሪቱ ከተገነቡ ማጠራቀሚያዎች ሁሉ በመያዝ አቅሙ ከፍተኛ የሆነውን የነዳጅ ማጠራቀሚያ (ዴፖ) ኢትዮጵያ ልትገነባ ጥናቶችን እያካሄደች መሆኑ ተሰማ፡፡

ጥናቱን እያስጠና የሚገኘው የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት በሃገር አቀፍ ደረጃ እየጨመረ የመጣውን ነዳጅ ፍላጎት ለማርካትና እጥረት በሚያጋጥምበት ወቅትም ረዘም ላለ ጊዜ ከክምችት በማውጣት በማደያዎች አማካይነት ለሕብረተሰቡ ለማከፋፈል በማሰብ ግንባታውን ዕውን ሊያደር ማቀዱን ለአዲስ ማለዳ አስታውቋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ዱከም አካባቢ እንዲገነባ የታሰበው ይህ የነዳጅ ማጠራቀሚያየተጠቀሰው ቦታ የተመረጠበት ዋነኛ ምክንያት ዱከም ከሚገኘው የኢትዮጅቡቲ የባቡር ጣቢያ” በቅርብ ርቀት እንዲገኝ በማሰብ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ቦታው የማጓጓዣ ወጪዎችን ለመቀነስም ዓይነተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ታምኖበታል፡፡ በአንድ የባቡር ጉዞ የሚጓጓዘው የነዳጅ መጠን 72 መኪኖች በአንድ ጊዜ ሊያመላልሱት ከሚችሉት የነዳጅ መጠን ጋር እኩል መሆኑም ተረጋግጧል፡፡

ከዚህ በፊት በአፋር ክልል 30 ሺኅ ሜትሪክ ቶን የሚይዝ የነዳጅ ማጠራቀሚያ መገንባቱ      ታወሳል፡፡ አዲሱ የነዳጅ ማጠራቀሚያ 3 መቶ ሺኅ ቶን  የመያዝ አቅም ያለው ሲሆን፣ በ2012 ዓ.ም በጀት ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ግንባታው ሲጀመር፣ በ10 ሺኅ ካሬ ሜትር ላይ 150 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደሚሆንበትም ይፋ ተደርጓል፡፡

የሂሳብ ጉድለት ከነበረባቸው መሐል 32 ተቋማት 66 ሚሊዮን ብር መለሱ

በተጠናቀቀው በጀት ዓመ  መጀመሪያው ስድስት ወራት የሂሳብ ጉድለት  ከነበረባቸው 59 ተቋማት መሐል 32ቱ ከተማ አስተዳደሩ በርካታ ገንዘብ ተመላሽ ማድረጋቸው ተነገረ፡፡

እንደ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና ኦዲተር ወይዘሮ ፅጌወይን ካሳ ገለጻ ከሆነ በ2011 ዓ.ም በሁለተኛው ግማሽ ዓመት በተሰራው ልዩ ኦዲት በአምስት ክፍለ ከተሞች በድምሩ 121 ሚሊዮን 365 ሺኅ 398 ብር ጉድለት ተመዝግቧል፡፡

በመጀመሪያው ስድስት ወራት በተከናወነው የኦዲት ሥራ በ59 ተቋማት ላይ የሂሳብ ጉድለት ተገኝቷል፡፡ በዚህም መሰረት ዐቃቤ ሕግ ተቋማቱን ተጠያቂ ለማድረግ አቅጣጫ ቢተላለፍምበሁለተኛው መንፈቅ ዓመት 32ቱ ተቋማት 66 ሚሊዮን 774 ሺኅ 741 ብር ከ75 ሣንቲም ተመላሽ አድርገዋል፡፡

ተቋማቱ የጥሬ ገንዘብ ጉድለትውዝፍ ሂሳብ፣ ተመላሽ ያልተደረገ ቅድመ ክፍያከመመሪያ ውጭ የተከፈለ ተጨማሪ አበልና ደምወዝያለአግባብ ግዢ ፈጽመው ተመላሽ የተደረጉ መሆናቸውን በተደረገው ምርመራ ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡        

በሸገር ግለሰቦች በጠራራ ፀሐይ በጥይት እየተገደሉ ነው  

ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ በመሳሪያ የሚወሰድ ግድያና ጥቃት መባባሱን የሚያመላክቱ መረጃዎች እየወጡ ናቸው፡፡

ረቡዕ ነሐሴ 22 ቀን ቦሌ መንገድ ላይ አንድ ግለሰብ ተኩስ ከፍቶ ሁለት ሰዎችን ገድሏል፡፡ ጥቃቱን ያደረሰው ግለሰብ አስቀድሞ ከአንድ ሰው ጋር ግብግብ የፈጠረው ሞባይሌን ሊሰርቀኝ ነበር በሚል ምክንያት እንደሆነ በቦታው የነበሩ የአይን እማኞች ይናገራሉ፡፡

ሞባይሌን ሊሰርቅ ነበር የሚለው ግለሰብ ሽጉጥ አውጥቶ  ጭንቅላቱን ተኩሶ በመምታት ወዲያው ወደመኪናው በመግባት ለማምለጥ ሞክሮም ነበር፡፡ ገዳዩን በሳይክል ሲከታተል የነበረ አንድ ግለሰብም በተመሳሳይ ሁኔታ፣ እሱም በሽጉጥ ተመትቶ ወድቋል፡፡

ጥቃት አድራሹ ግለሰብ ለማምለጥ ያደረገው ሙከራ የትራፊክ መንገዱ በመጨናነቁ ሳይሳካለት በመቅረቱመኪናውን ጥሎ ለማምለጥ ሲሞክር ሲከታተሉት በነበሩ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር  ሏል፡፡

በተያያዘ ዜና 40 ዓመት የሚጠጋ ዕስር የተፈረደበት ፖሊስሰኞ ዕለት ሐምሌ 29 ቀን 2011 ዓ.ም በሚከታተሉት ፖሊሶች ላይ ተኩስ ከፍቶ ጥይት በመጨረሱ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ታወቀ፡፡

በወቅቱ ቃሊቲ ማረሚ ቤት አካባቢ የትራፊክ እንቅስቃሴን ስታስተባብር የነበረች አንዲት የትራፊክ ፖሊስ ባልደረባ በተኩሱ ጉዳት ደርሶባታል፡፡

የሚከታተሉትን ፖሊሶች ለማምለጥ ላዳ ታክሲ ተከራይቶ ከግብረ አበሮቹ ጋር ሲጓዝ የነበረው ወንጀለኛ ከፊቱ መንገዱን በፒክ አፕ መኪና ዘግተው እጅ እንዲሰጥ የጠየቁት የፀጥታ ሃይሎች ላይ በያዘው ስታር ሽጉጥ ዳግመኛ ተኩስ ከፍቶ ጥይቱን ሲጨርስ ለማምለጥ ሙከራ አድርጎ ነበር፡፡

የአንድ መጋዘን ጣራ ላይ በመውጣት ለማምለጥ የሞከረው ግለሰብ በፖሊሶች ቁጥጥር ሥር ውሎ ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጽ/ቤት መላኩ ታውቋል፡፡

ይህን ድርጊት በዕለቱ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ነበራቸው የቀድሞ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አብዲ ዒሌን ከማስመለጥ ጋር ግንኙነት እንዳለው በመጠቆም ረቡዕ ነሀሴ 1 ቀን የወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቦት ነበር፡፡ ጉዳዩን አስመልክቶ ምላሽ የሰጠው የቃሊቲ ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት ግርግሩ ፈጽሞ ከአብዲ ዒሌ ማስመለጥ ጋር ግንኙነት እንደሌለው አስረድቷል፡፡                

LEAVE A REPLY