የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ነሐሴ 6 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ነሐሴ 6 ቀን 2011 ዓ.ም

ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ የኢትዮጵያን 350 ሚሊዮን ችግኞች አላውቅም አለ

ከሁለት ሳምንታት በፊት ሐምሌ 22 ቀን 2011 ዓ.ም በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ ኢትዮጵያ 350 ሚሊዮን ዛፎች በመትከል የዓለም ሪከርድ ሰብሪያለሁ ስትል ያወጣችውን መግለጫ ዓለም አቀፉ የክብር መዝገብ እንደማያውቀው አረጋገጠ፡፡

በወቅቱ ኢትዮጵያ በ12 ሰዓታት ውስጥ 200 ሚሊዮን ዛፎችን ለመትከል ቆርጣ ተነስታ ፣ በቀኑ መገባደጃ ላይ 350 ሚሊዮን ዛፎች በመትከል መርሃ ግብሯን እንዳጠናቀቀች  የፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ  ዶ/ር ጌታሁን መኩሪያ በይፋ መግለፃቸው የሚዘነጋ አይደለም፡፡

የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩን በሁሉም ሚዲያዎች ከሥር ከሥር መረጃውን እየተቀበሉ ሲያስተላልፉ የነበሩ ጋዜጠኞች  በስድስት ሰዓቱ ዜና እወጃቸው የችግኝ ተከላው 70 ሚሊዮን እንደደረሰ  መናገራቸው ይታወሳል፡፡ እነኚሁ ሚዲያዎች በእኩለ ቀን ሕንድ በ66 ሚሊዮን ዛፎች ይዛው የነበረውን ሪከርድ ኢትዮጵያ እንደሰበረቸው የገለጹልንን ቁጥር በአምስት እጥፍ አብዝተው ከቀኑ አስር ሰዓት ላይ ከ300 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን መዘገባቸው ብዙዎችን ጥርጣሬ ውስጥ ከትቶ ነበር፡፡

ብዙኃኑ ሕብረተሰብ ለችግኝ ተከላው የወጣውና ወደ ቤቱ የተመለሰው ከንጋት እስከ ረፋድ መሆኑ እየታወቀ፤ የ70 ሚሊዮኑ የግማሽ ቀን ዘገባ ከሰዓት በኋላ 350 ሚሊዮን  ያደረሱት አካላት ወደየቤቱ የተመለሰውን ሕዝብ በምን መንገድ ሲያስተክሉት እንደዋሉ እስካሁን ድረስ ለማወቅ አልተቻለም፡፡

ይህን መሰሉ የጥንቃቄና የቁጥር ትክክለኛነት ጥያቄ እየቀረበ ባለበት ወቅት ጉዳዩ የሚመለከተው የዓለም ድንቃ ድንቅ ድርጊቶችን መዝጋቢው ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ የዛፍ ተከላውን ሪከርድ  የመሰበር ሙከራውን ለማረጋገጥ ከኢትዮጵያ መንግሥት  የደረሰው ምንም ዓይነት ማመልከቻ እንደሌለ አስታውቋል፡፡

“ምንም ዓይነት ሪከርድ ሲሰበር እኛ በንቃት እንከታተላለን፡፡ የዝግጅቱ አስተናባሪዎች ደግሞ ሪከርዱ ሲሰበር እንድንመዘግብላቸው ማመልከቻ እንዲያስገቡ እንመክራለን፡፡” የሚሉት የድርጅቱ ቃል አቀባይ ጄሲካ ዳውስ ፣ኢትዮጵያ በትክክል ሪከርዱን ሰብራ ከሆነ ምን ያህል ሰዎች እንደተሳተፉ ፣ የት እና መቼ እንደተከናወነ የሚገልፅ ውልያለው መረጃ መስጠት ይኖርባታል፡፡ አልፎ ተርፎም ሁለት ገለልተኛ ምስክሮች ሪከርዱ መሰበሩን በሥፍራው ተገኝተው ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ግዙፏ የህዋ ጣቢያ ዛሬ ማታ የአዲስ አበባ ሰማይን ታቋርጣለች

ዛሬ ሴ 6 ቀን 2011 ዓ.ም  ምሽት 1 ሰዓት 52 ደቂቃ በህዋ ላይ እየተንቀሳቀሰች መረጃዎችን የምትሰበስበው ዓለም አቀፍ የህዋ ጣቢያ በአዲስ አበባ ሰማይ ላይ እንደምታቋርጥ ተነገረ፡፡

አየሩ ደመናማ ሆኖ ካልጋረዳት በስተቀር፣ አመቺ ቦታ ላ ከተሆነ ያለ ምንም መሳሪያ እገዛ በዓይን ልትታይ እንደምትችል ታውቋል፡፡ የህዋ ጣቢያዋ ከመሬት ስበት ውጪ የምትሽከረከር ናት፡፡ አንድ የእግር ኳስ ሜዳን የምታክለው ጣቢያዋ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ምርምሮችና ሙከራዎች ያለማቋረጥ በውስጧ ባሉ ባለሙያዎችና በራሷ አማካይነት ታካሂዳለች፡፡

በምድር ዙሪያ ተንሳሳፊ የሆነችው በዚች የህዋ የሙከራ ጣቢያ ምድር ላይ ላለው የሰው ልጅ ጠቀሜታ ያላቸው ምርምሮችን ከማድረግ ባሻገር ለዘለቄታው የህዋ አሰሳ የሚጠቅሙ መረጃዎችን እንደምትሰበስብ ነው እየተገለጸ ያለው፡፡

ዛሬ ምሽት ለሁለት ሰዓት ስምንት ደቂቃዎች ሲቀሩ የአዲስ አበባ ሰማይን ስታቋርጥ ትታያለች የተባለችው የህዋ ጣቢያ ግዙፍ አውሮፕላን ወይም እጅግ ደማቅ በሰማይ ላይ የምትንሳፈፍ ኮከብ የምትመስል  ስትሆን ፤ የጉዞ መስመሯን ሳትቀይር በአንድ አቅጣጫ ትጓዛለች፡፡

አውሮፕላን ከሚጓዝበት ፍጥነት እጅግ በበለጠ ሁኔታ በሰማይ ላይ የምትበረው፣ በሰዓት 28 ሺህ ኪሎ ሜትርሮችን በመጓዝ በየዘጠና ደቂቃው ዓለምን የምትዞረው የህዋ ጣቢያ ውስጥ ያሉ ጠፈርተኞች ከዚህ የተነሳ በየዕለቱ ፀሐይ 16 ጊዜ ስትጠልቅና ስትወጣ የማየት ዕድል አላቸው፡፡                  

LEAVE A REPLY