አሜሪካ አገር የሚኖሩና «ምሁራን» ነን በሚሉ አገር ለመመስረት የተደራጁ የኦሮሞ ብሔርተኞችና በኦነግ ደጋፊ አሜሪካውያን ርዳታ የተቋቋመ አንድ ማኅበር አለ። ማኅበሩ «የኦሮሞ የጥናት ማኅበር» ወይንም በእንግሊዝኛ አጠራሩ [Oromo Studies Association (OSA)] ይባላል።
ብሔርተኞቹ ኦነጋውያን ማኅበሩን «የጥናት ማኅበር» ቢሉትም በኦሮሞ ጥናት ጥርሱን የነቀለው Brian Yates የተባለው የSt. Joseph University የታሪክ ፕሮፌሰር ግን «Invisible Actors: The Oromo and the Creation of Modern Ethiopia (1855–1913)» በሚል እ.ኤ.አ. በ2011 ባሳተመው መጽሐፉ በOSA ጉባኤ የሚቀርቡት ወረቀቶች የሚታተሙበት የJournal of Oromo Studies ወረቀቶች ጥናት ለመባል የማይበቁ፣ አንዴም በindependent reviewer ተገምግመው ያላለፉና የኦሮሞ ብሔርተኛ ፖለቲከኞች ፍላጎት ብቻ የሚስተናገዱባቸው የፕሮፓጋንዳ ፓምፕሌቶች መሆናቸውን የአሰፋ ጃለታና መሰል ኦነጋውያንን የፈጠራ ትርክቶች በአብነት በማቅረብ ያስረዳል።
እኔም የOSA ኅትመቶችን በሙሉ እንደመረመረ ሰው ፕሮፌሰር ብሪያን በሚለው እስማማለሁ። በOSA ጉባኤ ወረቀት የሚያቀርቡ ኦነጋውያን ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች እሽቅድምድም ታይቶና ተሰምቶ የማይታወቅ የፈጠራ ታሪክና የሐጢዓት ክስ የማምረት ይመስላል። አንዱ ኦነጋዊ ዶክተር በአንዱ የOSA ጉባኤ ግኝቴ ያለውን «ምኒልክ ኦሮሞን ጨፍጭፏል» ብሎ ሲያቀርብ ሌላኛው የመንፈስ ወንድሙ ደግሞ በቀጣዩ የOSA ጉባኤ ባቀረበው ዝባዝንኬ «ምኒልክ አምስት ሚሊዮን ኦሮሞ ጨፍጭፏል» ብሎ ሌላ ሸቀጥ አመረተ።
በዚህ በሁለቱ ኦነጋውያን ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች ፉክክር የተማረከው ሌላኛው ያበደ ኦነጋዊ በተከታዩ የOSA ጉባኤ ቀርቦ «አፍሪካዊ ሂትለር ነው» በማለት ከሱ በፊት በተካሄደው የOSA ጉባኤ ጥናት አቀረብሁ ያለው ሰውዬ ምኒልክ ጨፈጨፋቸው ያላቸውን ኦሮሞዎች ቁጥር ሂትለር ከጨፈጨፋቸው አይሁዶች ቁጥር ጋር ለማስተካከልና ምኒልክን «የአፍሪካ ሂትለር» ለማድረግ ተጨፈጨፉ የተባሉትን ኦሮሞዎች ቁጥር ወደ ስድስት ሚሊዮን በማሳደግ ሳይማር መጠምጠሙ ሳያንሰው ጉባኤውን ወሲባዊ ብስጭቱን ወደ ፖለቲካ ለወጠበት። የOSA መድረኮች ሁሉ በዚህ መልክ የበለጠ በመዋሸት ተቀባይነት ለማግኘት ኦነጋውያን ዶክተሮችና ፕሮፌሰሮች የፈጠራ ታሪክ ውድድር የሚያቀርቡባቸው አስቀያሚ ቲያትሮች ናቸው።
በጥናት ስም የተቋቋመው OSA ከሰሞኑም አዲስ አበባ ውስጥ አካሄድሁት ያለውን የሰላሳ አራተኛ ዓመት ጉባኤውን በሙሉ ለመከታተል ሞክሬ ነበር። ማኅበሩ ዘንድሮም እንደ ድሮው ነው። ማኅበሩ የኦሮሞ ጥናት ማኅበር ነኝ ቢልም ዘንድሮም ልክ እንዳለፉት ሰላሳ አራት ዓመታት ሁሉ የወረቀት አቅራቢዎቹ ማዕከል መከረኛው አማራ ነው። መቼ ይሆን በኦሮሞ ስም ተቋቋምሁ የሚለው የዚህ ማኅበር ወረቀቶች አማራን ሳያወግዙ ስለ ኦሮሞ የሚያወሩትና ኦሮሞን ብቻ ማዕከል አድርገው መቅረብ የሚጀምረው?
መቼስ ይሆን ስለ ኦሮሞ ተቋቋምሁ የሚለው ማኅበር መዝጊያ አማራን ሳያወግዝ ስለኦሮሞ ያስጠናውን ጨምቆ የሚያቀርበው? በማኅበሩ ጉባዔዎች ጥናት የሚያቀርቡ ተጋባዦችን የሚደርቱት ወረቀት ርዕስ የኦሮሞ ምንትሴ እያለ ሐተታቸው ግን አማራን ማውገዝን ጥናታችን የሚሉት ዝብዝዝንኬ ማዕከል ማድረጋቸውን የሚያቆሙት መቼ ይሆን? መቼስ ይሆን ማኅበሩ የሚያዘጋጃቸው መድረኮች ታሪክ ተጠንቶ የሚቀርብብባቸውና በindependent reviewer ተገምግመው ያለፉ እውነተኛ የምርምር ወረቀቶች ጉባኤ የሚሆነው?