የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ነሐሴ 7 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ነሐሴ 7 ቀን 2011 ዓ.ም

የሜቴክ አዲስ ጉድ ቀጥሏል፤  ተቋሙ ያመረታቸው አስር ሺኅ ትራክተሮች፤ ፈላጊ ስላጡ በነፃ ሊታደሉ ነው

ገር ሀብትና ንብረት በማባከን የሚታወቀው የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ሰሞኑን አዲስ ጉድ ተገኝቶበታል፡፡ ዘራፊው ቡድን ከተገፋ በኋላ አዲስ የሥራ አመራር ቦርድ የተሾመለት ኮርፖሬሽኑ፣ ቀደም ሲል ያለ ገበያ ጥናት የተመረቱና ከስድስት ዓመታት በላይ በአዳማ የእርሻ መሣሪያዎች ኢንዱስትሪ  ውስጥ ተከማችተው የሚገኙ፤ ከአስር ሺኅ በላይ የሚሆኑ ትራክተሮችና መለዋወጫዎች ምንም ዓይነት ፈላጊ ማጣታቸው ይፋ ሆኗል፡፡

በሌብነት የተዘፈቀው ቡድን ሜቴክን በሚያስተዳድርበት ጊዜ፤ በጣም በወረደ ደረጃ ያመረታቸው ከአስር ሺኅ በላይ የሚሆኑት ትራክተሮች፣ ፈላጊ ስላላገኙለት ከነመለዋወጫቸው ደብቆ በማቆየት፣ በርካታ ቢሊዮን ብር ያላግባብ እንዲባክን አድርጓል፡፡ ይህን አሳፋሪና አሳዛኝ ጉድ የደረሰበት ኮርፖሬሽኑን የሚያስተዳድረው አዲስ አመራር ነው፡፡

ሃገሪቱን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለማሸጋገር፣ መደላደል እንዲሆንና የሃገር ውስጥ ኢንጂነሪንግ አቅም የመፍጠር ተልዕኮ በመንግሥት ተሰጥቶት፤ 2002 . የተቋቋመው ሜቴክ፣ በከፍተኛ ዕዳ ውስጥ ተዘፍቆ በአሁኑ ወቅት በካዝናው ውስጥ ምንም መንቀሳቀሻ የሌለው ተራ ድርጅት ሆኗል፡፡

ይህንን ተቋም ከገባበት አዘቅት ለማውጣት፤ ትራክተሮቹ ዋጋቸው ተቀንሶ ለግብርና ሚኒስቴርና ለስኳር ኮርፖሬሽን እንዲሸጡ፣ በሁለተኛ አማራጭ በከተማ ውስጥ ቆሻሻ ለማንሳት ወይም ለሌላ ተመሳሳይ ሥራ እንዲውሉ፣ በአነስተኛ ዋጋ እንዲሸጡ የታሰበ ሲሆን፤ በሦስተኛ ደረጃ ቆራርጦ በመሸጥ  የተቋሙን  ጥቅም ማስከበር ይቻላል የሚሉ ውሳኔዎች በአዲሱ አመራር በኩል ተላልፈዋል፡፡

ሦስቱም አማራጮች ካልተሳኩ፤ ለክልሎች በስጦታ መልክ ማከፋፈልና ማደል የተቋሙን ገጽታ ከመገንባት አንፃር ውጤታማ ሊያደርገው ይችላልም ተብሏል፡፡

ከስድስት ወር በላይ ተከማችተው የከረሙት እና ያለ ገበያ ጥናት ከውጭ በገፍ ገብተው የተገጣጠሙት ትራክተሮችና መለዋወጫዎች፣ ሌሎች የኢንዱስትሪ ማሽነሪዎች እና መለዋወጫዎች ወቅታዊ ግምት ዋጋቸው 13 ቢሊዮን ብር በላይ መሆኑ ታውቋል፡፡      

500 የጎዳና ተዳዳሪ ሰልጣኞች በዝቅተኛ ደሞዝ ሥራ አንቀጠርም አመፁ

የተለያዩ የለውጥ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ደፋ ቀና እያልኩ ነው በሚለው የአዲስ አበባ መስተዳድር ሠራተኞችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በመልሶ ማቋቋም የለጠኑ 500 የሚሆኑ ተማሪዎች ወደ ሥራ ለመግባት ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ሰልጣኞቹ ሥራውን ትተው በካምፕ ውስጥ ለመቀመጥ የተገደዱት የሚከፈለን ደወዝ አነስተኛ ነው በሚል መሆኑም ይፋ ሆኗል፡፡

የጎዳና ተዳዳሪዎቹ ሰልጥነው ወደ ሥራ የሚገቡ(ዝቅተኛ ነው ያሉት) ደሞወዝ 1 ሺህ 700 ብር መሆኑ ቅር አሰኝቷቸዋል፡፡ ሰልጣኝ ተማሪዎቹ ከደወዝ ባሻገር በኮካ ኮላ ፋብሪካ በኩል የሚከፈል ሰባት መቶ ብር የቤት ኪራይ ገንዘብ ለሰባት ወር አባቢ ቢዘጋጅም ቅጥሩን ለማከናወን ፈቃደኛ መሆን አልቻሉም፡፡

በከተማው መስተዳደር ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የማህበራዊ ደህንነት ልማት ማስፋፊያ ዳይሬክተር እንዳሻው አበራ እንደሚሉት ከሆነ በመልሶ ማቋቋሙ ከሰለጠኑ 966 ተማሪዎች ውስጥ 225ቱ የቀረበላቸውን አማራጭ ተቀብለው በሥራ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሠልጥነው የተለያዩ ሥራዎች ከተቀጠሩት ሰልጣኞች ውስጥም ከ1 ሺ 700 ብር እስከ 11 ሺኅ ብር ደወዝ በተለያዩ ድርጅቶች የመቀጠር እድል አግኝተዋል፡፡

አሁን በማሰልጠኛው የቀሩት ተማሪዎች የሥራ እድል እስከሚገኝላቸው ድረስ ሙሉ ወጪያቸው እየተሸፈነላቸው መሆኑን የጠቆሙት ላፊው ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰልጣኞች በዝቅተኛ ደወዝ ሥራ አንጀምርም በማለት በካምፕ የተቀመጡትና ውዝግብ እየፈጠሩ በመሆናቸው ለእነሱ ምንም የተለየ ድጋፍ አይደረግላቸውም ብለዋል፡፡

ሊቦከምከም እና ፎገራ ወረዳ  በተከሰተው ጎርፍ የሰው ሕይወት ጠፋ

በፎገራ እና ሊቦከምከም ወረዳ የርብና የጉማራ ወንዞች ሞልተው በመፍሰሳቸው በሥፍራው የሚገኙ በርካታ ቀበሌዎች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል፡፡ ይህንን ተከትሎ በሊቦከምከም ወረዳ የኹለት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ በሰብል ላይም ይህ ነው የማይባል ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል፡፡

በአደጋው ኹለቱ ሰዎች ሊሞቱ የቻሉት ከአካባቢው በዋና ለመውጣት ሲሞክሩ  ቀደም ሲል የተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ በመግባታቸው እንደሆነ ታውቋል፡፡ በዚህ የጎርፍ አደጋ ምክንያት ቢያንስ 400 የሚሆኑ ሰዎች በተዘጋጀላቸው መጠለያ ጣቢያ እንዲቀመጡ ተደርገዋል፡፡

በወረዳው የሚገኙት ጥማጋ” እካብ ቀበሌዎችም በውሃ ክፉኛ ተጥለቅልቀዋል፡፡ የጎርፍ መጥለቅለቁ  ካጋጠመ በኋላ የክልሉ መንግ ወደ ሥፍራው ጀልባ በመላኩ ሰዎች ጉዳት ያጋጥማቸው መቅረቱን ለቢቢሲ የገለፁት የወረዳው ኮሚዩኒኬሽን ሓላፊ አቶ አብራራው ምህረት፤ ቤት ንብረታቸውን ጥለው ከወጡት  መካከል መዋኘት  የሚሉት አሁንም ወደ ቀዬአቸው እሄዱ ቤታቸውን እንደሚያዩ ተናግረዋል፡፡

ከነሐሴ አንድ ጀምሮ ለረጅም ሰዓት  በሚጥለው ኃይለኛ ዝናብ የርብ ወንዝና የጉማራ ወንዝ በመሙላታቸው የጎርፍ  መጥለቅለቁ በመከሰቱ ፣ በወረዳው ባሉ 6 ቀበሌዎች የሚኖሩ ማህበረሰቦች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴያቸውን ለማድረግ ተቸግረዋል፡፡    

በታሪክ የመጀመሪያው ሃገር አቀፍ የይቅርታ፣ አንድነትና የሠላም ፌስቲቫል ይዘጋጃል

ለኹለት ቀናት የሚቆይ እና በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነ የሠላም ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው፡፡ በሃገሪቱ የታየውን ፖለቲካዊ ውጥረት ከማርገብ ባሻገር እያየነው ያለውን ደም መፋሰስና መፈናቀል ይህ የይቅርታ፣ አንድነት እና የሰላም ፌስቲቫል ለዘለቄታው መፍትሄ ሊያበጅለት ይችላል ተብሎ ተገምቷል፡፡

በሃገር አቀፍ ደረጃ ጳጉሜ 2 እና 3 ቀን 2011 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀው ፌስቲቫል ላይ የዘጠኙም ክልል ርዕሰ መስተዳደሮች እና የፌደራል ከፍተኛ መንግስት የሥራ ሓላፊዎችን ጨምሮ ጉዳዩ ይመለከታቸዋል የሚባሉ 500 ሰዎች ተሳታፊ እንደሚሆኑ የሠላም ፌስቲቫል አዘጋጅ ኮሚቴው ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሰምተናል፡፡

በሃገሪቱ ላይ ያንዣበቡትን የጥፋት አደጋዎች ለመቅረፍ ይቅርታና አንድነት ወሳኝ ነው ያለው አዘጋጅ ኮሚቴ ለሠላሙ ዕውን መሆን ምሁራን፣ የፖለቲካ ልሂቃንና የሃገር ሽማግሌዎች ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በቀድሞው የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሸመ  እንደሚመራ የተነገረለት ሃገር አቀፍ የአንድነት፣ የይቅርታ እና የሠላም ኮሚቴ በጎ ፍቃደኞችን ያሰባሰበ እንደሆነ በዛሬው ዕለት በአርቲስት አብርሃም ወልዴ እየተመራ መግለጫውን የሰጠው አሰተባባባሪ ቡድን አስታውቋል፡፡

በዚህ ታሪካዊ የይቅርታ፣ አንድነት እና የሠላም ፌስቲቫል ላይ የአምስት ሃገራት መሪዎች በተጋባዥነት ይገኛሉ፡፡ የአንድነት መንፈስና የዜግነት ፖለቲካ ተረስቶ በየክልሉ ቋንቋ እና ዘርን መሠረት ያደረጉ የከረረ የብሔርተኝነት ፖለቲካ በከፍተኛ ሁኔታ በተንሰራፋበትና ፅንፈኛ ብሔርተኞቹ ፓርቲዎች በርካታ ደጋፊ እያገኙ ባለበት በአሁኑ ወቅት የመጣውን የሠላም ግብዣ በመቀበል ለዕርቁ ተባባሪ ይሆናሉ ወይ የሚለው የአዘጋጅ ኮሚቴው ትልቅ ፈተና እንደሆነ በርካታ የፖለቲካ ተንታኞች ከወዲሁ ስጋታቸውን እየገለጹ ነው፡፡  

ገሪቱን ባንኮች የመጠቅለል ዕቅድ የያዘ የዲያስፖ ባንክ ሊቋቋም ነው

በውጭ ምንዛሬ የሚከፈል ካፒታል ያለው የአዲስ የኢንቨስትመንት ባንክ ኑሮአቸው በለንደን ባደረጉ ኢትዮጵያውን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ሊቋቋም ነው፡፡

በእንግሊዝ የአክሲዮን ገበያ እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ውስጥ የሚሰሩ የፋይናንስ ስር ባለሙያዎችን ያቀፈው አደራጅ ኮሚቴው በኢትዮጵያ ውስጥ ወኪል በማዘጋት የገያውን ሁኔታ ማስጠናት ጀምሯል፡፡

በ50 ሚሊዮን ዩሮ የተፈቀደ ካፒታል እና በ15 ሚሊዮን ዩሮ የተከፈለ ካፒታል ይቋቋማል ተብሎ የሚጠበቀው የዲያስፖራ ባንክ ቁጥራቸው ሦስት ሺህ የሚደርስ በአውሮፓ፣ በአሜሪካ፣ ካከለኛው ምስራቅና ደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ባቀፈ መልኩ ይመሰረታል፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያውን በባንክ ሥራ ላይ እንዲሰማሩ የሚፈቅደው አዋጅ በነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ እስኪወጣ በመጠባበቅ ላይ መሆናቸውን የሚናገሩት የአደራጅ ኮሚቴው አባል አቶ መክብብ ተስፋዬ በአንድ ዓመት ውስጥ ባንኩ ሙሉ ለሙሉ ተቋቁሞ ስራ እንደሚጀምር አስታውቀዋል፡፡

የዲያስፖራው ባንክ በተለመደው የንግድ ባንክ ሥራ ውስጥ ለመሰማራት ፍላጎት የለውም፡፡ አዲሱ ተቋም የኢንቨስትመንት ባንክ ሆኖ አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር በኢትዮጵያ ያሉ ባንኮችን በውጭ ካሉ የሚያገናኝ ኮርስፖንት ባንክ ለመሆን ዕቅድ ነድፏል፡፡

የብሔራዊ ባንክ አዲሱ የባንክ ሥራ አዋጅ ሲወጣ፣ የንግድ ባንክ ሥራን መሥራት በግዴታነት ካስቀመጠ እና የገያውም ፍላጎት አስገዳጅ ከሆነ የዲያስፖራው ባንክ ይህንን አሰራር ከግምት ውስጥ ሊከተው ይችላልም ተብሏል፡፡

የኢንቨስትመንት ሥራዎች እና አዳዲስ ፈጠራዎችን የሚያደግፉ ሥራዎችን መስራት፣ የቤት ብድሮችን ማበረታት ላይ የሚያተኩረው የዲያስፖራ ባንክ የረዥም ጊዜ ዕቅዱ ደግሞ የገር ውስጥ ባንኮችን መጠቅለል እንደሆነ ከአደራጅ ኮሚቴዎች በኩል ተሰምቷል፡፡

የባንኩ ሥያሜ እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮች በቅርቡ የሚወሰኑ ሲሆን ከሁለት ዓመት በፊት የገበያውን አካሄድ በመመልከት የኢንቨስትመንት ባንክ የመመስረት ሐሳብ ስለነበራቸው መስራቾቹ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን ሲያደርጉ መቆየታቸውም ነው ለማወቅ የተቻለው፡፡

በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ 17 የንግድ ባንኮች በገሪቱ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ ቀደም በዜና ዘገባችን በገለፅነው መሠረት አዲስ ይቋቋማሉ ተብለው ከሚጠበቁት እስላማዊ ባንኮች መሐል ሦስት እስላማዊ ባንኮች የአክሲዮን ሽያጭ ጀምረዋል፡፡                                        

አረጋሽ አዳነ መንግስት ከጌታቸው አሰፋ ሌላ፣ በጉያው የተሸጎጡ ወንጀለኞችን እንዲይዝ ጠየቁ

ሕወሓት ነር ታጋዮች እና ከፍተኛ ሹማምንት መል ዋነኛዋ የነበሩትና በግንባሩ መሰነጣጠቅ ስዬ አብርሃና ገበሩ አስራት የሚገኙበትን ቡድን ያስስተባ ታጋይ አረጋሽ አዳነ፣ አሁን በገሪቱ ያለውን ለውጥ አጣጥለዋል፡፡ በሕግ መጠየቅ ያለባቸው ወንጀለኞች ላይም ለየት ያለ አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡

በ1968 ዓ.ም የተማሩበትን ዲግሪና በሚሰሩበት የውጭ ድርጅት ውስጥ የሚከፈላቸውን ረብጣ ብር አሽቀንጥረው፣ “ለትግራይ ሕዝብ ነፃነት እታገላለሁ” ሲ ደደቢት በርሃ የወረዱት ታጋይ አረጋሽ አዳነ ድፍረታቸው ያመኑበትን ነገር ፊት ለፊት በመጋፈጥና ሀሳባቸውን  ያለ ስጋት የማራመድ ባህሪቸው ከወንድ ታጋዮችም በላይ እንደሆነ ይነግርላቸዋል፡፡

አስራ ሰባት ዓመቱ የጫካ ዘመን ከተጠናቀቀ በኋላ በማዕከላዊ መንግሥት ውስጥም ሆነ በሕወሓት ዘንድ ባላቸው ተሰሚነት ከአቦይ ስብሃት ነጋ ጋር ስማቸው ጎልቶ የሚጠራው አረጋሽ አዳነ በተለያዩ ጉዳዮች (በተለይም በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት) ከመለስ ጋር ፊት ለፊት የተላተሙ ደፋርና የድርጅቱ ዓይን መሆናቸውም አይዘነጋም፡፡ በሽምቅ ተዋጊው ቡድን በኩል የፈጠጠ እልህኝነታቸውና ተጋፋጭነታቸው የሚወደድላቸው ሆነ የሚፈራላቸው ተጋዳላይ አረጋሽ አዳነ ከትግል አጋሮቻቸው ጋር ጎራ ለይተው ከተፋለሙ በኋላ በሽንፈት ከሕወሓት ሰናበ ከእነ ገብሩ አስራት ጋር አረና ፓርቲን መስርተዋል፡፡

ከወራት በፊት በተከበረው የግንቦት ያ በዓል ላይ በውርደት ከድርጅቱ ከማባረር ባሻገር ለአስራ ስድስት ዓመታት ገር ውስጥ የቁም ዕሥረኛ አድርጎ ያስቀመጣቸው ሕወሓት፤ በመቀሌ ከተማ ባዘጋጀው ክብረ በዓል ላይ ከኡጋንዳ ከመጡት ስዬ አብርሃ ጋር በክብር እንግድነት ተገኝተው ያደረጉት ንግግር፣ እንዲሁም ገዳይና ዘራፊዎቹን ደብቆ ካስቀመጠው ቡድን ጋር በፍቅር “እፍ እብድ” ብለው መታየታቸው በርካታ ኢትዮጵያውያንን በእጅጉ አሳዝኖ እንደነበር ይታወሳል፡፡

ሰሞኑን ትግራይ ምንም ዓይነት ለውጥ የለም ከጊዜ ወደ ጊዜ በከፍተኛ ደረጃ ሕዝብ ላይ የሚደረገው ተፅዕኖ እየጨመረ መጥቷል ሲሉ ተደምጠዋል ነባሯ ታጋይ፡፡ “በእኔ እምነት ከመጀመሪያውም ለውጡ በትክክለኛ መንገድ የመጣ አይደለም፡፡” በማለት በገሪቱ የሚታየውን አዲስ የፖለቲካ መስመር ያጣጣሉት በትግራይ መቀሌ ከተማ ተወልደው ያደጉት የሕወሓት መስራች ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መጀመሪያ ላይ ፓርላማ ቀርበው ባደረጉት ሕዝብ ተስፋ አድርጎ የነበረ ቢሆንም  በሂደት ግን ፖለቲካው እየተበላሸ መጥቷል ሲሉ ስርዓቱን ተችተዋል፡

በዜጎች  ላይ ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አድርሰው፤ የገር ሀብትና ንብረት ዘርፈው የተሸሸጉ ሰዎችን በተመለከተ “ወንጀል ሰርተው የተሸሸጉት ብቻ ሳይሆን ያልተሸሸጉትም መጠየቅ አለባቸው” በማለት የገለፁት ታጋይ አረጋሽ አዳነ“በሕዝብ ተዓማኒነት እንዲኖር ከተፈለገ ትግራይ የተሸሸጉት ብቻ ሳይሆኑ ከመንግስት ጋር እየኖሩና እየሠሩ ሉትም በተመሳሳይ መንገድ የሰረቁ፣ በተመሰሳይ መንገድ ያጠፉ አሉ፡፡ ስለዚህ ይሄ ጥያቄ የጌታቸው አሰፋና እና ሌሎች እስር ቤት ያሉ አመራሮች ብቻ መሆን የለበትም” ሲሉ ለቀድሞ አጋሮቻቸው ተቆርቋሪነታቸውን ያሳየ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር በተጠቃሚዎች ቅሬታ ቀረበበት

የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ተገቢውን መረጃ በመስጠት በኩል ችግሮች እንዳሉበት ተነገረ፡፡ የኢትዮ ጅቡቲ ምድር ባቡር ትራንስፖት አክሲዮን ማህበር በበኩሉ ተሳፋዎቼን መረጃ የመከልከል ፍላጎት የለኝም ብሏል፡፡

የባቡር ተጠቃሚ የሆኑ በርካታ ሰዎች ችግር ተፈጥሮ ሲቆሙ፣ አንዳንዴም ወደመጡበት በሚመለሱበት ወቅት ስለተፈጠረው ሁኔታ መረጃ የሚሰጣቸው አካል እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ የባቡሩ ፍጥነት አቅም መገደብን በተመለከተ፣ ቀደም ሲል ከአዲስ አበባ ድሬድዋ በአራት ሰዓት ይደረሳል የተባለው የባቡር ጉዞ አስር ሰዓት እየወሰደ መሆኑን በመጠቆም ቅሬታቸውን የሚያቀርቡ አሉ፡፡ ሻንጣ የሚጭንና የሚያወርድ ሠራተኛ አለመኖርም ሌላኛው ችግር ሆኖ ተጠቅሷል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ቦርደዴ በሚባለው አካባቢ በፀጥታ ችግር ምክንት የባቡር ሀዲድ በድንጋይ በመዘጋቱ ሰሞኑን ባቡር አገልግሎት የተባለው ችግር መከሰቱን ያመኑት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ጥላሁን ሳርካን “የመረጃ እጥረት ስለሚገጥመን እንጂ ተሳፋሪዎቻችን መረጃ ለመከልከል ብለን ያደረግነው ነገር የለም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በውስጣዊ ችግር ምክንያት አንድም ባቡር ቆሞ እንደሚያውቅ የተናገሩት ዋና ዳይሬከተር ችግሮቹ የሚከሰቱት በሃይል መቆራረጥና በፀጥታ ችግር ብቻ እንደሆነ አረጋግጠው በየትውም ዓለም ላይ ባቡር አገልግሎት የሻንጣ ጫኝና አውራጅ ስለሌለ እኛም በዚህ ዘርፍ የሚሰሩ ተቀጣሪ ራተኞች የንም ብለዋል

LEAVE A REPLY