የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ነሐሴ 9 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ነሐሴ 9 ቀን 2011 ዓ.ም

የወሲብ ንግድና ልመናን የሚቀርፉ ረቂቅ ህጎች ተቃውሞ ገጠማቸው

የአዲስ አበባ አስተዳደር የጎዳና ልመናና የወሲብ ንግድን ለማገድ ያዘጋጀው ረቂቅ ሕግ ከወዲሁ በበርካታ ሕዝብ ዘንድጥያቄ እያስነሳ ይገኛል፡፡

ረቂቅ ህጉ በአሁኑ ወቅት ለካቢኔ ቀርቦ ውይይት እየተካሄደበት ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሩ ብቻውን መወሰን ስለማይችል ጉዳዩ የሚመለከታቸ አካላት የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች እና የዕምነት ተቋማት መሪዎች አስተያየት እየሰጡበት ናቸው ተብሏል፡፡

የመስተዳድሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ ፌቨን ተሾመ በረቂቅ ህጉ ላይ ከህረተሰቡ ጋር መተማመን ላይ ከተረሰ በኋላ የጎዳና ልመናን ለማስቀረትና አምራች ኃይሉ ከዚህ ሕይወት ለማውጣት ትኩረት ተሰጥቶ ለመስራት ወደ ምክር ቤት ይመራል ብለዋል፡፡

ልመና እንደባህል እየተወሰደ ስለሆነ በሕግ ካልተከለከለ አስቸጋሪ መሆኑ አያጠያይቅም የሚሉት ፕሬስ ሴክረተሪዋ ዕርምጃው ነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ከማፍራት አኳያ ትልቅሚና እንዳለውም አረጋግጠዋል፡፡ አዲስ አበባ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ ለሀገር ፀጥታም ማሰብ ተገቢም እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የወሲብ ንግድ ኢትዮጵያዊ እሴት ስላልሆነ ዋና ከተማዋን ዚህ ዓይነቱ የረከሰ ተግባር ለማፅዳት ታስቦ በተያያዥነት እየተሰራ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ከጊዜ ወደ ጊዜ በከተማዋ እያደገ የመጣውን የኤች.አይ.ቪ ስርጭትን በማባባሱ በኩል የወሲብ ንግድ መበራከት ከፍተኛ ድርሻ ያለው መሆኑ በጥናት በመረጋገጡ ይህንን ለመቆጣጠር ከወሲብ ነጋዴዎች እስከ ተገልጋዩ ድረስ የሚወርዱ ቅጣቶች ሕግ መረቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ አዲስ አበባ በኤች አይስርጭት ከሀገሪቱ ከተሞች በ2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

በተለይም ከወሲብ ንግድ ጋር በተያያዘ የሚወጣው ህግ የሰዎችን የመዝናናት እና የመደሰት መብት በግልጽ መጋፋት ነው የሚሉ ውስጣዊ ቅሬታዎች ሰሞኑን በስፋት እየተደመጡ ናቸው፡፡ መንግስት የጎዳና የወሲብ ንግድን በሚያካሂዱ ላይ ጠንከር ያለ ዕርምጃ እንደሚወስድ ገልጾ ይህንን ከማድረጉ በፊት ግን ሕይወታቸውን  በዚህ መልክ ለሚመሩ ሴቶች በቂ ስልጠና እና የሥራ እድል እንደ ሚያመቻች አስታውቋል፡፡ አዲሱ የወሲብ ንግድ ህግ ተግባራዊ ከሆነ በመንገድ ላይ አንዲት ሴትን ለወሲባዊ ጉዳይ የሚያነጋግር ወይም የሚደራደር ወንድ አንድ ሺኅ ብር ይቀጣል፡፡

የትግራይ ክልል የማትሪክ ፈተናው በአንድ ክልልተሰርቋል ሲል ውጤቱን አጣጣለ

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤትን በተመለከተ በሕወሓት የምትተዳደረው የትግራይ ትምህርት ቢሮ ቅሬታ እንዳለው ገለፀ፡፡ በትግራይ ክልል ፈተናው የተካሄደው የፈተና አወሳሰድ ስነምግባርን በጠበቀ መልኩ ቢሆንም በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ግን ስርዓቱን የጠበቀ አልነበረም ያሉት የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኢንጂነር ገብረመስቀል ካህሳይበተለይ በአንድ ክልል ከኩረጃ የፀዳ ስላልነበር ፈተናው እንዳለቀ ማጣራት እንዲካሄድ ጥያቄ አቅርበን የተሰጠን ምላሽ እናየዋለን የሚል ነበርሲሉ ለቢቢሲ ክሳቸውን አሰምተዋል፡፡

ላፊው በተጨማሪም ከትግራይ ክልል እና ከአንዳንድ አካባቢዎች የተነሳው ቅሬታ ምላሽ ሳያገኝ ውጤቱ ይፋ በመሆኑ ቅሬታ እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡ የትግራይ ትምህርት ቢሮ ሓላፊበተለይ አንድ ክልልያሉትን ሥፍራ በሥም ባይጠቅሱትም ዘንድሮ ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቦበታል ተብሎ የተመሰከረለት የአማራ ክልልን መሆኑ ተገምቷል፡፡  

ጉዳዩ የሚመለከተው የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እቶ አርአያ ገብረእግዚአብሔር ግን ከፈተና አሰጣጥ ጋር በተያያዘ በፈተናው ወቅትም ሆነ ከዛ በኋላ ባሉት ቀናት ለኤጀንሲያቸው የቀረበ ሬታ እንዳልነበር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ሆን ተብሎ የተማሪን ውጤት መቀየር አይቻልምተማሪዎች ያጠቆሩትን ወረቀት ነው ማሽን የሚያነበው ያሉት ላፊ ዘንድሮ የተሰጠው ፈተና ጥብቅ በሆነ ክትትል እንደተከናወነ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል፡፡ አሁን ላይ የቀረበውን ቅሬታ መነሻ በማድረ አስፈላጊው ማጣራት ተከናውኖ ከአምስት እስከ አስር ቀናት ባሉት ጊዜያት ውስጥ ምላሽ እንደሚሰጥ ተገል፡፡

በሆሮ ጉድሩ ወለጋ ተፈናቃይ 10 ህፃናት በምግብ እጥረት ሞቱ

በሆሮ ጉዱሩ ወለጋሀሙሩ ጉዩ ቴቦተብሎ በሚጠራው ቀበሌ ሠፈሩ ተፈናቃዮች መሀል አስር ሕፃናት በቂ ምግብ ባለማግኘታቸው ለሞት እንደተዳረጉ ታወቀ፡፡

በመጠለያው ያሉ ሕፃናት ስት ወራት ያህል የእህል ድጋፍ ተቋርጦባቸዋል፡፡ የወረዳውና የዞኑ አደጋ ሥጋት አመራርጽ/ቤት ሐላፊዎች ግን ድጋፉ የተቋረጠው ለሁለት ወራት ብቻነው ውንጀላውን በአንድ ወር ቀንሰዋል፡፡

የሕፃናቱ በምግብ እጥረት መሞትን ያልካደው የክልሉ አደጋ ሥጋት አመራር ኮሚሽን ለተፈናቃዮች የሚቀርበው የምግብ ድጋፍ የዘገየው እህል ለማድ በዝናብ ምክንያት መንገዱ መኪና ሊያስገባ ባለመቻሉ እንደሆነ አስታውሷል፡፡

አሁንም ያለው የዝናብ እና የጭቃ ሁኔታ ዕርዳታውን ለማድረስ አመቺ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ ለተረጂዎቹ ገንዘብ በመስጠት ያለባቸውን ችግር በመገበያየት ለጊዜውም ቢሆን እንዲቀርፉ ለማድረግ እንደታሰበ ሰምተናል፡፡              

ለቀጣዮ ምርጫ ጃፓን የ3 ሚሊየን ዶላር ዕርዳታ ሰጠች

ጃፓን ኢትዮጵያ ቀጣይ ለምታካሄደው ምርጫ የ3 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንዳደረገች ተሰማ።

በአዲስ መልክ የተዋቀረው የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የድጋፍ ስምምነቱ በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ዳይሱኬ ማጹናጋ እና በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ተወካይ ቱራሃን ሳለህ በኩል ሲፈጸም በቦተው ተገኝተዋል።

ኢትዮጵያ በቀጣይ ለምታካሂደው ምርጫ ደረጃቸውን የጠበቁ የምርጫ ኮሮጆዎችን ለማቅረብ እና በምርጫ ሂደቱ በቀላሉ የማይለቁ ቀለሞችን ለማሟላት ታስቦ የተደረገ ድጋፍ መሆኑም ታውቋል።

የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የምርጫ ግብአቶች ለማሟላት እየተሰራ ያለው ስራ ምርጫ ቦርዱ ፍትሃዊ፣ ግልጽና ታአማኒ ምርጫ ለማካሄድ ሂደት ላይ መሆኑን አንዱ ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የተከናወኑት ምርጫዎች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የምርጫ ግብዓቶችን እንዳልተጠቀመች ያስታወሱት ሰብሳቢዋ፥ ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ጥርጣሬዎች እና ትችቶች ሲቀርቡ በመቆየታቸው ይህ ሁኔታ ዳግም እንዳይከሰት እንዲህ አይነት ድጋፎች ጠቀሜታቸው የጎላ ነው ብለዋል።

በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ዳይሱኬ ማጹናጋ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በቀጣይ የምታካሂደው ምርጫ የዜጎችን ህይወት የሚያሻሽል ይሆናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።

ጥቁር ዓባይ ጫማ ፋብሪካ በመንግስት ትዕዛዝ ተዘጋ

ላለፉት 25 ዓመታት ጫማ እና ሌሎች የቆዳ ውጤቶችን በማምረት በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ የሚታወቀው ጥቁር ዓባ ፋብሪካ በመንግሥት ትዕዛዝ እንዲዘጋ መደረጉ ተረጋገጠ፡፡

ከፋብሪካው የሚወጣ በካይ ፈሳሽ እና ተረፈ ምርት ፋብሪካው በሚገኝበት አካባቢ ነዋሪ በሆኑ ዜጎች ላይ ከፍተኛ የጤና ችግር አስከትሏል በሚል እንዲዘጋ የተደረገው ጥቁር ዓባይ ጫማ ፋብሪካ ከአካባቢው አርብቶ አደሮች የቆዳ ውጤቶችን በመቀበል በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ የጫማ እና ሌሎች የቆዳ ምርቶችን እያቀነባበረ ወደ ጣሊያን እና የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ሲልክ ቆይቷል፡፡

በዚህም ሀገሪቱ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ እንድታገኝበዘርፉ የቴክኖሎጂ ሽግግር ዕውን እንዲሆን ከማስቻሉም በላይ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል እንዲፈጠር ማድረጉ በሰፊው ይነገርለታል፡፡

በደብረብርሃን ከተማ ቀበሌ 07 ውስጥ ተገንብቶ ለ25 ዓመታት በምርት ላይ የቆየው ጥቁር ዓባይ ፋብሪካ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ የጤና ችግር ፍጠ በመረጋገጡ እንዲዘጋ ትዕዛዝ የተላለፈው ከከተማው ጤና ቢሮ ነው፡፡ ዕድሜ ጠገቡ ፋብሪካ እንዲዘጋ ውሳኔ ከመሰጠቱ በፊት ችግሩን ለመቅረፍ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም እንዲያስወግድ ተነግሮት ነበር ተብሏል፡፡

እንደ ምንጮቻችን ገለጻ ከሆነ በፋብሪካው አካባቢ የሚኖሩ ጥቂት የማይባሉ ዜጎች ከፋብሪካው በሚወጣ በካይ ፈሳሽ እና አደገኛ ሽታ ሳቢያ ለከፋ የጤና ችግር ተጋልጠው በደብረብርሃን ሪፈራል ሆስፒታል እና በአዲስ አበባ ልዩ ልዩ ሆስፒታሎች ህክምና ማድረጋቸው በማስረጃ ተረጋግጧል፡፡ ብዙዎቹ ታማሚዎች  የበሽታቸው ምክንያት ምን እንደሆነ በመታወቁበህክምና ባለሙያዎች የመኖሪያ አካባቢያቸውን እንዲቀይሩ ትዕዛዝ የተሰጣቸው መሆኑ ለመረዳት ችለናል፡፡

ይሁንና የፋብሪካው የምርት ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ኤርሚያስ ወሰኑ ስለ ጉዳዩ ተጠይቀው በሰጡት አስተያየትኅብረተሰቡ ያነሳው ጥያቄ እና ደረሰ የተባለው የጤና ችግር የሚያስተባብሉት ባይሆንም ፋብሪካው ዘመናዊ ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ችግሩን ለመቅረፍ አቅም ስላለው የተላለፈው ፋብሪካውን የመዝጋት ውሳኔ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል፡፡

የአማራ ልማት ማህበር 21 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ዕቅድ ይዟል

የአማራ አቀፍ ልማት ማኅበር (አልማ) በአማራ ክልል የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን ደረጃ ለማሻሻል የሚያስችለውን የለውጥ ዕቅድ አልማ (የአማራ አቀፍ ልማት ማህበር)  ለክልሉ ትምህርት ቢሮና ለአጋር አካላት አቅርቧል።

የልማት ማህበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታ ማኅበሩ ደረጃቸውን የጠበቁ የትምህርት ተቋማት ለትምህርት ጥራት የሚኖራቸውን ፋይዳ በመረዳቱ ከመቼውም ጊዜ በላቀ መልኩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሆነ ተናግረዋል።

ይህንን ዕቅዱን ለማሳካት ከ2012 እስከ 2014 ዓ,ም ባሉት ሦስት ዓመታት 21 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ከአባላቱ በመሰብሰብ ለታሰበው የትምህርት ቤቶች ግንባታ ለማዋል ቁርጠኛ መሆኑንም ይፋ አድርጓል።

በክልሉ  የተለያዮ ከተሞች አዳዲስ ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡ እና ነባሮቹም የማደስ ሥራ ይከናወንላቸዋል ያሉት የአልማ ሓላፊ በሁሉም ዞኖች አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለመስራት መታቀዱን ጠቅሰው ይህም አሁን በክልሉ ያለውንና 16 በመቶ የሆነውን ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶች ሽፋን ወደ 50 በመቶ ሊያሳግደው እንደሚችል አብራርተዋል።

ገንዘቡ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ከሚገኙ አባላት፣ ከመንግሥትና ከሚመለከታቸው አካላት የሚሰበሰብ ሲሆን ከፊታችን ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር እንደሚጀምርም ታውቋል።

LEAVE A REPLY