በጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን 105 ዕስረኞችን አስፈትተው አዲስ አበባ ገቡ

በጠ/ሚ/ር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳን 105 ዕስረኞችን አስፈትተው አዲስ አበባ ገቡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በተጓዙባቸው ሀገራት በዕስር ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን በማስፈታቱ ረገድ የተሳካላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይአህመድ በሱዳን ሌላ ታሪክ ጽፈዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሱዳን ዕስር ላይ የነበሩ 105 ኢትዮጰያውያንን በመያዝ አዲስ አበባ ገብተዋል::

እነዚህ ተፈቺዎች ኢትዮጵያውያን በህገወጥ መንገድ ሱዳንን እንደመተላለፊያ በመጠቀም ወደ አውሮፓና መካከለኛው ምስራቅ ለመግባት ሲሞክሩ በሱዳን የፀጥታ ሃይሎች የተያዙ ናቸው::

ስደተኞቹ በሱዳን ዕስር ቤት የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ከተለቀቁ በኋላ እዛው በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምበሲ ተጠልለው የቆዩ መሆናቸው ተሰምቷል:: ኢትዮጵያውያኑ ከእስር የተለቀቁት ዜጋን ያስቀደመ ዲፕሎማሲ በመከተል መሆኑም ተነግሯል፡፡

የሱዳን ተቃዋሚዎችና ወታደራዊ ሃይል በመሰረቱት የሽግግር መንግስት ዙሪያ የመጨረሻ የስምምነት ፊርማ ስነ ስርዓትን ዕውን ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደሀገር ቤት ሲመለሱ ነው ኢትዮጵያዊያኑን ይዘው አዲስ አበባ የገቡት፡፡ ከዕስር ተፈተው አዲስ አበባ ከገቡት መካከል አብዛኞቹ ሴቶች  ናቸው፡፡

የሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች ሉዓላዊ ምክር ቤት መመስረት መቻላቸውን ተከትሎ በርካታ ሱዳናውያን ለዋና አደራዳሪውለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ያላቸውን ፍቅር እና አድናቆት እየገለፁ ነው::

LEAVE A REPLY