ውዝግብ ውስጥ የቆዮት አማራ እና ቤኒሻንጉል ክልሎች የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ

ውዝግብ ውስጥ የቆዮት አማራ እና ቤኒሻንጉል ክልሎች የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአማራ እና የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የልማትና የሰላም ስምምነት መፈራረማቸው ተነገረ።

የክልሎች ርዕሰ መሥተዳድሮች እና የልዑክ አባላት ለሁለት ቀናት በአሶሳ ከተማ በጋራ ሰላምና ልማት ላይ ሲያደርጉት የነበረው ውይይት ዛሬ ሲቋጭ ኹለቱ ክልሎች የልማትና የሰላም ስምምነት ፊርማ ተፈራርመዋል።

የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ትናንት ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብን ከመጎብኘታቸው ባሻገር አሶሳ ከተማ ከሚገኙ የአማራ ክልል ተወላጆች ጋር ምክክር አድርገዋል።  በስብሰባው ትኩረት የሚሹ የፖለቲካ፣ የልማትና የሰላም ጥያቄዎች ቀርበው ጥልቅ ውይይት ተደርጎባቸዋል።

ዛሬ በአስተዳደር ወሰን አካባቢዎች የሚኖሩ ሕዝቦች በሰላም እንዲኖሩ የተለያዩ ስራዎች ቢከናወኑም በነበረው የጸጥታ ችግር መፈናቀል፣ ሞትና የንብረት ውድመት ስለ መከሰቱ የተወያየው ጉባዔ የጸጥታ ችግሮችን አስቀድሞ መለየትና መከላከል ባለመቻሉ ችግሮች ስለ መፈጠራቸውም ተነጋግሯል።

የኹለቱ ክልሎች የሥራ ኃላፊዎች ችግሮቹን ለማስተካከል ያከናወኗቸው ተግባራት በጥንካሬ የተነሱ ሲሆን፥ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ለማጠናከር ውይይቶች ሲደረጉ በግጭቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ የተጀመሩ ጥረቶችን አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም ውሳኔ ተላልፏል።

LEAVE A REPLY