የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ነሐሴ 14 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || ነሐሴ 14 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ሀብታቸውን ለማስመዝገብ ፍቃደኛ አይደሉም ተባለ

የአገሪቱ ባለሥልጣናት ሀብታቸውን ለማስመዝገብ ፍቃደ አለመሆናቸው፣ ለሥራው ከባድ ዕንቅፋት እንደሆነበት የስነ ምግባር እና ጸረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የያዝነውን በጀት መት አፈጻጸም እና የ2012 ዓ.ም ዕቅዱን ዛሬ ባዘጋጀው የውይይት  መድረክ ላይ ሲያስተዋውቅ ነው የጸረ ሙስና ኮሚሽን ይህንን ያጋለጠው፡፡ በውይይቱ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት መ/ቤቱ ሀብት ማስመዝገብ ላይ ያለው አፈጻጸም ደካማ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

ሀብት ምዝገባን በተመለከተ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት ፍቃደኛ ካለመሆናቸው ጋር ተያይዞ ችግሩ ሊከሰት እንደቻለ እና የሀብት ምዝገባ ሥራው ፈታኝ እንዲሆን አድርጓል ተብሏል፡፡

አሁን በአዲስ መልክ በመዘጋጀት ላይ ካለው ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት የስነ ምግባር ደንብ በተጨማሪ በሀብት ማሳወቅ እና ማስመዝገቢያ፤ እንዲሁም የስነ ምግባር መኮንኖች አሠራርን ለመወሰን በወጣው ህገ ደንብ ላይ ረቂቅ ማሻሻያዎች መቀረፃቸውን ከደረሰን ዜና መረዳት ተችሏል፡፡    

ኢትዮጵያ 1.5 ትሪሊየን ብር ዕዳ ውስጥ ተዘፍቃለች

ዓለም ባንክ ጨምሮ ከተለያዩ ገራት እና ከገር ውስጥ ከፍተኛ ገንዘብ በመበደር የሚታወቀው የኢሕአዴግ መንግስት ሊገፋ የማይችል ዕዳ ውስጥ ዘፍቋታል፡፡

ኢትዮጵያ እስከ (እ.ኤ.አ) ርች 2019 ድረስ ያልተከፈለ የገር ውስጥና የውጭ  1.5 ትሪሊዮን ብር ወይም 52.57 ቢሊዮን ዶላር ዕዳ አለባት፡፡ ከዚህ አጠቃላይ ዕዳ 26.93 ቢሊዮን ዶላር ወይም 769.08 ብር ከተለያዩ የውጭ አበዳሪዎች ተወስዶ ያልተከፈለ ነው፡፡ ቀሪው 730.5 ቢሊዮን ብር ደግሞ ከአገር ውስጥ የመንግሥት ባንኮች የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከልማት ባንክ  ከልማት ባንክና ከብሔራዊ ባንክ በብድር የተገኘ ነው፡፡ ከመንግስት ሰራተኞች የማህበራዊ ዋስትና ወይም ጡረታ ፈንዶች ተወስዶ ያልተከፈለ ዕዳም በዚህ የገር ውስጥ ብድር ላይ እንደሚካተት ሪፖርተር ጋዜጣ ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘውን ሰነድ መሠረት አድርጎ ዘግቧል፡፡

      የተለያዩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች መንግሥት በገባላቸው የብድር መክፈያ መተማመኛ (loan guarantee)፣ ሌሎች ለት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ደግሞ ያለ መንግሥት የብድር መክፈያ መተማመኛ በራሳቸው ከውጭ አበዳሪዎች ተበድረው ያልከፈሉት 319.3 ቢሊዮን ብር ወይም 11.17 ቢሊዮን ዶላር መኖሩ ያጋለጠው የገንዘብ ሚኒስቴር ሰነድ ነው፡፡ ያለመንግሥት የብድር መክፈያ መተማመኛ ከውጭ ገንዘብ የተበደሩት ግዙፎቹ የልማት ድርጅቶች አየር መንገድ እና ኢትዮ ቴሌኮም መሆናቸውንም አጋልጧል፡፡ ድርጅቶቹ እስከ ርች 2019 ድረስ ያልከፈሉት ዕዳ 116.96 ቢሊዮን ብር ወይንም 3.9 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡

    የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን፣ የኢትዮጵያ ኤሌትሪክ አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ገንዘብ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተገባላቸው የብድር መክፈያ መተማመኛ ገንዘብ የተበደሩ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ናቸው፡፡ እነዚህም ተቋሞች እስከ ማርች 2019 ድረስ አገሪቱ ያለባትን አጠቃላይ የውጭ ብድር የሚያመለክት ሲሆን፤ በዚህም መሠረት አጠቃላይ የአገሪቱ ዕዳ 730.5 ቢሊዮን ብር መድረሱን መግለጫው አረጋግጧል፡፡

የአገር ውስጥ ብድር ዕዳ የሚመለከተው ማዕከላዊ መንግሥትንና የመንግስት የልማት ድርጅቶችን እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡ በዚህም መሠረት የማዕከላዊ መንግሥት የአገር ውስጥ ዕዳ 343.5 ቢሊዮን ብር ሲሆን የመንግስት ልማት ድርጅቶች ዕዳ ደግሞ 386 ቢሊዮን ብር ዕዳ አለባቸው፡፡

8 ወር ያልተሰበሰበው የደቡብ ክልል ም/ቤት የ2012 ዓ.ም በጀትን ማፅደቅ አልቻለም

የደቡብ ክልል የ2012 ዓ.ም በጀት ባለማፅደቁ በ2011 ዓ.ም በጀት ዓመት ላይ በመመስረት የአንድ ወር በጀት ብቻ ታስቦ ተለቆለታል፡፡ ውሳኔው የዋጋ ግሽበትን ያላማከለ ከመሆኑ ባሻገር የዞን አመራሮችን ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደከተተም በስፋት እየተወራ ነው፡፡

የደቡብ ብብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት ላለፉት  ስምንት ወራት ስብሰባ ባለማድረጉ ነው የቀጣይ ዓመትን በጀት ማፅደቅ ያልቻለው፡፡ የክልሉ መንግሥት ዋና መቀመጫ በሆነችው ሃዋሳ ከወራት በፊት የተደራጁ ወጣቶች ከሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ የምክር ቤቱን ስብሰባ በኃይል በመበተናቸው ምክር ቤቱ ያቋረጠውን እና አስቸኳይ ስብሰባውን በአዲስ አበባ ለማካሄድ መገደዱ አይዘነጋም፡፡

በአሁኑ ወቅት የክልሉ የ2012 ዓ.ም በጀት ባለመፅደቁ ከፍተኛ ውዝግብ ተከስቷል፡፡ አስር ዞኖች “ክልል እንሁን” የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን ተከትሎ፤ እንዲሁም ራሱን የሲዳማ ነፃ አውጪ አድርጎ የተመለከተው “ዕብሪተኛው” ኢጄቶ ቀሰቀሰው አመፅ እና በደረሰው ከባድ ጉዳት  ጭንቀት ውስጥ የከረመው ደ....ን አሁንም በችግር ተወጥሯል፡፡

በጊዜያዊነት የተለቀቀው አንድ አስራ ሁለተኛ በጀት፣ ያለፈው ዓመት ቀመር ላይ በመመስረቱ መደበኛ ሥራዎችን ለማከናወንም ሆነ ለአስቸኳይ ወጪዎች በቂ አይደለም እየተባለ ነው፡፡ ይሁንና የመንግሥት ሠራተኞችን ደምወዝ ለመክፈል፣መደበኛ ሥራዎችን እና አስቸኳይ ሥራዎችን ለማከናወን፤ በታሳቢነት የተለቀቀው በጀት በቂ መሆኑን የክልሉ ፕሬስ ሴክረተሪያት ሓላፊ ፍቅሬ አማን ይናገራሉ፡፡ በተያያዥነት ክልሉ የገቢ ግብር የማሰባሰብ ሥራውን እያካሄደ በመሆኑ የገንዘብ እጥረት እንደማያጋጥምም ገልጸዋል፡፡

የደቡብ ክልል በ2011 ዓ.ም 37.9 ቢሊዮን ብር ነበር በጀቱ፡፡ ይህም ኦሮሚያ ክልል በያዝነው በጀት ዓመት ካፀደቀው በጀት ግማሽ ሲሆን፣ የትግራይ ክልል ካፀደቀው በጀት ደግሞ በዕጥፍ ይበልጣል፡፡ የደቡብ ክልል ከኢትዮጵያ ህዝብ ሃያ በመቶ የሚሆነውን በመያዝ በህዝብ ብዛት ከኦሮሚያ እና ከአማራ ክልል ቀጥሎ  በሦስተኛነት ተቀምጧል፡፡                

አዳማ ከተማ ኹለተኛው የኢንዱስትሪ ፓርክበ300 ሚሊዮን ዶላር  ገነባ ነው

          በአዳማ ከተማ ለኹለተኛ ጊዜ በ300 ሚሊዮን ዶላር የኢንዱስት ፓርክ ሊገነባ በዝግጅት ላይ መሆ ወቀ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ዋና ከተማ በአንድ መቶ ሺህ ሄክታር መሬት ላይ እንደሚገነባ የተነገረለት የኢንዱስትሪ መንደር የግንባታ ወጪ 15 በመቶውን የኢትዮጵያ መንግሥት ቀሪው 85 በመቶ ከቻይና መንግሥት ጋር በተደረሰ የዝቅተኛ ወለድ ስምምነት በሚገኝ የብድር ገንዘብ ይሸፈናል፡፡

በአዳማ የሚቋቋመውን የኢንዱስትሪ መንደር ግንባታ የቻይናው ሲቪል ምህንድስና ኮንስትራክሽን ኮርሬሽን (ሲሲሲ) ያከናውነዋል፡፡ ኮንስትራክሽን ድርጅቱ ቀደም ሲል በ146 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርክንእንደገነባ ይታወሳል፡፡

በከተማዋ ለኹለተኛ ጊዜ የሚገነባው የኢንዱስትሪ ፓርክ ሲጠናቀቅ ለ2.600 ዜጎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡

                 

ቃና ቴሌቪዥን ከዓመታዊ ገቢው አምስት በመቶውን ተቀጣ

ቃና ቴሌቪዥን አሳሳች የጥርስ ሳሙና ማስታወቂያ አስተላልፏል በሚል ከዓመታዊ ገቢው ላይ አምስት በመቶውን እንዲከፍል ቅጣት እንደተጣለበት ተሰማ፡፡

ሌሎች የጥርስ ሳሙናዎች በቂ አይደሉም፤ ለዚህም ነው ምርጫዬ ዳቢር ኸርባል የሆነው በሚል አረፍተ ነገር እናት እና ልጅ የሚነጋገሩበት ማስታወቂያ በጥናት ያልተረጋገጠ በሌሎች ተወዳዳሪዎችም ፍትሃዊ ያልሆነ ነው በማለት የብሮድካስት ባለስልጣን አቤቱታ ደብዳቤ ማስገባቱን ተከትሎ በንግድ ውድድር የሸማቾች ጥበቃ ባለስልጣን ዐቃ ህጎች በቴሌቪዥን ጣቢያው ላይ ክስ መሥርተው ነበር፡፡

የዳበር ኸርባል” የጥርስ ሳሙና አስመጪ ድርጅት ባለቤት አብዱራቅ ታከለም ፍትሃዊ ያልሆነ ማስታወቂያ  አርተዋል በሚል በተመሳሳይ ሁኔታ ከዓመታዊ ገቢያቸው ላይ የአምስት በመቶ ቅጣት ተጥሎባቸዋል፡፡

አወዛጋቢው ማስታወቂያ ያዘጋቢ ሚዲያ እና የማስታወቂያ ድርጅት ከዓመታዊ ገቢው ላይ የአምስት በመቶ ቅጣት እንደተጣለበት ከባለስልጣኑ ከወጣው መረጃ ለማወቅ ችለናል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ብዙ ተመልካች በኢትዮጵያ ያገኘው የቃና ቴሌቪዥን ለንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ይግባኝ ሰሚ ችሎት ቅሬታውን አሰምቶ ውሳኔውን እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡

አራት ቢሊዮን ብር 5 ኤርፖርቶችና 6 ተርሚናሎች ይገነባሉ

በአራት ቢሊዮን ብር ወጪ አምስት አውሮፕላን ማረፊያ እና ስድስት ተርሚናሎች ሊገነቡ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ፡፡

ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን እና የህዝቦች ግንኙነትን መሠረት በማድረግ በደብረማርቆስ ሚዛን አማን፣ ሬ መቱ፣ በነገሌ እና ያቤሎ ከተሞች የአውሮፕላን ማኮብኮቢያ እና ማረፊያ ግንባታ ይካሄዳል፡፡ ከሚገነቡት ሥፍራዎች መሐል ቀደም ሲል ጥቂት ሰዎችን ብቻ የሚያጓዙ አውሮፕላኖችን በማስተናገድ ይሰሩ የነበሩ እና አገልግሎት ያቋረጡ ይገኙበታል ተብሏል፡፡

በሌላ በኩል በሽሬ፣ ደሴ፣ ኮምቦልቻ ደምቢዶሎ፣ ጂንካ እና ጅማ ከተሞች ላይ የመንገደኞች ማስተናገጃ ጣቢያዎች ወይም ተርሚናሎች ይገነባሉ፡፡ ደንቢዶሎ ከተማ የሚገነባው የአውሮፕላን ማረፊያ ሙሉ ለሙሉ ባይጠናቀቅም የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛል፡፡ በነቀምቴ የተጀመረው ተርሚናል ግንባታ የሚቀጥል ሲሆን የመቐለ፣ ባህርዳር እና ድሬድዋ ኤርፖርቶች የማሻሻል ሥራም የአየር መንገዱ ዕቅዶች ናቸው፡፡

የሼክ አላሙዲ ንብረት የሆነው ሳውዲ ስታር ምርቱ አርባ በመቶ ወረደ

የሳውዲ ስታር ሰፋፊ የአርሻ ፐሮጀክት፣ 2011 . ምርትካለፈው ዓመት ሲነፃፀር፤ 40 በመቶ ቅናሽ አሳየ፡፡ ኩባንያው ምርቱ በብዛት ቢቀንስም፣ የበቆሎና የጥጥ ምርቱ ግን በከፍተኛ ደረጃ እንዳሽቆለቀለ ነው የተነገረው፡፡

የሼክ መሐመድ ሁሴን አሊ አልአሙዲን ንብረት የሆነው የሳውዲ ስታር ሥራ አስኪያጅ በድሉ አበራ፤ የግብዓት ግዢ በመዘግየቱ፣ የመስኖ ሥራውም በተያዘው ዕቅድ መሰረት ሊካሄድ ባለመቻሉ ምርቱ እንዳሽቆለቆለ ገልጸዋል፡፡

የእርሻ ማሳው የሚገኝበት የጋምቤላ ክልል የተከሰተው የሰላም እና የፀጥታ ችግር ምክንያት ሰራተኞች በሥራ ገበታቸው ላይ ተሟልተው አለመገኘታቸው በራሱ ሌላኛው እክልነው ተብሏል፡፡ የድርጅቱ የጥጥ ምርትም በተለያዩ ተባዮች እየተበላ ተፈላጊውን ውጤት ሊያስገኝ አልቻለም፡፡

ሳውዲ ስታር ከህንድ ካራ ቶሪ አግሮ ኢንዱስትሪ ኩባንያ ጋር የተለያዩ የግብርና ማሽኖችን ለመግዛት ውል ቢገባም፤ በድርጅቶቹ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ጉዳዩ ወደ ፍርድ ቤት ማምራቱ አይዘነጋም፡፡

2002 . በጋምቤላ ክልል በአበቦ ወረዳ አስር ሺህ ሄክታር መሬት በግብርና ለማልማት ቦታ የወሰደው ሳውዲ ስታር ከዚህ ሰፊ መሬት 1411 ሄክታሩን ብቻ እንዳለማ ታውቋል፡፡

LEAVE A REPLY