የአዲሱ” የክልል እንሁን” ትኩሳት እና የዶ/ር እብይ ምላሾች || በታምሩ ገዳ

የአዲሱ” የክልል እንሁን” ትኩሳት እና የዶ/ር እብይ ምላሾች || በታምሩ ገዳ

በትላንትና፣ በእለተ እሁድ ወደ ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵይ ጅማ በማምራት ከማህበረሰቡ ጋር ውይይት ያደረጉት ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ ከአካባቢው ተወካዬች “የክልል እንሁን” ጥያቄ አንደገጠማቸው ታውቋል።

እንደ ፈረንሳይ የዜና አገልግሎት(AFP)ዘገባ ከሆነ በፌደራል መንግስቱ የሀብት ክፍፍል ዙሪያ በደል እና መድሎ ደርሶብናል የሚል ቅሬታ ያደረባቸው እና በለፈው ህዳር ወር ውስጥ “የክልል እንሁን” ጥያቄን በድምጽ ብልጫ ያጸደቁት የከፊቾ ዞን ሹማምንቶች ይሄንኑ ጥያቄያቸውን በጠ/ሚ/ሩ ፊት ለማንጸባረቅ ሞክረዋል።

የህዝቡ ስጋቶች ተገቢነታቸውን ያመኑት ዶ/ር አብይ አህመድም “ሁሉንም ነገር በአግባቡ እንፍታዋለን፣ ችግሮቻችሁን ለመፍታት ክልል መሆን መፍትሄ ይሆናል ካላችሁም እናየዋለን “የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በነጭ ፣በአረንጓዴ እና በሰማያዊ ቀለማት ያሸበረቀው የከፊቾ ባህላዊ ኮትን ለብሰው ከምክትላቸው አቶ ደመቀ መኮንን፣ከመካላከያ ሹሙ አቶ ለማ መገርሳ እና ከባለቤታቸው ወ/ሮ ዝናሽ ታያቸው ጋር በመሆን በአካባቢው የደረሱት ዶ/ር አብይ አህመድ በሺዎች የሚቆጠረው የከተማው ነዋሪዎች ስማቸውን ደጋግሞ እየጠሩ ልዩ አክብሮታቸውን እንደገለጹላቸው ዘገባው አክሎ ገልጿል።

ታላቋ ኢትዬጵያን ወይስ አዲስ ክልልን እናስቀደም?

በቦንጋ ከተማ ቆይታቸው በተለያዩ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና መሰል ጉዳዬች ዙሪያ የተወያዩት ዶ/ር አብይ አህመድ የልማት ችግሮች ጎልተው እንደሚታዩ እና ትኩረት መሰጠት እንዳለበት ተሰብሳቢ ህዝቡንም ” ታላቋ ኢትዬጵያን እንገንባት ዘንድ ድጋፋችሁ አይለየን “የሚል ብሔራዊ አንድነትን የሚያጸና ንግግር በማድረግ ላይ ሳሉ አንዳንድ የአካባቢው ባለስልጣናት በበኩላቸው እኤአ ከ13 90 እስከ 1897ስለ ነበረው የከፋ ንጉሳዊ ዘመን ገናናነት ይናገሩ ነበር ያለው የኣጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘገባ አቶ ዳውድ መሐመድ የተባሉ የአካባቢው ባለስልጣን “በአሁኑ ወቅት የእኔም ሆነ የሕዝቡ ፍላጎት አዲስ አስተዳደር/ክልል መመስረት ነው “በማለት ለጠ/ሚ/ር አብይ አሕመድ በግላጭ እንደነገሯቸው ታዝቧል።

በዘጠኝ ክልላዊ መንግስታት ላለፉት ሀያ ሰባት አመታት በተመራችው፣ ከመቶ ሚሊዬን በላይ ህዝብ፣ከሰማኒያ በላይ ብሔር ባላት ኢትዬጵያ በደቡብ ኢትዬጵያ ውስጥ ብቻ በትንሹ አስራ አንድ የሚደርሱ ዞኖች “ወደ ክልልነት እንሸጋገር” የሚል ጥያቄን አቅርበው ጥያቄዎቻቸው ገና በእንጥልጥል ላይ ባሉበት በዚህ ወቅት ጅማ/ከፊቾ ላይም የራሳችንን ክልላዊ መንግስት ካላቋቋምን ከሚሉ ወገኖች ጋር የተጋፈጡት ዶ/ር አብይ አህመድ ጥይቄውን ላነሱ የማህበረሰብ ተወካዬች የመለሱት እንደ ሲዳማው ጉዳይ በዛቻ እና በማስፈራራት ሳይሆን “እስቲ ትንሽ ተረገጉ፣ታገሱን” የሚል ተማጽኖ አዘል መልእክት ለማቅረብ መገደዳቸውን አኤፍ ፒ አክሎ ዘግቧል።

ዘር እና ቋንቋን ማእከል ያደረገው የአገሪቱ ፌደራላዊ አስተዳደር እና ህገ መንግስት ምንም እንኳን የብሔር ብሔረሰቦችን መብት እስከመገንጠል ቢደግፍም የክልል እንሁን ጥያቄዎች በምን መልኩ ይስተናገዳሉ? የሚለውን እካሄድ በቅርቡ ሲዳማ ውስጥ የተፈጸመው የሰላማዊ ዜጎች ህይወትን ማጥፋት፣ ከኖሩበት በገፍ ማፈናቀል፣ የመኖሪያ ቤቶችን፣ የንግድ እና የአምልኮት ተቋማትን ማውደም እና መሰል እኩይ ድርጊቶች መከሰት የአብዛኛው የኢትዬጵያ ሕዝብ ልብ በእጅጉ ማድማቱ፣ አንገት ማስደፋቱ አይዘነጋም። ያ ጥያቄ እና መዘዙ አሁንም በይደር ለወራት ተራዘመ እንጂ ቀጣዩ እጣ ፈንታ ገና አለየለትም።

በቀጣይነት የሚነሱ ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ለማስተናገድ እና ሊከተሉ የሚችሉ አላግባብ ግጭቶች፣ ደም መፋሰሶች ካሉ ሁኔታዎችን ለማብረድ የጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ አስተዳደር ከፊቱ የተደቀነው አገራዊ ምርጫ ታሳቢ በማድረግ ሆደ ስፕፊነት፣ ብልሀት፣ ብቃት እና ቁርጠኝነትን ማሳየት ይጠበቅታል የሚሉ ወገኖች ተበራክተዋል።

LEAVE A REPLY