አዎ፤ አውሮፓዊው ቅኝ ገዢ ጣሊያን አድዋ ላይ ድል ሆኗልበ1888 ዓ/ም። በኢትዮጵያና ኢትዮጵያን በሚወክለው ቀስተደመናዊ ሠንደቅ ዓላማዋ ላይ ግን ከትውልድ የዘለለ ቂምቋጥሮ የደማ ልቡን በመዳፉ ደግፎ በተቆረጠው ቋንጃውእያነከሰ አንድ እግሩን ኤርትራ ላይ ልብና ሌላ እግሩን ጣሊያን– አውሮፓ ላይ አድርጎና ጠቅላይ ሚኒስትሩን ፍራንቺስኮክሪስፒን ከሥልጣን አባርሮ ድፍን ጣሊያን ሀዘን ተቀመጠ።
አርባ ዓመት ሲታመምና ሲያገግም ኖረ። ጣሊያን በኢትዮጵያናበሠንደቋ ላይ ለአርባ ዓመት ያረገዘው ቂም ዱቼንና ፋሽስትፓርቲን ወለደ። ለጣሊያን ትንሳዔ ኢትዮጵያ መሥዋዕትመሆን አለባት ሲል እነሆ ዱቼ በሮም አደባባይ ተጣራ።ሙሶሎኒ ኢትዮጵያን በመሥዋዕትነት ለተዋረደችው ጣሊያን ትንሳኤ አቀረበ። አውሮፓ አጨበጨበ፤ ቪቫ ዱቼ ሲል ደገፈ።
እነሆም የምፅዐት ዘመን በሀበሻ ምድር ሆነ። አዎ፤ ታላቁየኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ በፋሽስቶች ተረገጠ፤ ተቃጠለ፤ታገደ። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማበፋሽስቶች በይፋ ከኢትዮጵያ ሠማይ ላይ ተጋዘ። ተሰደደ።ህገ ወጥ ሠንደቅ ዓላማ ተብሎም ታወጀ። አረንጓዴ፤ ቢጫቀይ የኢትዮጵያን መለያ (መንግሥታዊ ያይደለ) ህዝባዊሠንደቅ ዓላማ የያዘ ሁሉ በፋሽስት ጥቁር ለባሽ ኮማንዶናጦር ሠራዊት በጥይት ተነደለ፤ በእግረ ሙቅ ተከረቸመ፤በቆመጥ ህሊናውን እስኪስት ተወገረ፤ በሶማሊያ በኤርትራእና በጣሊያን ደሴቶች እስር ቤቶች እየተወሰደ ታጎረ። በሀገሩምድርም ወህኒ ተወረወረ፤ ከሀገርም ተሰደደ። እነሆምለአምስት ዓመት ኢትዮጵያ በጣሊያን ፋሽስቶች ሥርወደቀች። እነሆም እልፍ ኢትዮጵያውያንም ስለ ሀገራቸውናስለ ሠንደቅ ዓላማቸው ወራሪ ፋሽስቶችንና ምንደኛባንዶችን እየጣሉ ወደቁ።
በአምስቱ ዓመት የወረራና የግፍ አገዛዝ ዘመን የኢትዮጵያሠንደቅ ዓላማ ግን ለአንዲትም ደቂቃ ቢሆን ከኢትዮጵያምድር ከተራራውና ከጉድባው፤ ከዋሻውና ከገደላ ገደሉ ስርአሻቅባ ከመውለብለብ የሚያግዳት አንዳችም የፋሽስት ሃይልአልነበረም፤ የአርበኛው ሀይልና ጉልበት ሠንደቅ ዓላማውንከፍ አድርጎ መያዝና ለነፃነቱ መዋደቅ ነበርና!! በአምስትዓመት የኢትዮጵያ አርበኞች መሥዋዕትነት እነሆ ኢትዮጵያከዱቼ ፋሽስት መዳፍ ነፃ ወጣች፤ ታላቂቷም የኢትዮጵያሠንደቅ ዓለማ ነፃነቷን ተቀዳጅታ በኢትዮጵያ ሠማይ በነፃነትተውለበለበች። ይህ የሆነው ከአንድም ሁለቴ በቀደመውዘመን ነበር። (እነሆም በተከታታይ ትውልድ ሁሉ ሠንደቅዓላማችንን እንደ አባትም እንደ እናትም ፆታ እያፈራረቅንዛሬ ድረስ የምንጠራው ለዚህ ነው)
የኢትዮጵያና የሠንደቅ ዓላማዋ ፍዳ ከጣሊያን ወረራ ጋርአላበቃም። ሶማሊያ የታላቋን ሶማሊያ ቅዠት እውንለማድረግ ካንዴም ሁለቴ የኢትዮጵያን ሠንደቅ ዓላማአቃጥላና ረግጣ፤ ኢትዮጵያንም ልታንበረክክ ተንጠራርታነበር። ኢትዮጵያንና ሠንደቅ ዓላማዋን የደፈረበኢትዮጵያውያን አናብስት ክንድ መድቀቁ የታሪክ ሀቅ ነውናየታላቋ ሶማሊያም ቅዥት ያው ቅዠት ሆኖ ቀርቷል።
ዘረኝነት የተጠናወታቸው ዕብሪተኞች ግን ድሮም ሆነዘንድሮ ከታሪክ አልተማሩም ነገም አይማሩም፤ አይታረሙም።አብነት ቢባል የደደቢቱን ህወሃት የሚቀድም አይኖርም።እርግጥ ነው ያጎረሰን እጅ ነካሹን ሻዕቢያን አንረሳም።በኢትዮጵያና በሠንደቅ ዓላማዋ ላይ የዋለውን ግፍ ለታሪክትተነዋል። እንደ ሻዕቢያና ህወሃት ሁሉ ኦነግም የኢትዮጵያንሠንደቅ ዓላማ አዋርዷል፤ ዘልፏል፤ በተረታ ተረት ትርክት በኢትዮጵያና በተጋመደው የህዝቦች አንድነቷ ላይተዘባብቷል። ኢትዮጵያ ላይ በኦቦ ለማ መገርሳ አስገምግሞ የተነሳው ኢትዮጵያዊነት በ‘ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው!” አዝማች ኮከብ መርህ እነሆ ዛሬ ላይ ‘ኢትዮጵያዊነት የለም’ እና ‘ኢትዮጵያዊ ስለመሆናችን መደራደር’ ለሚሉት ኦነጋውያን ሁሉ ትዝብት ሆነ እንጂ ትርፉ!
ዱቼ በራሱ ህዝብ ተዋርዶ ህይወቱንከማጣቱ በፊት ያኔ ጥቁር ለባሾችንኢትዮጵያ ላይ ሲያዘምት ለትግራይምንደኞች /ባንዶች/ የላከላቸውመልዕክት ነበር፤ አማራና ኦሮሞ ጠላቶቻችሁን ልናጠፋናእናንተን ልናሳድግ በእነሱም አናት ላይ እናንተን ልናበለፅግየመጣን በመሆኑ ከእኛ ጋር ቆማችሁ ዓላማችንን አራምዱ።አማራና ኦሮሞን ተባብረን ‘እሳትና ጭድ’ እናርጋቸው – የሚል። ያኔ የዱቼ ዓላማና ግብ በአብናቶቻችን አርበኞችደምና አጥንት በአጭር ተቀጨ። ቅኝ አገዛዙም ተሰባበረ።ዱቼም ሞተ ተቀበረ። ፋሺዝም በሀገረ ጣሊያን ተንኮታኮተ።ነገር ግን እነሆ ከትግራይ ምንደኞች የተወለዱት የህወሃትመሥራቾች ደደቢት በረሃ ገብተው ዱቼን ከሙታን መንደርአንስተው ከመንፈሱ ጋር ተጋቡ። እነሆም ዱቼ በደደቢት በረሃበህወሃት አድሮ ህወሃትን ሆነ። ህወሃትም የዱቼን መንፈስወረሰ። ፋሽዝምም በህወሃት ተተካ። ህወሃትም ፋሽሰትንሆነ። የዱቼ መልዕክትና ዓላማ /አማራና ኦሮሞን በማባላትየትግራይን የበላይነት ማስፈን/ ከ1967 ዓ/ም ጀምሮ እስከዚህዘመን የህወሃት ማኒፌስቶ ሆነ። የህወሃት መለያ!!
ዱቼ በአካል ቢሞትም ዓላማው በህወሃት አልሞተም። እነሆዱቼም በመለስ ተቀየረ፤ መለስም ዱቼን ሆነ። ጥቁር ለባሹየዱቼ ወራሪ በህወሃት አጋዚ ወራሪ ተተካ። ከደደቢት እስከአራት ኪሎ ህወሃት አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያን ሠንደቅዓላማ እንዳዋረደ፤ እንደረገጠ፤ እራፊ ጨርቅ እያለ ቁሳቁስእየቋጠረ አንደተዘባበተበት በግፍና በንፁሃን ደም እየዋኘእንደ ዱቼ አዲስ አበባን በበቀለኛውና ቂመኛው ወራሪውጦር ተቆጣጠረ። እነሆም ኢትዮጵያና ሠንደቅ ዓላማዋበሀገር በቀሉ ወራሪና ቅኝ ገዢ ህወሃት መዳፍ ሥርበኢህአዴግ መንግሥትነት ከግንቦት 20/1983 ዓ/ም ጀምሮእስካለንበት ዘመን እየተሰቃዩ ይገኛሉ።
እነሆም ኢትዮጵያን ባስተዳደሩት መሪዎች በየትኛውምዘመነ መንግሥት ውስጥ ተደርጎና ተሰምቶ የማያውቀውንአረንጓዴ ቢጫ ቀይ (የመንግሥት ዓርማ ያይደለ) የኢትዮጵያንህዝብ ሠንደቅ ዓላማ ፋሽስት ወራሪ ህወሃት አዋጅ አውጥቶበወንጀለኛ ሠንደቅ ዓላማነት ፈርጆ በኢትዮጵያ ሠማይ ላይእንዳይውለበለብ አገደ። ከወራሪው ዱቼ ዘመን ቀጥሎሠንደቅ ዓላማችን በወንጀለኝነት ከኢትዮጵያ ሠማይ ላይሲታገድ ሁለተኛው በዘመነ ህወሃት/ኢህአዴግ መሆኑ ነው።ንፁሁን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሠንደቅ ዓላማ መያዝ በህወሃትአጋዚ ጦር በጥይት ያስነድላል። በወህኒ ቤቶች ለግፍናለቶርቸር ይዳርጋል። በሽብርተኝነት ያስከስሳል። ከሀገርያሰድዳል።
በኢትዮጵያ ምድር ግን እንዲህ የነበረው በአምስቱ ዓመትየፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ ዘመን ብቻ ነበር። ህወሃት ሀገርበቀል ወራሪና ቅኝ ገዢ ከመሆኑ በቀር ተፈጥሮውም ሆነእርኩሰቱ፤ ለኢትዮጵያና ለሠንደቅ ዓላማዋ ያለውም ጥላቻከአምስቱ ዓመት የዱቼ ቅኝ አገዛዝ ቢብስ እንጂ የሚያንስአይደለም።
የተስፋይቱን ምድር ኢትዮጵያን የሚጠብቃት አንድ አምላክበየዘመኑ ከጥፋት የሚታደጋትን ትውልድና መሪ ባልታሰበወቅት ባልታሰበ ዘመን እያስነሳ ተዓምር ሲታይ ቆይቷል።በ2010 ዓ/ም በወርሃ መጋቢት የሆነው ይኸው ነው።በኦህዴዱ ለማ መገርሳ እና በብአዴኑ ገዱ አንዳርጋቸውቲሞች የታገዘው በኢህአዴግ ማህፀን ያደገውና የህወሃትንእርኩሰት የተጠየፈው ዶ/ር አብይ አህመድ /ጠቅላይ ሚኒስትር/ ሆኖ ተሾመ! እኛም ኢትዮጵያን አስቀድሞ ኢትዮጵያን ከፍላደረገ እንደ ኢትዮጵያዊም እንደ ሰውም ለኢትዮጵያናህዝቦቿ የነገ ተስፋና ሠላም ፍቅርና ብልፅግና አንድነትናህብረት ለቆመ መሪ ሁሉ ድጋፋችንና ዝግጁነታችን እንደአባቶቻችን ነውና አብይንና ቡድኑን የደገፍነውና ተስፋምየሰነቅነው በሙሉ ጉልበትና ፍላጎትም ከጎኑ የቆምነው እነሆየኢትዮጵያን ስም ጠርቶ ከፍ ስላደረጋት ነው! ኢትዮጵያውያን ከልሂቅ እስከ ደቂቅ ከሰሜን እስከ ደቡብ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ በድፍን ኢትዮጵያ ስናወግዘው ከኖርነው ኢህአዴግ ጎን የቆምነው ኢትዮጵያን የሚታደጉ፤ ኢትዮጵያውያንንም የሚያዳምጡ መሪዎች አገኘን ብለን ነው።
ከደቡብ አፍሪካ እስከ ሰሜን አሜሪካ ከእስያ ጥግ እስከ አውሮፓ ኢትዮጵያዊ ሁሉ አረንጓዴ ቢጫና ቀይ (ኮኮብ አልባ) የአባቶቹን ነፃ ሠንደቅ ዓላማ እያውለበለበ <አብይ የኛ፤ አብይ የኛ> እያለ በሲቃ የዘመረው በህወሃት/ኢህአዴግ ስትሳደድና ስትሰደድ የኖረችውም ሠንደቅ ዓላማ ነፃ የምትወጣ መስሎት ነው። በመስቀል አደባባይ ሰማየ ሰማያትን የጋረደው ኮኮብ አልባው ሠንደቅ ዓላማ እየተውለበለበ የአዲስ አበባ ወጣት፤ ጎልማሳና አዛውንት ሰኔ 16 ለአብይና ለቲሙ የድጋፍ ድምፁን ብቻ ሳይሆን የቀቢፀ ተስፈኞችን የግድያ ሙከራ ለሰከንድ ሳያመነታ በደሙ ጭምር አብይን የታደገው የሠንደቅ ዓላማውና የኢትዮጵያ ትንሳኤ ምልክት አብይ ተነክቶብኛል ብሎ በማመኑ ነው። ይህ ሀገራዊና ዓለም ዐቀፋዊ የኢትዮጵያውያን ፍፁማዊ ድጋፍና አብያዊ ዕምነትከመጋቢት 2010 ዓ/ም ጀምሮ ቢያንስ ለሰባት ወራት ሳይሸራረፍና <ከመደመር ባቡር> ወራጅ ሳይበዛ ዘልቋል።
ይሁንና ይህ ለአብይና ለቲሙ <ከድፍን> ኢትዮጵያውያን ያለ አንዳች ስስት የተሰጠ ዕምነትና ተስፋ በሚያስደነግጥ ፍጥነት ዕምነቱና ተስፋው በአብያዊው መንግሥት <ኢፍትሃዊ> ድርጊቶች ሲሸረሸር፤ ተስፋውም ሲሸሽ መታየቱ እጅግ ቅስምን የሚሰብር ክስተት እየሆነ ይገኛል። ሁለት ሺህ አሥራ ሁለት ገና ከመጥባቱ በመስከረም ወር በአዲስ ዓመት መባቻ ኮከብ አልባዋ የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ እንደ ህወሃት/ኢህአዴግ ዘመነ አገዛዝ ሁሉ በኦዴፓ/ኢህአዲግ መሪ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መንግሥታዊ መዋቅር በኦፊሴል በህገወጥ ሠንደቅ ዓላማነት ተወንጅላ ለስደትና ለግዞት መዳረጓ ህወሃት መራሹን ዘመን በአዲስ የመተካት ያህል እንዲሰማን አድርጎናል። ቢያንስ ይህችን የአባቶቻችንን የነፃነት ሠንደቅ በአብያዊው ዘመን በኢትዮጵያ ሰማይ ስር ያለፍርሃት፤ ያለመ,ታሰርና ያለመከሰስ ስጋት ኢትዮጵያውያን በነፃነት የማውለብለብ መብት ሊኖራቸው ይገባ ነበር። እነሆ ይህ በዶ/ር አብይ መንግሥት ሊሆን ግን አልተፈቀደም!!
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሆይ!! የኢትዮጵያንናየህዝቧን ሠንደቅ ዓላማ በሽብርተኛ ምልክትነት የወነጀለውንና ከኢትዮጵያ ሠማይ ላይ ያገደውን የህወሃት/ኢህአዴግ ህገ ወጥ አዋጅ በአንተ ዘመን ተደግሞ በአደባባይም በህግ አስከባሪዎችህ እጅ ኮኮብ አልባዋ ሠንደቅ ዓላማ ስትዋረድና ስትንገላታ እንደማየት የሚያምና የሚያስቆጣ ሁነት ከቶስ ምን አለ? አብይ ሆይ! በመንግሥትህ በኮኮብ አልባዋ ሠንደቅ ዓላማ ላይ የታወጀውን ዘመቻ ያለአንዳች ቅድመ ሁኔታ በህጋዊ አዋጅ አንሳልን!!! ይህንንየምንጠይቅህ በበዓለ ሲመትህ መጋቢት 24/2010 ዓ/ም ላይበክብርና በታላቅ የጀግንነት አክብሮት ደጋግመህ ባነሳሃቸውበአድዋ በመተማ በማይጨው በካራማራና በባድመ ይህቺንዛሬ የተወነጀለችውን ንፁህ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የኢትዮጵያንመገለጫ ሠንደቅ ዓላማ ከፍ አድርገው በተሰዉት እልፍአእላፍ ኢትዮጵያውያን አጥንትና ደም ነው።
(ፎቶ፤ በባድመ ሠማይ ላይ የተውለበለበው ሠንደቅ ዓላማ)
ስለ ኢትዮጵያ ታሪክና ስለ ኢትዮጵያውያን ጀግንነትና የነፃነትተምሳሌነት ሲተረክና ሲነገር በዚህ ታሪክ ውስጥ ሁሉ /ዛሬበሽብር ምልክትነት በደደቢቱ ህወሃት የተወነጀለውና ዛሬ ደግሞ አንተ በምትመራው መንግሥት የተደገመው/ ኮኮብ አልባው የኢትዮጵያ ህዝብ ሠንደቅ ዓላማ አለ።
ነፃነቷን በህወሃት/ኢህአዴግ የተገፈፈችውና በአንተ መንግሥት <ወንጀለኝነቷ> የፀደቀው ኮኮብ አልባ አረንጓዴቢጫ ቀይ /የመንግሥት ዓርማ ያይደለች/ የኢትዮጵያ ሠንደቅዓላማ ነፃ ሳትወጣ ስለ ኢትዮጵያውያን ጀግንነትና የጥቁርህዝቦች ነፃነት ሠንደቅ ተምሳሌነት በአደባባይ መዘከር ምንማለት እንደሆነ በቃላት ማስቀመጥ አንፈልግም፤ አንተየተከበርከው ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ የታሪክ ሰው ነህና።ሠንደቅ ዓላማችን በሽብርተኝነት ተወንጅላና ከሀገር ሠማይ ላይ ታግዳና እግር ስር ተጥላ የሠላም ዓየር የሚተነፍስኢትዮጵያዊ አይኖርምና አብይ አህመድ ሆይ ኢትዮጵያውያንሁሉ ምላሽህን እንጠብቃለን!! ሠንደቅ ዓላማችን ነፃትውጣ!!! አዎ! የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ነፃ ትውጣ!!!
ኢትዮጵያ በቅን መሪዎቿና በእግዚአብሄር እርዳታ ትንሳኤዋዕውን ይሆናል!
መስከረም 2012 ዓ/ም ( ሴፕቴምበር 2019)
ሲድኒ አውስትራሊያ
ዋቢ
1 ለዚህ ፅሁፍ አቅርቦት በሚስማማ መልክ /ከህወሃት ዓላማናግብ/ አኳያ የተፍታታው ዱቼ ለትግራይ የላከው መልዕክትየተገኘው ‘የሀበሻ ጀብዱ’ በአዶልፍ ፓርለሳክ ተፅፎ በተጫኔጆብሬ መኮንን ከተተረጎመው መፅሀፍ ነው።
*በባድመ ሠማይ ላይ ስለተውለበለበችው ኮኮብ አልባ ንፁህ /የመንግሥት ዓርማ ያይደለች/ የኢትዮጵያ ህዝብ የኢትዮጵያሠንደቅ ዓላማ ቀጣዩን ቪዲዮ ይመልከቱ፤https://www.youtube.com/watch?v=pDv0uaKuOiA
አድራሻ፤ mmtessema@gmail.com