የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || መስከረም 21 ቀን 2011 ዓ.ም

የኢትዮጰያ ነገ ዜናዎች || መስከረም 21 ቀን 2011 ዓ.ም

 በኢሬቻ ዋዜማ የአዲስ አበባ ፖሊሶች አዲስ ዮኒፎርም በይፋ ተመረቀ
ከኦሮሚያ ክልል በመጡ ወጣቶችና ከፍተኛ አመራሮች የተዋቀረውና በስም ብቻ አዲስ አበባ ፖሊስ ተብሎ የሚጠራው ተቋም አባላት አዲስ ዮኒፎርም ተሰፍቶላቸዋል:: የከተማው ፖሊስ ለበርካታ ጊዜ ሲጠቀምበት ከነበረው የፖሊስ የደንብ ልብስ በተጨማሪ በአዲስ መልክ የተዘጋጀ የደንብ ልብስ ዛሬ ይፋ ተደርጓል::
ከከተማው ም/ከንቲባ ጀምሮ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነርና የበላይ አመራሮች በኦዴፓ አባላት እና በኦሮሚያ ተወላጆች መዋቀሩ በእጅጉ አነጋጋሪ በሆነበት ወቅት አዲሱ የፖሊሶች ዩኒፎርም ሆን ተብሎ በኢሬቻ ዋዜማ ይፋ መደረጉ በሁሉም ረገድ ስልጣን ላይ ያለው አካል የተረኛነት ፖለቲካን በግልፅ እያንፀባረቀ መሆኑን ያሣያል በሚል እየተተቸ ይገኛል:: እሬቻና መስቀል መሀል ያለውን የሣምንት ልዮነት በማስቀመጥም ኮሚሽኑ አባላቱ ልብሱን በደመራው ዕለት ቢለብሱት ኖሮ ሁሉንም ብሔር በመወከል ረገድ የተሻለ እንደነበርም ይገልጻሉ::
አዲሱን የአዲስ አበባ የፖሊስ አባላት የደንብ ልብስ በዛሬው እለት የመረቁት ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ፤ የከተማዋን ሰላም እና ደህንነት ለመጠበቅ ጠንካራ ስራ እየሰራ ያለውን የአዲስ አበባ ፖሊስ የማዘመን ስራ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ በመሠራት ላይ መሆኑን ገልጸው
በዘላቂነትም የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባን የሚመጥን ዘመናዊ እና የተደራጀ የፖሊስ ሰራዊት ግንባታ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም ተናግረዋል::
ብሔርተኝነት አለመግባባቶች የሚታመሰው የደቡብ ክልል ም/ቤት የ8 ቢሊዮን ብር በጀት አፀደቀ

ብሔርተኝነት ፣ የክልልነት ጥያቄዎች እና ውስጣዊ አለመግባባቶች ያሉበት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል መንግስት መስተዳድር ምክር ቤት ለ2012 በጀት ዓመት ለክልል ማዕከል ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚውል የ8 ቢሊየን ብር በጀት ማፅደቁ ተሰማ::

ምክር ቤቱ ባካሄደው 203ኛ መደበኛ ስብሰባ ለመደበኛና ለካፒታል ወጪ 4 ቢሊየን ብር፣ ለክልላዊ ፕሮግራም ማስፈፀሚያ 3 ነጥብ አንድ ቢሊየን እንዲሁም ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈፀሚያ 1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር እና ለመጠባበቂያ 200 ሚሊየን ብር መድቧል::

ምክር ቤቱ የ2012 በጀት ዓመት የመደበኛ በጀት አመዳደብን ታሳቢ ያደረገው ቀደም ሲል በክልሉ ተዘጋጅተው ተግባራዊ የተደረጉ የበጀት አስተዳደር መመሪያዎችን መሰረት አድርጎ ሲሆን ፤ በክልሉ ባለበጀት መስሪያ ቤቶች ላይ የሚስተዋለውን አላስፈላጊ የበጀት ብክነት ለመቀነስና ለመቆጣጠር እንዲሁም ውስን የሆነውን ሀብት በተቀላጠፈ በተቀናጀና በውጤታማነት መጠቀም እንዲችል የበጀት አስተዳደር መዋቅር መሰብሰብ እና የአሠራር ማሻሻያ ተግባራዊ እንዲደረግም ወስኗል::

የ2012 ካፒታል በጀት የመንግስት የልማት ፖሊሲ እና ስትራቴጂዎች መሰረት ማድረግ የበለጠ ጠቀሜታ እንዳለው በመታመኑ ውስን ለሆኑ ጥቂት ፕሮጀክቶች የድህነት ቅነሳ ሴክተር፣ ለነባር ፕሮጀክቶች ትኩረት በመስጠት እንዲተገበሩም ነው ተነገረው::

የዘላቂ የልማት ፕሮጀክቶችን በተመለከተ በፌዴራል መንግስት የገንዘብ ሚኒስቴር በተዘጋጀው መመሪያ መሰረት ለክልሎች የሚመደበው ውስን አላማ ያለው የፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የድጎማ በጀት ማዋል የሚችለው በኢንዱስትሪው ዘርፍ በተለይም ለአግሮ እንዱስትሪ ማስፋፊ ፕሮጀክቶች መሆኑን ዜናው ያስረዳል::

ይህን ተከትሎ ለይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና በክልሉ በተለያዩ ዞኖች ለሚገኙ 31 የክላስተር ማዕከላት ግንባታ ማጠናቀቂያ ድጋፍ እንዲሆን ተወስኗል::

ክልላዊ ፕሮግራም ፕሮጀክቶች የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ግንባታ፣ የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ተዘዋዋሪ ፈንድ፣ ባለፉት በጀት ዓመታት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ የመስኖ ግንባታና የቴክኒክና ሙያ ግንባታ ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ የሚውል በጀት በመደልደል በፀደቀው በጀት እንዲደገፉ ም/ቤቱ ከመግባባት ላይ ደርሷል::

ቀዳማይ እመቤት ጽ/ቤት ያስገነባው የሕጻናት ማሳደጊያ ሥራ ጀመረ
በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት ወጪ የተገነባው የቁስቋም ብርሃን የሕፃናት ማሳደጊያ ማዕከል ዛሬ ተመርቋል::
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢኒጅነር ታከለ ኡማ እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ
ሓላፊዎች መገኘታቸውም ተነግሯል::
ቀዳማዊት እመቤት ወይዘሮ ዝናሽ ታያቸው የቁስቋም ብርሃን የሕጻናት ማሳደጊያ ማዕከል ግንባታ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ በአጭር ጊዜ በመጠናቀቁ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸው፤ ጽህፈት ቤታቸው ህፃናትን ጨምሮ ሴቶች እና አረጋዊያን ላይ የሚሰራውን ሥራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡
ምክትል ኪንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በበኩላቸው የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤት ለከተማዋ ህፃናት ላደረገው ድጋፍ በህፃናቱ እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በቀጣይነት በከተማዋ ውስጥ ለሚሰራቸው ስራዎች ሁሉ የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል::
ማዕከሉ 12 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገበት ሲሆን ከስድስት ወራት በፊት መጀመሩ ይታወሳል፡፡ 96 ህፃናትን ተቀብሎ መስተናገድ የሚያስችለው ማዕከሉ ቤተ መጽሀፍት፣ የመኝታ ክፍሎች፣ የመመገቢያ አዳራሽ ፣ ምቹ የመማሪያ ክፍሎች እና ሰፊ የመጫወቻ ቦታን ያካተተ ነው፡፡ ጽህፈት ቤቱ በአዲስ አበባ ቃሊቲ አከባቢ እያስገነባ ካለው የልዩ ፍላጎት ማዕከል በተጨማሪ በሌሎች የሃገሪቷ ክፍሎች 20 የሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤቶችን በመገንባት ላይ ነው::
በፓሪስ አንድ ግለሰብ አራት ፖሊሶችን በተቋማቸው ደጀፍ ገደለ

በርካታ አፍሪካውያን ስደተኞች እና አክራሪ የእስልምና ድርጅት አባላት፣ ደጋፊዎች በብዛት ይገኙባታል የምትባለውፓሪስ በየጊዜው የተለያዮ የነፍስ ማጥፋት ክስተቶች የሚታዮባት መሆኗ ቀጥሏል::

በአውሮፓዊቷ ፈረንሳይ ዋና ከተማ ፓሪስ አንድ ግለሰብ በፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት በር ላይ፣ ስለት በመጠቀም በፈጸመው ጥቃት አራት የፖሊስ አባላት መግደሉን ከሥፍራው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ::

በፀጥታ አካላቱ ላይ ጥቃት የፈጸመው ግለሰብ የፖሊስ ዋና መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ህንጻ ውስጥ ተቀጥሮ ይሠራ ነበር:: ጥቃቱን በፈጸመበት ቦታ ላይ በነበሩ ፖሊሶች በተተኮሰበት ጥይት ሕይወቱ አልፏል::

ጥቃቱን ተከትሎ ‘ኢል ዴ ላ ሲቴ’ የተባለው የፈረንሳይ ፖሊስ ዋና መስሪያ ቤት የሚገኝበት አካባቢ ከማንኛውም እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ ተዘግቷል::

አሳዛኙ ጥቃት የተፈጸመው የፈረንሳይ ፖሊሶች በአባላሎቻቸው ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች እንዲቆሙና እራሳቸውን የሚያጠፉ ፖሊሶች ቁጥር መጨመሩም ያሳሰበው መሆኑን መነሻ በማድረግ በመላ ሀገሪቱ ተቃውሞ ካካሄዱ ከአንድ ቀን በኋላ ነው::  የፈረንሳዩ የሃገር ውስጥ ሚንስትር ክሪስቶፍ ካስታነር ጥቃቱ የተፈጸመበት ሥፍራ በመገኘት ሀዘናቸውን ገልጸዋል::

LEAVE A REPLY