የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ 5 ለ4 በሆነ ድምፅ የታከለ ኡማ ከሓላፊነት መነሳት ሻረ

የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ 5 ለ4 በሆነ ድምፅ የታከለ ኡማ ከሓላፊነት መነሳት ሻረ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ማዕከላዊ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ በአዲስ አበባ ስብሰባውን በማካሄድ ላይ ይገኛል። የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ ሥራ አስፈጻሚ አካላት እያካሄዱት ባሉት ስብሰባ ላይ የተለያዮ ጉዳዮች ተነስተው በስፋት የተወያዮ ቢሆንም በዋናነት በኦዴፓ የተወሰኑ ከፍተኛ አመራሮች እና በጽንፈኛ የኦሮሞ ፖለቲከኞች በከፍተኛ ሁኔታ እየተራገበ ያለው “የፊንፊኔ ኬኛ” አጀንዳ ዋነኛው መሆኑን ለማወቅ ችለናል::

ለኦዴፓ ቅርበት ያላቸው ታማኝ ምንጮቹን መሠረት አድርጎ ዜናውን ያደረሰን በአዲስ አበባ የሚገኘው የኢትዮጵያ ነገ ሪፖርተር ከአዲስ አበባ ጉዳይ ባሻገር የከተማ መስተዳደሩ ም/ከንቲባ የታከለ ኡማ ጉዳይ ቀደሚ መወያያ ነበር:: በኢሬቻ በዓል ላይ የአማራ እና የኦሮሞ ሕዝብን የሚያጋጭ ንግግር በይፋ ያደረጉት የሽመልስ አብዲሳ ሀሳብም ሌላኛው ነበር::

ሁለቱ ግለሰቦች በተለያየ መንገድ ተገምግመው ከቦታቸው ይነሱ  በሚለው ላይ የሽመልስ አብዲሳ ጉዳይ ለአርብ ውይይት በይደር ሲታለፍ ታከለ ኡማ ግን ከከንቲባነት እንዲነሱ 5 ለ 4 በሆነ ድምፅ በማዕከላዊ ኮሚቴው ጸድቆ ነበር::ይሁንና አስቀድሞም ቢሆን የታከለ ኡማን መነሳት ያላመኑበት የኦዴፓ አስፈጻሚዎች ባሳደሩት ከፍተኛ ተፅዕኖ ከንቲባው በሥራ ላይ እንዲቆዮ እንደ አዲስ መወሰኑን ከደረሰን ዜና መረዳት ችለናል::

የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ በስብሰባውም የፓርቲውን እና የክልሉን መንግሥት የሥራ አፈፃፀም በመገምገም አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ ይጠበቃል። በዚህም ኮሚቴው የነበሩ ጥንካሬዎችን እና ድክመቶችን በመለየት መፍትሄ ይፈልጋል መባሉን ሰምተናል::

እንዲሁም ማዕከላዊ ኮሚቴው  በወቅታዊ ሀገራዊ እና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ ከመምከር ባሻገር የፓርቲው የውስጥ አንድነት እና የፖለቲካ ፓርቲዎች ሪፎርምንም በአጀንዳ መያዙ ታውቋል። ማዕከላዊ ኮሚቴው እንደ ሀገር እና እንደ ክልል የተጀመሩ ለውጥ እንቅፋቶችን በመለየት አቅጣጫ  እንደሚያስቀምጥም እየተነገረ ነው።

LEAVE A REPLY