ይችን የኔን አገር፤
የቢቸግር ሊቆች ፤
ከጫማዋ በፊት፤ ልኳን ሳያጠሩ፤
ይወዘውዟታል፤
በራሳቸው ኮቴ ፤
ጫማ ልበሽ ብለው፤
በምኞታቸው ልክ መጫሚያ እያሰሩ።
እነ ልክ አያውቁ፤
ልካቸውን እንጃ፤ልኳን እየካዱ ፤
በነርሱ ጫማ ልክ ፤
ያገሬን ቁመና ወርድ እየከነዱ፤
ተረከዝ ጣቶቿን፤
ከውራጅ ጫማቸው፤
ግቢ ግባ ብለው ከወዲያ ከወዲህ እየገደገዱ፤
ይኸው ዛሬ ድረስ፤
እንደው እምቡፍ እምቡፍ
እንደው ተንቦክ ተንቦክ ሆነባት መንገዱ።
|| ጃኖ መንግስቱ ዘውሎ ||