የለዛ አዋርድ ተሸላሚው ጃንቦ ጆቴ || ለኦቢኤን ቴሌቪዥን

የለዛ አዋርድ ተሸላሚው ጃንቦ ጆቴ || ለኦቢኤን ቴሌቪዥን

|| ትናንት ለኦቢኤን ቴሌቪዥን ጣብያ በአፋን ኦሮሚፋ ከሰጠው ቃለ ምልልስ ያነሳቸው ነጥቦች ||

– አማርኛ ቋንቋ አድጎ እዚህ የደረሰው በአርት (art) ነው:: አማርኛ ቋንቋን እንዲወደድ ያደረጉት ከሌላ ህብረተሰብ የወጡ አርቲስቶች ጭምር ናቸው:: ለምሳሌ ብንጠቅስ ከኦሮሞ ጥላሁን ገሰሰ ከትግራይ ፀሀዬ ዮሐንስ ከጉራጌ ማሕሙድ አህመድ ከአማራ ኤፍሬም ታምሩ እና ሌሎችም ናቸው::

– “አማርኛ ተጭኖብን ነው” የሚባለው አስተሳሰብ ፈፅሞ ስህተት ነው:: ማንም ማንም ላይ አልጫነም:: ይሄ የተሳሳተ አረዳድ ነው:: እኛም ቋንቋችን እንዲያድግ ከፈለግንና አማረኛ ያደገበትንና የተወደደበትን መንገድ መከተልና ቋንቋችንን ማሳደግ ነው ያለብን::

– “ቋንቋችንን ካልተናገራችሁ” ብለን በመሳሪያ ብናስገድድ ቋንቋችንን ከማሳደግ ይልቅ እንዲጠላና እንዳያድግ ነው ሚያደርገው::

– በቁጥር 40-50 ሚሊዮን ብንሆን የትም አንደርስም:: ምንም አናመጣም:: እኛ 50% ነን ብንል ሌሎችም እኮ ተሰባስበው 50% ይሆናሉ! ከሌሎች ብሄር ብሄረሰቦች ጋር ተፋቅረን ተሳስበን ስንኖር ነው ለውጥ የምናመጣው::

– ብዙ ነን ብለን ከዛም ከዚህም መጋጨት ለኦሮሞ ምንም የሚፈይደው ነገር የለም:: ጠላት ከማብዛት ውጭ!

– መለወጥ ያለብን በዙ ነገሮች አሉ:: በእኛ ላይ ጥሩ አመለካከቶች የሉም:: ለኦሮሞ የሚታገሉ ድርጅቶች ብዙ ስህተት ሰርተዋል:: የኦሮሞን ህዝብ ልክ እንደ ቡልጉ (አውሬ) እንዲታይ ትልቅ ሚና ተጫውተዋል:: ይህ ነገር በቶሎ ማስተካከል አለባቸው:: ያለበለዚያ ጠላት እያበዛን ነው ምንሄደው::

– መፎከር የሚገባው ያኔ ወያኔ አራት ኪሎ በነበረ ሰአት ነበር:: አሁን የእኛ ሰው ነው ሀገር እየመራ ያለው:: እኛ አራት ኪሎ ገብተን መፎከሩ በእኛ ላይ አያምርም!

– ይልቅ የሚያምርብን እንደአባቶቻችን አቃፊ ብንሆን ነው:: ማሸነፍ የምንችለው በፍቅር ብቻ ነው!

LEAVE A REPLY