ምሳ ሰዓት ላይ አንድ ወዳጄ ስልክ ደውሎ አቶ ጌታቸው ረዳ ከትግራይ ሚዲያ ሃውስ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ እንድመለከት ሲወተውተኝ ከወትሮ የተለየ ነገር ይኖራል ብዬ ጠብቄ ነበር። አንደኛውን ክፍል ለማየት ስከፍት “ኢትዮጵያ ለውጪ ባለሃብቶች ለቅርጫ የቀረበች ሀገር ሁናለች” የሚለው ርዕስ ትኩረቴን ሳበው። ከዚያ አንድ ሰዓት የፈጀውን ውይይት እንደ ምንም ብዬ በትዕግስት ተመለከትኩት። ነገር ግን ከተለመደው ውሸትና ሃሜት የተለየ ነገር አላገኘሁም። እንደገና ሁለተኛውን ክፍል በመመልከት ተጨማሪ 45 ደቂቃ አጠፋሁ። አሁንም አዲስ ነገር የለም። ሰዓቴን እንዲህ በከንቱ ማባከኔ ቆጨኝና ውይይቱን ተመልከተው ያለኝ ወዳጄ ጋር ደወልኩ። ስልኩን እንዳነሳው “ካልጠፋ ነገር በውሸትና ሃሜት ግዜዬን ታባክናለህ?” አልኩት። ወዳጄ በአነጋገሬ እየሳቀ “ይሄን እኮ ነው የምልህ! የ100 ደቂቃ ወሬን በሁለት ቃል ቁጭ ማድረግ – ውሸትና ሃሜት – በቃ!” አለኝ።
በእርግጥ ውሸትና ሃሜት አሣፋሪ ብቻ ሳይሆን ፋይዳ-ቢስ ነው። በመሆኑም እንዲህ ያለ ነገር መናገር ቀርቶ መስማት በራሱ አያስፈልግም። ሆኖም ግን አንድ ሀገርና ህዝብ አስተዳድራለሁ የሚል ቡድን ውሸትን እንደ ድርጅታዊ መመሪያ ሲከተል፣ አመራሮቹ “እከሌ እንዲህ ሲል ሰምቼው፣ እንዲህ ሲያደርግ አይቼው” እያሉ ሚዲያ ላይ ሃሜትና አሉባልታ ሲያቦኩ ማየት ከማሳፈርም አልፎ ያሳስባል። እንደ አቶ ጌታቸው ረዳ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች ውሸትን በመደጋገም እውነት ለማድረግ ሲጥሩ፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በሚወሰንበት የሥራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ በአካል ተገኝተው ከተሳተፊ በኋላ ለህዝቡ ሃሜትና አሉባልታ ይዘውለት ሲሄዱ ከመቼውም ግዜ በላይ ሊያሳስበን ይገባል።
በመሰረቱ እነዚህ ሰዎች ስልጣን ላይ የተቀመጡት በእውን የምናውቀውን እውነት እንዲክዱን ወይም ያልሰማነውን ሃሜት እንዲነግሩን አይደለም። ከዚያ ይልቅ በእለት ከእለት ህይወታችን የሚስተዋሉ ችግሮችን በመለየት መፍትሄ መስጠት፣ ለሀገርና ህዝብ ጠቃሚ የሆነ ለውጥና መሻሻል ማምጣት ነው። ህወሓቶች ግን በተለመደ ውሸትና ሃሜት አማካኝነት ስልጣናቸውን ለመጨመር፣ እድሜያቸውን ለማራዘም የሚታትሩ ናቸው። እንደ ጌታቸው ረዳ ያሉት ደግሞ ሚዲያ ላይ ወጥተው ሲናገሩ ለእነሱ አፍረን የተውነውን ጉዳይ ያስታውሱናል። በውሸትና አሉባልታ የሌሎችን ስም ለማጥፋት ሲጀምሩ ግን አፍረን የደበቅነውን እውነት ለማውጣት እንገደዳለን። “አካፋን ‘አካፋ’ ካላሉት ማንኪያ ነኝ ብሎ ይፈተፍታል” እንደሚባለው ሁሉ እንደ አቶ ጌታቸው ረዳ ያለን ሌባና ሀገር ሺያጭ በሆነው ልክ ካልነገሩት የሀገር መካሪና ተቆርቋሪ መስሎ ይመጣል።
አቶ ጌታቸው ረዳ “ኢትዮጵያ ለውጪ ባለሃብቶች ለቅርጫ የቀረበች ሀገር ሁናለች” ያለው እንደ ኢትዮቴሌኮምና አየር መንገድ ያሉ የመንግስት ልማት ድርጅቶች ወደ ግል ሊዘዋወሩ መሆኑን መነሻ በማድረግ ነው። በአንድ በኩል የኢትዮጵያ መንግስት በጉዳዩ ዙሪያ ተገቢ ቅድመ-ዝግጅትና ቁጥጥር ማድረግ አለበት። በሌላ በኩል የህወሓት ባለስልጣናት ደግሞ እነዚህ ድርጅቶች በሽያጭ ቀርቶ በነፃ ለጠላት ቢሰጡ እንኳን አንዲት ቃል የመናገር ሞራል የላቸውም። ምክንያቱም እነሱ ስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት በእነዚህ ድርጅቶች ላይ ምን ሲሰሩ እንደነበር ጠንቅቀን እናውቃለን።
አቶ ጌታቸው ረዳ ኢትዮቴሌኮም ሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ግል እንዳይዛወሩ የሚፈልግበት መሰረታዊ ምክንያት ለሀገርና ህዝብ ጥቅም ሳይሆን በእነዚህ ድርጅቶች አማካኝነት የሚፈፅመው ዘረፋና ማጭበርበር እንዳይቋረጥ ወይም እንዳይጋለጥ በመስጋት ነው። ለምሳሌ አቶ ጌታቸው የፍትህና ህግ ምርምር ኢንስቲቱዩት ዋና ዳይሬክተር በነበረበት ወቅት ይጠቀምበት የነበረው የመስመር ስልክ አንድ አመት ባልሞላ ግዜ ውስጥ 1,172,409 ብር ወጪ አስወጥቷል። ይሄ ሁሉ ብር ከመንግስት ካዝና ወጪ ሆኖ የተከፈለው በ2010 ዓ.ም ነው። አሁን ባለው ያልተገደበ የድምፅና ኢንተርኔት ጥቅል ዋጋ ቢሰላ የአንድ ስልክ አመታዊ ወጪ ከ50 ሺህ ብር አይበልጥም። ከዚህ አንፃር አቶ ጌታቸው ረዳ ሲጠቀምበት የነበረው ስልክ ቁጥር 0945402516 በአንድ አመት ውስጥ ያስወጣው ወጪ 23ሺህ እጥፍ ይበልጣል።
የቴሌኮም ባለሞያዎች “አንድ ስልክ እንዴት ይህን ያህል ወጪ ሊያስወጣ ይችላል?” በሚል አቶ ጌታቸው ረዳ አዘውትሮ የሚደውልባቸውን ስልኮች በመለየት ጉዳዩን ለማጣራት ጥረት አድርገው ነበር። በዚህ መሰረት አቶ ጌታቸው አዘውትሮ የሚደውለው ወደ ውጪ ሀገር ሲሆን በተደጋጋሚ ከደወለባቸው ስልክ ቁጥሮች ውስጥ አብዛኞቹ በአሜሪካ የሚገኙ በቤት ሽያጭ ድለላ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ናቸው። አቶ ጌታቸው አሜሪካ ውስጥ የራሱ መኖሪያ ቤት እንዳለው ይታወቃል። ሆኖም ግን አሜሪካ የሚገኙ የቤት ደላላዎች ጋር በተደጋጋሚ ይደውላል። ከዚህ አንፃር አቶ ጌታቸው ከራሱ አልፎ ሰሌሎች ባለስለልጣናት ድለላ ወይም አገናኝ ሆኖ ይሰራ እንደነበር መገመት ይቻላል። “የስልኩን ኢንተርኔት አዘውትሮ የሚጠቀመው ለምን ጉዳይ ነው?” የሚለውን እዚህ ጋር መጥቀስ ስለሚያሳፍር ዝም ብሎ ማለፍ ይሻላል። ይሄ ለሥራ ተብሎ በተሰጠው አንድ የመስመር ስልክ 1.2 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስወጣ ሰውዬ እድሉን ቢያገኝ ኢትዮጵያን በቁሟ አይሸጣትም? ታዲያ ይሄ ሰው “ኢትዮጵያ ለውጪ ባለሃብቶች ለቅርጫ የቀረበች ሀገር ሁናለች” ሲል ትንሽ አያፍርም?
ኢትዮቴሌኮም ወደ ለውጪ ኩባኒያዎች ቢሸጥ እንደ ጌታቸው ያሉ ባለስልጣናት በአንድ ስልክ 1.2 ሚሊዮን ብር ወጪ ሊያስወጡ ይችላሉ። ሆኖም ግን ከዚህ ቀደም እንደሚያደርጉት ሁሉ የእያንዳንዱን ስልክ መስመር ጠልፈው እንደፈለጉ ለመሰለል አይመቻቸውም። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ተያይዞ ያለው ሁኔታ ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ነው። በእርግጥ “የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ግል ይዘዋወር ወይስ አይዘዋወር?” የሚለው ለብዙዎቻችን አከራካሪ ሊሆን ይችላል። ሆኖም ግን የብዙሃኑ ጥያቄ “ዝውውሩ ለሀገር ይጠቅማል ወይስ አይጠቅምም?” የሚል ነው። የህወሓቶች ጥያቄ ግን “ዝውውሩ ለማጭበርበርና ዘረፋ ይመቻል ወይስ አይመችም?” የሚል ነው። ለዚህ ደግሞ በድጋሜ አቶ ጌታቸው ረዳን እንደ ማሳያ መጥቀስ ይቻላል።
ከህወሓት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውስጥ እንደ ጌታቸው ረዳ ከመቀሌ – አዲስ አበባ የሚመላለስ ሰው የለም። ከወራት በፊት ቦሌ መድሄኒያለም አከባቢ በአጋጣሚ መንገድ ላይ በተገናኘንበት ወቅት በሳምንት ሁለት ቀን አዲስ አበባ እንደሚቆይ በራሱ ነግሮኛል። በእርግጥ ብዙዎቻችሁ እንደ አንድ የኢህአዴግ ሥራ አስፋፃሚ አባል በሣምንት ሁለቴ ለስራ የሚመላለስ ሊመስላችሁ ይችላል። እውነታው ግን ከዚህ የተለየ ነው። አቶ ጌታቸው ረዳ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል ከመቀሌ አዲስ አበባ የሚመላለሰው፣ እንዲሁም በቱርክ አየር መንገድ በኩል ወደ ውጪ ሀገር የሚጓዘው ከአቶ ጌታቸው አሰፋ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማስፈፀም ነው። ለዚህ ደግሞ አቶ ጌታቸው አሰፋ አስፈላጊውን የጉዞ ማስረጃ አዘጋጅቶለታል።
ጌታቸው ረዳ ሁለት ፓስፖርት አለው። አንደኛው እንደ ማንኛውም ሰው በራሱ ፎቶና አሻራ ያወጣው ፓስፖርት ነው። በሁለተኛው ፓስፖርት ላይ ከፎቶ ምስሉ በስተቀር ሙሉ መረጃው የሃሰት ነው። የእጁ ጣቶች እንደተቆረጡ አስመስሎ አሻራ ሳይሰጥ የተጭበረበረ ፓስፖርት አውጥቷል። ወደ ውጪ ሀገር ቀርቶ እዚሁ ሀገር ውስጥ ከመቀሌ – አዲስ አበባ በሳምንት ሁለቴ የሚመላለሰው በተጭበረበረ ስምና አድራሻ ነው። ለምሳሌ ባለፈው አመት ሐምሌና ነሃሴ ወር ላይ ከመቀሌ – አዲስ አበባ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል በርሯል። ሆኖም ግን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የመረጃ ቋት ውስጥ በተገኘው የመንገደኞች ስም ዝርዝር ውስጥ “ጌታቸው ረዳ ካህሣይ” የሚል ስም ያለው ተሳፋሪ የለም። በተጠቀሱት ሁለት ወራት ውስጥ በተደጋጋሚ ወደ አዲስ አበባ እንደመጣ አረጋግጬያለሁ። ነገር ግን የመጀመሪያ ስማቸው ጌታቸው የሆኑ ተሳፋሪዎች ከታች ያሉት ብቻ ናቸው።
ከላይ በተጠቀሰው መሰረት እ.አ.አ. ሐምሌ 09/2019 በቱርክ አየር መንገድ በኬኒያ ናይሮቢ አድርጎ ወደ ግብፅ ካይሮ እንደበረረ ይታወቃል። ሆኖም ግን አንዳቸውም ውስጥ ጌታቸው ረዳ ካህሳይ የሚል ስም ያለው ተሳፋሪ የለም። ምክንያቱም በሀገር ወይስጥ ሆነ በውጪ በረራ ላይ የሚጠቀመው ከላይ የተጠቀሰውን የተጭበረበረ ፓስፖርት ነው። ጌታቸው ረዳ የተጭበረበረ ፓስፖርት የሚጠቀምበት ምክንያት ደግሞ የጌታቸው አሰፋ ጉዳይ አስፈፃሚ ስለሆነ ነው። ትክክለኛ ሥራና ተግባሩ ከታወቀ ከተጠያቂነት ማምለጥ እንደማይችል ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀ የተጭበረበረ ሰነድ ይጓዛል።
በዚህ መሰረት አቶ ጌታቸው ረዳ ከመቀሌ አዲስ አበባ፣ እስከ ካይሮ ድረስ እየተጓዘ ከጌታቸው አሰፋ የተሰጠውን ትዕዛዝና መመሪያ ይፈፅማል። በእንዲህ ያለ ተግባር ላይ የተሰማራ ፖለቲካ አመራር ለትግራይ ህዝብ ከውሸትና ሃሜት በስተቀር ምንም ሊናገር አይችልም። ምክንያቱም ሥራና ተግባሩ በሀገር ክህደት ጭምር የሚያስጠይቀው ነው። ለምሳሌ ወደ አዲስ አበባ በመምጣት እዚህ ካሉ የጌታቸው አሰፋ ርዝራዦች ጋር ይገናኛል፣ በኢህአዴግ የሥራ አስፈፃሚ ስብሰባ ላይ በመገኘት ይሰልላል፣ ከአክራሪ ብሔርተኛ ቡድኖች አባላት ጋር በመገናኘት የፌደራሊስቶች ግንባርን ለመመስረት ያደራጃል፣ እንዲሁም ከግብፅ የደህንነት ኃላፊዎች ጋር በመመሳጠር በህዳሴው ግድብ ዙሪያ በሚደረገው የሦስትዮሽ ድርድር ላይ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ ለመሸጥ ይደራደራል። በዚህ መልኩ ሀገርን ለሽያጭ ያቀረበ ሰው ትግራይ ሚዲያ ሃውስ ላይ ቀርቦ “ኢትዮጵያ ለሽያጭ ቀርባለች” ብሎ ይለፍፋል።