ጥቅምት 2012
በልጅነታችን እስቲ ንካኝ! አስቲ ንካኝ! እንባባልና አንዱ ጀብደኛ ይነካል! ከዚያ በኋላ መሬት ጠባብ ትሆናለች! ድንጋይም ውድ ይሆናል! ደም ደምን መጥራት ይጀምራል! ያኔ አምቡላንስ የለ! ፔኒሲሊን የለ! በቆላ ቁስል እንቅልፍ ማጣት ነው!
አሁን በቴሌቪዥን የምናያቸው ጎረምሶች አጣና እየቆረጡ ባንድ ምት ብቻ ለማጋደም የተዘጋጁ ናቸው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛፍ ትከሉ እያለ ሲለፋ የነበረው ለነዚህ መሣሪያ ፋብሪካ እንዲሆን መስሏቸዋል! አላወቁም እንጂ ባለንበት ዘመንና በእኛ አካባቢ ጠመንጃ ርካሽ ነው፤ ከማዕድን ዘይት የሚገኘው ዶላር የታላላቆቹን የኢንዱስትሪ ባለጸጎች ሀብት የሚዘርፍ ነው፤ ሁለት ነገሮች አካባቢያችንን የጦር መሣሪያ ገበያ ያደርጉታል፤ አንደኛ የአረቦች የማይበርድ ጠበኛነት፣ ሁለተኛው የጦር መሣሪያው ተለዋዋጭነት ከቤንዚኑ ጋር ተደምሮ ዱላን ጊዜ ያለፈበት ያደርገዋል፤ ጊዜ ያለፈበት መሣሪያው ብቻ አይደለም፤ ዱላ የያዙትም ናቸው! ዱላው አጉል መዛቻ በመሆኑ ክላሺንኮፍን ይጠራል፤ ያኔ እንደዚህ ዱላ ይዞ ወይም ውዥግራ ይዞ በባቡር መንገድ ላይ ንጉሥ መሆን ያከትማል፤ ጀግና መሳዩ ሁሉ አይጥ ይሆናል!
ዛቻ በልጅነታችን የምንጫወትበት የጠብ ዘዴ ነበር፤ ጠቡም፣ መሣሪያውም፣ ስልቱም በተለወጠበት ጊዜ መቶ ዓመት ወደኋላ ሄዶ ከጫካ ዱላ የሚቆርጥ እዚያው ጫካ ውስጥ ቢቆይ ይሻለዋል፡፡
ዛቻ ለአሜሪካም አልበጀም፤