“የእነ ዶ/ር አብይ ስምምነት ለእስራት ዳረገን ” ነዋሪዎች || ታምሩ ገዳ

“የእነ ዶ/ር አብይ ስምምነት ለእስራት ዳረገን ” ነዋሪዎች || ታምሩ ገዳ

በቅርቡ የአለማቀፉ የሰላም ኖቤል ተሸላሚ የሆኑት ዶ/ር አብይ አህመድ በቅዳሚነት ከኢትዮ-ኤርትራ ጋር የነበረው ውጥረትን በማርገባቸው እንደሆነ ሸላሚው ድርጅት መግለጹ እሙን ነው።

ይሁን እንጂ የሰላም ሂደቱ ሆነ የውጥረቱ የመጀመሪያ ገፈት ቀማሾች የሆኑት የትግራይ እና የኤርትራ ህዝቦች መካከል እንዳንዶቹ በተለይ ደግሞ የድንበር አካባቢ ነዋሪዎች የሰላም ሂደቱ ምንም እንዳልፈየደላቸው ይልቁንም ለእስራት መዳረጋቸውን አምርረው በመናገር ላይ ይገኛሉ።

አጃንስ ፍርራንስ ፕሬስ(ኤ ኤፍ ፒ)ሰሞኑን ትግራይ ውስጥ ያነጋገራቸው ወ/ሮ ዛይድ አረጋዊ የዶ/ር አብይ አህመድ የዘንድሮው የአለም ሎሬት ኖቤል ተሸላሚነትን ሲሰሙ”ከአምስት ወራት በፊት ለአንድ ኤርትራዊ ነጋዴ እንጨት ለማድረስ ወደ ኤርትራ በመጓዝ ላይ ሳለ ያለአንዳች ምክንያት በኤርትራ የጸጥታ ኃይሎች ወደ እስር ቤት የተወረወረው ወንድሜ አለም አረጋዊ ነበር ከአይኔ ላይ የተደቀነብኝ”።በማለት በሁለቱ አገራት መካከል አለ የሚባለው የሁለትዬሽ ግብይት ወንድማቸውን ዋጋ እንዳስከፈለው ወ/ሮ ዛይድ አምርረው ተናግረዋል።

የወ/ሮ ዛይድ ወንድምን የመሳሰሉ ከደርዘን በላይ የትግራይ ተወላጆች የተለያዩ የኮንስትራክሽን እቃዎችን ፣ሩዝ ፣የታሸገ ውሃ…ወዘተ ወደ ኤርትራ በመውሰድ እና ለመሸጥ ሲሞክሩ በኤርትራ የጸጥታ ኃይሎች ተይዘው ለእስራት እና ለድብደባ መዳረጋቸውን የሚገልጹ መረጃዎች እንደደረሳቸው አቶ ዮሴፍ ምስጋና የተባሉ የአካባቢው ሹም ለ ኤ ኤፍ ፒ ተናግረዋል ።

እንደ ወ/ሮ ዛይድ እምነት በዶ/ር አብይ አህመድ እና በአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነት ዋንኛ አላማው የሁለቱ ህዝቦችን ነጻ እንቅስቃሴን ለማቀላጠፍ እንጂ በድን በር አካባቢ ላሉ ነዋሪዎች ሰቆቃቸውን ለመጨመር ባልሆነ ነበር ባይ ናቸው። ለዚህም ይመስላል “በሁለቱም ድንበሮች ላይ ነጻ የሰዎች እና የሸቀጦች ዝውውር ከሌለ የሰላም ስምምነቱ መፈራረም ፋይዳው የቱ ላይ ነው?”ሲሉ ወ/ሮ ዛይድ ይጠይቃሉ።

ዶ/ር አብይ የኖቤል ሽልማቱን ከማግኘታቸው ከአንድ ቀን በፊት አስራ ሶስት የትግራይ ልጆች በኤርትራ የጸጥታ ኃይሎች ተይዘው ወደ እስር ቤት እንዲገቡ ተደርገዋል፣ሁለቱ አሁንም በእስር ላይ ናቸው ተብሏል።በኢትዬጵያ የስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ ያሚገኘው አህመድ ያያ አብዲ እምነት በኢትዮጰያ እና በኤርትራ ገዢዎች መካከል የተደረገው የሰላም ስምምነት ምንም አይነት ብሩህ ተስፋ እንዳላመጣለት ነገሩ ሁሉ ” ላም አለኝ በሰማይ…”አይነት እንደሆነበት ተናግሯል።

ከሳምንታት በፊት ወደ በትግራይ ከሚገኘው የስደተኞች ጣቢያ የገባው ሌላኛው ኤርትራዊው ስብአት አብ አብረሃ እንዲሁ “ጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ እና ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ የተፈራረሙት የሰላም ስምምነትን ተከትሎ ዶ/ር አብይ የተሸለሙት ሽልማት ለእኔ ያመጣልኝ አንዳችም ነገር የለም” ሲል ቅሬታውን ገልጿል።

ሁለቱ አገራትን የሚያገናኙት ድንበሮች ዳግም የተዘጉ ሲሆን የእርቀ ሰላም ሂደቱን ተከትሎ “ከንግድ ጋር በተያያዘ” በኤርትራ የጸጥታ ኃይሎች ታስረዋል፣የሰብአዊ መብት ጥሰትም ገጥሟቸዋል ስለ ተባሉት ኢትዮጵያዊያን የትግራይ ተወላጆች ጉዳይ በተመለከተ የሁለቱ አገራት ሆኑ የክልሉ ባለስልጣናት እስከአሁን ድረስ ያሉት ነገር የለም። ከአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ ድንበር የሚዋሰኑት ኢትዮጵያ እና ኤርትራን የድንበር ማካለሉ ሂደት ወደፊት ብርቱ ፈተና ሊገጥመው እንደሚችል ተንታኞች ይናገራሉ።

ሰሞኑን በአአዲስ አበባ እና በተለያዩ የኦሮሚያ ከተሞች ተነስቶ በነበረው ተቃውሞ እና ስር አት አልበኝነት ሳቢያ ከሰባ በላይ ዜጎች ህይወት ከመቀጠፉ ቀደም ብሎ ዶ/ር አብይ “ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ በመቀሌ ጎዳናዎች ላይ በነጻ መሄድን ይሻሉ” በማለት ሰለ እርቀ ሰላሙ መጠናከር አስፈላጊነት መግለጻቸው አይዘነጋም። የድንበር ማካለሉ

LEAVE A REPLY