በሁሉም የኦሮሚያ አከባቢዎች ለነፃነት ትግሉ ዉድ ዋጋ ተከፍሏል። ከቤጊ እስከ ጭናቅሰን እና ከሞያሌ እስከ ሰላሌ ወጣቶች እና አዋቂዎች በቆራጥነት ታግሏል። የአምቦ ግን ከሁሉም ይለያል። ጀገናዉ የአምቦ ህዝብ በተማሪዎች እንቅስቃሴ ጀምሮ ለነፃነት ሲል ልጆቹን ገብሯል። በተለይ ደግሞ ወያኔ ከመንገሱ በፊት ጀምሮ እስከወደቀበት ጊዜ ድረስ ፊት ለፊት ሲጋፈጠዉ ኖሯል። በአጭሩ ትንሿ አምቦ ላለፉት በርካታ ዓመታት የታላቁ የኦሮሞ ህዝብ የትግል ማዕከል እንደነበረች አለም ያዉቃል። ኦሮሞ ለወንድሞቹ ያለዉ አክብሮት እና ፍቅርም ይገለፅባታል!
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ ከአምቦ ህዝብ ጋር ታሪካዊ ሊባል የሚችል ግንኙነት አላቸዉ። በ2009 ነገሮች በከረሩ ጊዜ ዶር አብይ ከአምቦ ህዝብ ጋር ስለነፃነት ትግሉ አቅጣጫ መክሯል። ከህዝቡም ምርቃት እና ምክር ተቀብሎ ወያኔን ለማሸነፍ ቃል ገብቶ ተመልሷል። ከድል በኋላ ደግሞ አምቦ የኦሮሞ ኒዉዮርክ ወይም የድል ምልክት እንደሆነች ተናግሯል። አምቦ ትለማ ዘንድም ባለሀብቶችን ከማስተባበር ባሻገር የእጃቸዉን ሰዓት በአምስት ሚሊየን ብር ሽጠዉ ለግሷል። ተመላልሶም ጠይቋታል።
የአብይና የአምቦ ግንኙነት ያልተመቻቸዉ ወገኖች አሉ። እነዝህ በኦሮሞ ትግል ስም ተከሽነዉ በኦሮሞ ልጆች ደም የሚነግዱ ናቸዉ። ኦሮሞ ነፃነት እና ሠላም ሲያገኝ ንግዳቸዉ ስለሚመክን ያለምክንያት ሰላሙን ይነሳሉ። ከወንድሞቹም ጋር ሊያጋጩት ጥላቻን ይሰብካሉ። ከምንም በላይ ግን ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይን ከኦሮሞ በመነጠል ህዝቡን በለቅሶ ፖለቲካ ዉስጥ ለማቆየት ይፈልጋሉ። ይህ የሚሳካዉ ደግሞ አምቦ ላይ ደም በማፍሰስ መሆኑን አምኗል። በአንድ አመት ተኩል ጊዜ ዉስጥ አምቦን ለመበጥበጥ ከአስር ያላነሱ ሙከራዎችን አድርጓል። ነገር ግን የአምቦ ህዝብ መቸ ምን ማድረግ እንዳለበት ስለሚያዉቅ ሙከራቸዉ ከሽፏል። ሲያቅታቸዉ በወያኔ ባጀት ከሌላ ቦታ ሰዉ አምጥተዉ አምቦ ላይ ያሰፍራሉ። ከፖሊስ አባላትም ቅጥረኛ ይመለምላሉ። ዝግጅት ጨርሰዉ ጊዜ ሲጠብቁ ጥቅምት 12/2012 ግርግር ያገኛሉ። በግርግሩ መሀል ቅጥረኛ ፖሊሶቹ ተኩሰዉ ሰዉ ይገላሉ። የፈለጉትን ያህል ባይሆንም የንፁሃንን ደም አፍሷል። ሌሎች ጉዳቶችም ደርሷል። ከሁለት ቀናት በፊት ደግሞ ተጨማሪ ደም በማፍሰስ የዶር አብይን ስም ለማበላሸት ሰፋሪዎቹ ሠልፍ አድርገዉ የአብይን መንግስት በማዉገዝ በድል ማግስት የሸፈተዉን መሮን አወድሷል። አሁን ላይ ሁሉም ነገር ግልፅ ሆኗል። ሦስት ፖሊሶች እና ሌሎች የወንጀሉ ተሳታፊዎች በቁጥጥር ስር ዉሏል። የአምቦ ህዝብ ሴራዉ እንደማይመለከተዉ ተናግሯል። የሴራዉ ጠንሳሾችም ተለይቶ ታዉቋል! እዉነት ይቀጥናል እንጂ መች ይበጠሳል? አብይን ከኦሮሞ ለመነጠል ለስድስት ወራት ሲሰራ የነበረዉ የአምቦ የፖለቲካ ሴራ ከ ሀ እስከ ፐ ይህን ይመስላል። በመጨረሻም ሴረኞቹን ለትልቅ ኪሳራ ጥሎ ከሽፏል! እዉነት ግን እያሸነፈ ይሄዳል።
ሠላም ዋሉ!