ሁሌ ገንዘብ እንደልብ ቢኖርም በሰማይ መንገድ የለም! || ታዬ ደንደአ

ሁሌ ገንዘብ እንደልብ ቢኖርም በሰማይ መንገድ የለም! || ታዬ ደንደአ

ለህወሀት ስርቆት እንጂ ብልፅግና አይሆንለት። ሌብነት ስራ መሆኑን በ”ታላቁ” መሪ ተምሯል። ሌጋሲዉን ለማስቀጠልም ቃል ገብቷል!

ብልፅግና እንዳይወለድ ህወሀት ብዙ ሴራ ሸርቧል። በብሔር፣ በሀይማኖት እና በትምህርት ቤት አመፅ ቀስቅሶ ህይወት እንዲጠፋና ንብረት እንዲወድም አድርጓል። በሁሉም አይነት ሚዲያ አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ ነፍቶ አስነፍቷል። አሁን ደግም ሀገር አቀፍ አመፅ ለማስነሳት ከአፍንጫዉ በታች መቃብር ዉስጥ ሆኖ ይንደፋደፋል። ተደጋፊ ደጋፊዎቹም የተመደበችዉን አራት መቶ ሚሊዬን ብር ለመካፈል ዳፋ-ቀና ማለት ጀምሯል። አንዳንዱም በህወሀት ድጋፍ አራት ኪሎ ለመግባት ቀቢፀ-ተስፋ ሰንቋል።

እስኪ ሰዉ እንዴት በዝህ ወቅት እንደዚህ ይሆናል? ህወሀት ከነበረበት ማማ ሲወርድ መቀበል አቅቶት ቀልቡን ቢስት እዉነት ይኖረዋል። የሚያሳዝነዉ ለሬሳ የሚላላኩ “ምሁራን” እና ፓርቲዎች መኖራቸዉ ነዉ። ለማንኛዉም ብልፅግና አሸንፎ ተወልዷል። አሁንም አሸንፎ ያድጋል።

የኢትዮጵያን ህብረብሔራዊ አንድነት፣ የህዝቦቿን ነፃነት፣ እኩልነትና ብልፅግናም ያረጋግጣል። ለምስራቅ አፍሪካ ሰላም እና ልማትም ዋስትና ይሆናል! ልፋ ያለዉ ግን በከንቱ ይለፋል!

ሁሌ ገንዘብ እንደልብ ቢኖርም
በሰማይ መንገድ የለም!

LEAVE A REPLY