የዚህ አመት የአለም ሰላም ኖቬል ሽልማት ተሸላሚ የሆኑት የኢትዮጵያው ጠ/ሚ/ር ዶ/ር አብይ አህመድ ሽልማቱ በሚሰጥበት በመጪው ማክሰኞ በኖሮዎይ መዲና ኦስሎ ሲገኙ ለጋዜጠኞች ምንም አይነት መግለጫ እንደማይሰጡ እና ጥያቄም እንደማይቀበሉ ተገለጸ።
ዜና አገልግሎት ሮይተርስ እንደዘገበው በእየአመቱ በሚሰጠው ያኖቤል ሽልማት ዋዜማ ላይ እድለኛ ተሻላሚዎች ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጡበት መድረክ የተለመደ ቢሆንም ዶ/ር አብይ ግን የኖሮዌይ ጠ/ሚ/ር ኤሪና ሶልብርግን እና ንጉስ ሃራልድ አምስትኛውን ከማነጋገር እና ፓርላማውን ከመጎብኘት ውጪ ለጋዜጠኞች ምንም አይነት መግለጫ ለመስጠ እንደማይፈልጉ እና በሽልማቱ ማእከል ውስጥ በእየአመቱ ታዳጊ ህጻናቶች የሚያከናውኑት ሰላም ተኮር ክብረ በዓልም ላይ እንደማይታደሙ ለኖቤል ሽልማት አዘጋጅ ኮሚቴው አሳውቀዋል።
ቀደም ባሉት የሰላም ኖቬል ሽልማት አሰጣጦች ዙሪያ በሚስጥራዊነቱ የሚታወቀው የኖቬል ሽልማት ሰጪው ድርጅት ዋና ጸሐፊ የሆኑት ኦልቭ ኒጆልስታንድ በበኩላቸው ” ሀሳብን በነጻ የመግለጽ መብት መከበር እና የነጻ ፕሬስ ማበብ ለኖቬል ሽልማቱ ዋንኛ ሚና ተጨዋች እና ቁልፍ አካል መሆኑን ስለ ምናምን ፣ ዶ/ር አብይ በኖርዌይ ቆይታቸው ከጋዜጠኞች ለሚወረወሩ ጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡ እንደምንሻ አቋማችንን በግልጽ አሳውቀናል”ብለዋል።
በስልጣን ላይ ሳሉ የኖቤል ሽልማት ተቀቀብለው፣ ነገር ግን ለጋዜጠኞች መግለጫ ካልሰጡ የአገር መሪዌች መካከል ስልጣን በያዙ ማግስት ሽልማቱን የተቀበሉት እና አሰጣጡም በወቅቱ ብዙ ውዝግብ ያስነሳው የቀድሞው የአሜሪካ ፕ/ት ባራክ ኦባማ ዋንኛ ተጠቃሽ ናቸው።
የጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ ቃል አቀባይት የሆኑት ብሌኔ ስዩም ስለ ሁኔታው ከሮይተርስ ተጠይቀው በሰጡት መልስ “በአገር ውስጥ ካለባቸው የተደራረቡ፣ትኩረት እና ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች የተነሳ ጠ/ሚ/ሩ አብይ በተባለው የፕሬስ ኮንፈረስ ቀን በኦስሎ ሊገኙ አይችሉም፣ዶ/ር አብይ በሽልማቱን በተመለከተ ከሽልማት ሰጪው ድርጅት ጋር በተደረሰው ስምምነት መሰረት ቁልፍ እና ቅድሚያ በሚሰጠው ፕሮግራም በሆነው የሸላሚውን ድርጅት ግብዣን በማክበር በሽልማት አሰጣጡ ላይ ብቻ እንደሚገኙ አሳውቀናል ” ሲሉ ተናግረዋል።
ስልጣን ከያዙ ወደ ሁለት አመት እየተቃረቡ የሚገኙት ዶ/ር አብይ አህመድ የተለያዩ አህጉራዉ እና አካባቢያዊ ሽልማቶችን የተሸለሙ ሲሆን ሽልማቶቹን በአብዛኛው በግንባር ተገኝተው ከመቀበል በተወካዮቻቸው አማካኝነት እንደደረሷቸው የፋዊ የሆኑ መረጃዎች ይገልጻሉ።