የሱዳን ሽግግር መንግስት የገና በዓልን በኦፊሴላዊ አጸደቀ || ታምሩ ገዳ

የሱዳን ሽግግር መንግስት የገና በዓልን በኦፊሴላዊ አጸደቀ || ታምሩ ገዳ

በህዝባዊ አመጻ እና ተቃውሞ ባለፈው ሚያዚያ 2019 እኤእ ከስልጣናቸው የተባረሩት በቅድሞው የሱዳን ፕ/ት አልባሸር ዘመን እውቅና ተነፍጎት የቆየው በክርስቲያን አማኞች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ የሚሰጠው የገና ክብረ በዓል እውቅና ተሰጠው።

በተለይ የሱዳን አካል የነበረችው እና አብዛኛው ህዝቧ የክርስትና እምነት ተከታይ የሆነው ደ /ሱዳን ከካርቱም መንግስት ከተገነጠለች እኤአ 2011 ወዲህ አናሳ በሆኑት በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰው ግፍ እና መከራ የበረታ ነበር።

ለሁሉም ጊዜ አለው እንዲሉ ሱዳንን ለሰላሳ አመታት የገዙት አልባ ሽር ተወግደው ፍርዳቸውን በሚጠባበቁበት በዚህ ወሳኝ ወቅት አገሪቱን በመምራት ላይ ያሚገኘው የወታደራዊ እና የሲቪል ጥምረት የሆነው የሽግግር መንግስቱ የእምነት ነጻነት እንዲከበር መንገድ በመጥረጉ በምእራባዊያኖች ዘንድ የተከበረው የገና በዓልን ያለመሸማቀቅ ለማክበር ወደ አደባብይ የወጡ ሱዳናዊያን ክርስቲያኖች “እየሱስ ክርስቶስን እወዳለሁ” የሚል የካኒቴራ ቲ ሸርት አድርገው ወደ አዳባባይ የወጡ ሱዳናዊያኖች ከህዝበ ሙስሊሙ ሳይቀር ሞቅ ያለ ድጋፍ እንደተቸራቸው አሶሼትድ ፕሬስ ከመዲናይቱ ካርቱም ዘግቧል።

ወደ ጎዳና ከወጡት የክርስትና እምነት ተከታዮች መካከል አንዱ የሆነው ኢዛዲር ኢብራሄም” አዱሱ የሱዳን የሽግግር መንግሰት የእምነት ነጻነታችንን በአደባባይ እንድተገብር በመፍቀዱ በጣም ደስተኛ ነኝ፣ሀሌ ሉያ!፣ ሀሌ ሉያ !”ሲል ደስታውን ገልጿል።

ኖሃ ማኑል የተባሉ የሀይማኖት አባት በበኩላቸው”ትላንት ፈጣሪን በማምለካችን ብቻ እንደ ወንጀለኛ እንቆጠር ነበር ፣ዛሬ ግን ይኸው የታገደው የእምነት ነጻነታችን ተመለሰልን ፣የገና በዓላችንንም በአደባባይ ዳግም ለማክበር በቃን”ብለዋል።

የጌታ እየሱስ ክርስቶስ መወለድን በስፋት ከሚተርኩት የመጻህፍት ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ ተጠቃሽ የሆኑት የሉቃስ እና የዮሐንስ ወንጌሎችን በበራሪ ወረቀት መልክ ሲያድሉ ከነበሩት ወጣት ሱዳናዊያን ወንዶች እና ሴቶች ጋር በአጋጣሚ የተገናኘችው የእስልምና እምነት ተከታይዋ ናሀላ ሙስጠፋ “ምንም እንኳን በራሪ ወረቀቶቹን ወስጄ ለማንበብ ባልፈልግም፣ ያ ለሙስሊሞች ሳይቀር የማይመች አምባ ገነን ስርአት ተወግዶ ክርስቲያን ወገኖቼ ዛሬ እምነታቸውን እንዲህ በአደባባይ ሲገልጹ በማየቴ በጣም ደስተኛ ነኝ።” ብላለች።

ታህሳስ /ዲሰምበር 25 በሱዳን ውስጥ ኦፊሴላዊ የገና ክብረ በዓል ቀን ሆኖ በመታወጁ ለወትሮው ከሙስሊም ጎረቤቶቻቸው ጋር የረመዳን በአል እንጂ የገና በዓልን የማያከብሩት ሱዳናዊያን ክርስቲያኖች በዓሉን በጋራ በደስታ ማክበር ጀምረዋል፣ ክርስቲያኖች ለሙስሊሞች “ኢድ ሙባረክ” እንደሚሉ ሁሉ ሙስሊሜችም በፊናቸው “መልካም የገና በዓል ይሁንላችሁ” ሲሉ ተስተውለዋል። ቀደም ሲልም በአዲሱ የሽግግር ካቤኔት ውስጥ ሴት የክርስትና እምነት ተከታይ መቀላቀላቸው መንግስቱን በብዙዎች ዘንድ መልካም ተስፋ ተጥሎበታል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የክርስትና እና የእስልምና ሀይማኖቶች ቀደምት አገር በሆነችው በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሚታየው ዘር እና ሀይማኖት ተኮር ግጭቶችን የሚዘውሩ፣የሚያጋግሉ ፣ገጀራዎችን የሚያቀርቡ የጥፋት ሀይል ሆኑ፣ ለእነዚህ እኩይ አስተሳሰብ ለተጸናወታቸው ወገኖች ጀርባቸውን የሚሰጡ የዘመኑ ሹማምንቶችም ቢሆኑ ከጎጆ ወጪው የሱዳን መንግስት ብዙ የሚማሩት ነገሮች ስለመኖሩ አያጠያይቅም።

LEAVE A REPLY