|| ዶ/ር አማረ ተግባሩ ||
ዲሴምበር 3 በ 2:19 ከሰዓት 2019
በኣለፉት 40 ዓመታት የጻፍኳቸውን ጽሑፎች ለማሰባሰብ ስሞክር ኣንድ ትልቅ ከበሬታና ምስጋና ሊሰጣቸው የሚገባ ሰው ትዝ አሉኝ። እሳቸውም ዶ/ርኣበራ ሞላ ይባላሉ። የሚኖሩትም በሰሜን አሜሪካኮሎራዶ በሚባለው እስቴት ይመስለኛል። ምስጋናዬምአለ ምክንያት አይደለም። ወደ ኋላ ተመልሼ ከጽሑፎቼ መካከል ከመጥፋት ተርፈው ከያለበት የተገኙትን ሳገላብጥ በእጄ የጻፍኳቸውና በፎቶ ኮፒ እየተባዙ የተሰራጩት ቀለማቸው እየደበዘዝ ለመነበብ አስቸግረው አገኘኋቸው።
በእጅ መጻፉ ቀርቶ ኦሊቬቲ በሚባል የአማርኛው ፊደል ቅጥያ እየተደረገ በተቀረፀበት የጽሕፈት መኪና ራሴ ታይፕ እየመታሁ የጻፍኳቸውና በ70ዎቹና 80ዎቹ መጨረሻ ድረስበ የማተሚያ ቤቱ በነበሩት የሕትመት መሣሪያዎች ፊደሎቹ እየተለቀሙ ይታተሙና ተባዝተው ይሰራጩ ከነበሩትም መካከል የተገኙትም ወረቀቱ ከመንተቡየተነሳ በቀላሉ የሚነበቡ አልነበሩም። ልክ የዛሬ 25 ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ በዶ/ር ኣበራ ሞላ በተዘጋጀው ዘመናዊ የግዕዝ ሶፍትዌር ፕሮግራም እየታገዝኩ የጻፍኳቸውን ተመልሼ ስመለከት በወረቀት ከታተሙ በኋላ በዲስኬት save ከተደርጉም በኋላ ዲስኬትን ወደፍላሽ ዲስክና ኮምፒዩተር ለመገልበጥ የሚቻል በመሆኑ ጨርሶ ከመጥፋትና እንደገና እጅግ ዘመናዊ በሆነው እኚሁ ሰው ባሻሻሉት የግዕዝ ሶፍትዌርፕሮግራም አብዛኛውን መልሶ ለማንበብና የጎደሉትንም ለመሙላት አስችሎኛል።
የግዕዙን ፊደል ማዘመን ማለት ለኔም ሆነ በቋንቋው ተጠቃሚ ለሆነው ትውልድ ምን ያህል ሥራን እንዳቃለለ መገንዘብ አያዳግትም። ይህንን የፈጠራ ሥራየጀመሩትንና እስካሁንም ድረስ ይበልጥ በማበልጸግ በመድከም ላይ ያሉትን ሁሉ ማመስገን እወዳለሁ።
የተለየ ምስጋናዬ ግን ለዶ/ር አበራ ሞላ ነው።ምክንያቱም ልክ የዛሬ 25 ዓመት በአንድ ወዳጄ በኩል እሳቸው develop ያደረጉትን Geez software program በማግኘት የመጀመሪያዋን መጽሐፌን ለመጻፍ በመቻሌ ነው። የእዚያን ዘመን Geez software program እና ዛሬ በዶ/ር ኣበራም ሆነ ከእሱ በኋላ በእሱ ፈርቀዳጅነት የእሱን ፈጠራና ግኝት ተንተርሰውናተ ደግፈው በተነሱ ሌሎች innovated ሆነው በገበያና በአገልግሎት ላይ የዋሉት መካከል ትልቅ እመርታመኖሩ አይካድም። ይህንን የመሰለው innovativeness ከጊዜ ወደ ጊዜ እየረቀቀ በመሄዱ ቋንቋውን በማበልጸግና በዋነኝነት ከሚነገሩ ታላላቅ ቋንቋዎችጎን ለጎን ካንዱ ወዳንዱ ለመተርጎም በማያስቸግር መንገድ እየተቀያየረና እየተዳበለ በሶሽያል ሚዲያው ጭምር (compatible) የማገልገል ብቃት እንዲኖረው ለማድረግ ተችሏል። ይህም ቋንቋውን ከግንኙነትና ከመግባቢያ መሣሪያነቱ (instrumentality) ባሻገር ለእኛለቋንቋው ተናጋሪዎችና ለተጠቃሚዎቹም ጭምርsymbolic ትርጉም ኖርት ይህንን በመሰለው የአገርትልቅ ቅርስና ለትውልድ ታሪክ በማቆየትና በማበልጸግ የተሠራው የፈጠራ ሥራ የጋራ ኩራት እንዲዳብር እንዳደረገ አያጠራጥርም። ስለዚህም ከ25 ዓመትበኋላ ዶ/ር አበራ ሞላ የግዕዙ ፊደል ለኮምፕዩተር እንዲመች አድርገው በማዘመን እሳቸው ምክንያትሆነውኝ ከተጠቃሚዎቹ አንዱ ለመሆን ዕድሉን በማግኘቴ ይህችን አጭር መጣጥፍ በመጫር ለኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ዶክተር ኣበራ ሞላ ክብርናምስጋናዬን በይፋ በአደባባይ ለማድረስ እሻለሁ።”
የሳይንቲስቱ ዶክተር አበራ ሞላ በረከቶችናቱርፋቶች አጭር ማስታወሻ።
ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት የሰንዳፋ ተወላጅ ዶክተርአበራ ሞላ
ቅድሚያ ግንባር ቀደም የተመራጭነት ክብርና ማዕረግ ይገባቸዋል። የኢትዮጵያ የጥንት ስልጣኔ የሆንውንየኢትዮጵያ ፊደልን ከዛሬው የ21ኛው ክፍለ ዘመንየሳይንስና ቴክኖሎጂ የዓለም ስልጣኔ ጋር እኩል እንዲራመድ በዓለም አቀፍ ደርጃ ያዘመኑና ለሁሉም የኢትዮጽያ ቋንቋዎች በሙሉ በኮምፒተርና በእጅ ሰልኮቻችን እንድንጠቀም ያስቻሉና የዩኒኮድ/ዩኒበርሳል ኮድ/ያደረጉ የሳይንስ ጀግናና አርበኛ ናቸው።
እንዲሁም የዶክተርን የፈጠራ ሳይንስ ውጤት እንደአንድ ተቀዳሚ መስፈርት በመውሰድ
1/አማርኛ ቋንቋ በዋሽንግቶንና ዙሪያው የስራ ቋንቋ እንዲሆን አስችሏል
2/የአፍሪካ ህብረትም የስራ ቋንቋ ሆኗል
3/በእስራኤልም ታጭቷል
4/በጃማይካም /በራስ ተፈሪያን ጥያቄና ግፊት ለመንግስት ዘርፍ ቀርቧል
5/በቲሪንዳድና ቶቤጎ ከ75 በላይ አድባራት እየተገለገሉበት
በመሆኑ ታሳቢ እጩ እየሆ ነው
6/ ለአለም አቀፍ እግር ኳስ ስፖርት DSTV የስራ ቋንቋ ሆኗል።
በእነዚህና ሌሎች ለምሳሌ የአክሱም ሃውልት ማስመለስ የመሳሰሉት ሁሉ የላቀ ባለ ሚና በመሆናቸው እውቅናና ተጓዳኝ አቻ የማክበር ማዕረግ ተሰጥቷቸው ሊመረጡ ይገባል።