ጃዋር መሐመድ ኦፌኮ ጋር መቀላቀሉን ዶ/ር መረራ ጉዲና አረገገጡ

ጃዋር መሐመድ ኦፌኮ ጋር መቀላቀሉን ዶ/ር መረራ ጉዲና አረገገጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኦ.ኤም.ኤን ዋና ስራስኪያጅ ጃዋር መሐመድ ከጥቂት ሳምንታት በፊት በሰሜን አሜሪካ ባደረጋቸው ህዝባዊ ስብሰባዎች ወደ ፓርቲ ተቀላቅሎ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር ተናግሮ ነበር።

ዛሬ በይፋ በዶክተር መረራ ጉዲና የሚመራው ኤፌኮ አባል መሆኑን ፓርቲው ይፋ አድርጓል።

ዶክተር መረራ አንድ ሰው ወንጀለኛ እስካልሆነ ድረስ አባል መሆን ይቻላል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በርካቶች ጃዋር ሞሐመድ ባለፈው ወር ጠባቂዎቼ
ሊነሱ ነው በሚል በፌስ ቡክ ገጽ ላይ ባሰፈረው መልእክት የተነሳሱ ወጣቶች በቀሰቀሱት ግጭት ለሞቱት 86 ሰዎች ተጠያቂ ያደርጉታል።

ጃዋር መሃመድን ወደ ፖለቲካ መግባት በኦሮሚያ ወጣቶች ዘንድ ያለውን ተሰሚነት ተጠቅሞ ወደ ስልጣን ማማ ለማምጣት ቀላል ይደረግለታል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች አሉ።

በአንጻሩ የጀዋር ውሳኔ የተሳሳተ እና ከአሁን በኋላ ልቅ የነበረውን ነጸነቱን በተወሰነ መልኩ ሊያሳጣው እንደሚችል ያላገናዘበ ነው በማለት አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ነገ የሰጡ በሰሜን አሜሪካ የሚኖሩ አንድ አክቲቪስት ጃዋር ከዚህ በኋላ እንደፈለገው ሊሆን አይችልም፤ ተሰሚነቱም በፓርቲው የታጠረ ይሆናል፤ ማለታቸውም በተጨማሪ ውሳኔው ዋጋ ያስከፍለዋል ብለዋል።

LEAVE A REPLY