የሀያ ሰባት አመቱ ቸኮለ መንበሩ እንደማንኛውም ወጣት ኢትዮጵያዊ ኑሮን አሸንፎ ፣ከትልቅ የስኬት ደረጃ ላይ በመድረስ ቤተሰቡን እና አገሩን በመጥቀም ፣በመልካም ስም ያማስጠራት ምኞት ነበረው።
ቢቢሲ በአማራ ክልል፣ባህርዳር ውስጥ ሰሞኑን ያነጋገረው ቸኮለ ወላጅ አባቱን በጨቅላ እድሜው በሞት ቢነጠቅም፣ ከአያቶቹ እና በእናቱ እቅፍ ውስጥ በመሆን ትምህርት ሊማር ቢወጥንም ዘመዶቹ በቂ ቅሬት ባለማፍራታቸው የተነሳ እራሱን ለመለወጥ ስል ከአጎቱ ቤት እየኖረ በጎችን በመጠበቅ ውድ ትምህርት ቤት ገብቶ ለመማር ይቋምጣል።
የትምህርት ቤት የመግባት ህልሙን በአያቶቹ ጣልቃ ገብነት ወረታ ከተማ ውስጥ የጀመረው ታዳጊው ቸኮለ ግስጋሴው ከሁለተኛ ክፍል ሊዘል አልቻላም።ሁኔታውንም ሲረዳ ጫማ ጠራጊ ጓደኛው አማካኝነት የጫማ መጥረጉን ስራ ስራዬ ብሎ የተያያዘው ቸኮለ በትርፍ ጊዜው የእውቀት ገበያውን በምከናወን፣ እንደርሱ ከትንሽ ስራ ተነስተው ለ ዶክተርነት እና ለኢንጂነርነት ለመሳሰሉት ከፍተኛ ደረጃ በደረሱ የአገሩ ልጆች ገድል በመጽናናት እጅግ አስቸጋሪ የህይወት ውጣ ውረዶችን በጽናት በመቋቋም ባለፈው 2013 እኤእ በባህር ዳር ዪኒቨርሰቲ በመግባት በትምህርት ቆይታው በወር የኪስ 200ብር($10 ወይም £8)በማግኘት በኬሚካል ኢንጂነሪንግ(Chemical Engineering )የትምህርት ከአምስት አመት ድካም እና ቆይታ በሁዋላ ለመመረቅ ችሏል።
“ኢትዮጵያ ለኢንጂነረኒግ ምሩቆች ምቹ ገበያ አላት የሚል ወሬን ተከትዮ ፣ በተመረቅኩ ማግስትም የስራ እድለኛ እና ደሞዝተኛ እሆናለሁ ብዬ ” ነበር የሚለው ምስኪኑ ቸኮለ ትምህርቱ ሊገባደድ ሲቃረብ ግን ያልጠበቀው ፍርሃት በውስጡ ገባ።እርሱም “ይህንን ሁሉ የህይወት ውጣ ውርድን በግሌ ጥረት እና በጓደኞቼ ድጋፍ ዘልቄ ስራ ባጣስ?” የሚል ነበረም።
የፈሩት ይደርሳል… እንዲሉ በተመርቀ ማግስት ስራ ለማፈላለግ ሲል ከትውልድ ቀየው 491 ኪሜ ደቡባዊ አቅጣጫ ፣አዲስ አበባ ውስጥ ለሶስት ወራት በስራ ፍለጋ ቢማስንም፣ሌላው ቀርቶ ለተማረበት እና ለተመረቀበት የስራ ዘርፍ የማይመጥን ስራ ቢያመለክትም” ወደፊት ደጎስ ያለ ደሞዝ እና ጥቅማጥቅም ሊጠይቀን ይችላል”የሚል ስጋት ያደረባቸው ባለሀብቶች እና የስራ ሀላፊዎች በእውቀቱ አይደለም በጉልበቱ እንኳን ሊቀጥሩት አለመፈለጋቸውን፣በ ፋብሪካ ውስጥ በቀን 29 ብር ( $1)ተቀጥሮ ለመስራት ቢሞክርም በህይወት በቀር ሁሉም ነገር ሰማይ ጥግ በደረሰባት አዲስ አበባ ውስጥ ኑሮን መቋቋም ባለመቻሉ ስራውን ለማቋረጥ መገደዱን ወጣቱ የኢንጂነሪግ ምሩቅ ቸኮለ መንበሩ አሳዛኙ ገጠመኙን ለቢቢሲ ዘጋቢ አካፍሏል።
ለስራ ፍለጋ ሲል ከባሕርዳር እስከ አ/አ ከዚያም እስከ ወልዲያ(ወሎ)የተጓዘው ወጣቱ ቸኮለ እድል ፊቷን ስታዞርበት ወደ ባሕር ዳር ከተማ በመመለስ በእውኑም ሆነ በህልሙ ያልጠበቀው እና ያላለመው ያ ከአመታት በፊት ጥሎት የ ሄደው የጫማ ጠረጋ ስራውን ዳግም ለመጀመር ተግዷል።
“ለትምህርት እና ለእውቀት ገበያ ያደረግኩት ውጣ ውረድ፣ በሽልማት ፈንታ ብዙ ዋጋ አስከፈለኝ፣ባልማር ኖሮ ዛሬ እንዲህ ባልተቆጨሁ ነበር ” የሚል መንፈስ በውስጡ ያደረበት ወጣቱ ኢንጂነር ቸኮለ በአሁኑ ወቅት በኢንጂነሪንግ ሙያው ሳይሆን የሰዎችን ጫማን በመጥረግ ላይ ተሰማርቶ የተመለከቱት በባህር ዳር ዩንቨርስቲ ውስጥ ለአምስት አመታት የእውቀት አባቶቹ የነበሩት መምህራኖቹ አንዳንዶቹ በአይናቸው የሚያዩትን ማመን አቅቷቸው በድንጋጤ ጥለውት እንደሚሄዱ፣እንዳንዶቹ በበኩላቸው ሞራል እንዳይሰበር ገንዘብ በመስጠት እንደሚያበረታቱት ፣የኮሌጅ ጓደኞቹ ጭምር ጫማቸው ሳይቆሽሽ እርሱን ለማበረታታት ሲሉ ብቻ ጫማቸውን እንዲያው ለአመሉ ቀለም በማስቀባት የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርጉለት ሳይገልጽ አላለፈም።
ወጣቱ የኢንጂነሪንግ ምሩቁ ቸኮለ ምንም እንኳን የቱንም ያህል ፈተናዎች ቢበረቱበት፣ ላለፊት ሶስት አመታት ፊቷን ያዞረችበት እድል ፈንታው አንድ ቀን ትታደገው ዘንድ ተስፋ በማድረግ በተለያዩ ጊዜያት በማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ የሚለጠፉ የተለያዩ ክፍት የስራ ማስታወቂያዎችን ከመቃኘት እና ከመሞከርም አልተቆጠበም።
ኢንጂነር ቸኮለ መንበሩ የመሳሰሉ የዚህ አለም ፈተናን እና መከራን ተጋፍጠው ከስኬት ማማ ላይ ለመድረስ ጥቂት ሲቀራቸው በተለያዩ እንከኖች ምክንያቶች ካለሙበት ሳይደርሱ መቅረታቸው እንደ ዜጋ እንደ ሰብአዊ ፍጡር ልብን በእጅጉ ይነካል።ኢንጂነር ቸኮለ የእውነተኛ እና ርሁረህ ኢትዬጵያኖችን እገዛ ከሚሹ ተተኪ ትውልድ እና ወገኖቻችንን መካከል አንዱ ለመሆኑ አሌ አይባልም።
ውድ ወገኖቼ :- ይህ የልጅነት ሆነ የወጣትነት ሕይወቱን ያላጣጣመው የነገው ተስፋ የሆነ ወገናችንን አቅሙ እና እድሉ ያለን ወገኖች ሀላፊነት በመውሰድ ” ጎ ፈንድሚ” (Gofundme)አማካኝነት ይሁን በቀጥታ ወንድማችን ኢንጂነር ቸኮለ መጠነኛ ስራ የሚያገኝበት እና የተሻለ ኑሮ የሚመራበት መንገድን ብንቀይስለት በፈጣሪ ዘንድ ትልቅ ብድር ማቆየት ሲሆን፣ ለእይምሯችንም ትልቅ ሰላም እና የመንፈስ እርካታ ነው።
በአካል ሳናውቀው አሳዛኙ እና የብዙዎቻችን ቅስም የሰብረው ይሄን ገጠመኝን ያደረሰን ቢቢሲም ቢሆን ” ለጫማ መጥረግ ስራ ዳግም ተዳርጎ የነበረው ኢትዮጵያዊው፣ ኢንጂነር ቸኮለ መንበሩ/ Engineer Chekole Menberu ቅን በሆኑ ወገኖቹ አማካኝነት ከትልቅ ቦታ ደረሰ “የሚል አለማቀፋዊ ሽፋን ያዘለ ዜናውን በቅርቡ እንደሚያስነብበን ሙሉ ተስፋ አለኝ።