ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ ባለቤትነት ህግን አጸደቀች || ታምሩ ገዳ

ኢትዮጵያ የጦር መሳሪያ ባለቤትነት ህግን አጸደቀች || ታምሩ ገዳ

ብዙዎችን ሲያነጋግር የነበረው የሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን በመጠኑም ቢሆን ሊቀርፍ ይችላል የተባለ ህግ በፓርላማው መጽደቁ ታወቀ።

ዜና አጋግሎት ሮይተርስ ዛሬ እንደዘገበው ዜጎች ለጦር መሳሪያ ባለቤትነት መብት የሚያስችላቸው የእድሜ ጣሪያ ከስንት አመት እንደ ሚጀመር ክልሎች ይወሰናሉ ተብሏል። በሁለት መቶ ሰማኒያ ሁለት የህዝብ እንደራሴዎች በተገኙበት የፓርላማ ውሎ በሀለት ተቃውሞ እና በአራት ድምጸ ታቅቦ የጸደቀው አዲሱ ህጉ እንደሚለው ማንኛውም ዜጋ ከአንድ በላይ የጦር መሳሪያ ባለቤት መሆን አይፈቀድለትም።ህጉን የጣሰ ወይም የጣሰች እስከ ሶስት አመት የሚቆይ እስራት ይጠብቃቸዋል ።

ከመንግስታዊ ተቋማት ውጪ ግለሰቦች የጦር መሳሪያ ወደ አገርቤት የማስገባት እና የማዘዋወር መብት እንደሌላቸው የደነገገው አዲሱ ህግ ሕገወጥ የጦር መሳሪያ የሚያዘዋውሩ ሰዎችም ከስምንት እስከ ሀያ አመት የሚቆይ እስራት እንደሚጠብቃቸው በህጉ ውስጥ መካተቱን ዘገባው አክሎ ገልጿል።እንደ ህዝብ እንደራሴው አቶ ተስፋዬ ዳባ እምነት”በኢትዮጵያ ውስጥ ከደርግ ውድቀት አንስቶ ከበቂ በላይ የጦር መሳሪያ በግለሰቦች እጅ በመኖሩ የህጉ መውጣት የጦር መሳሪያ ባለቤትነትን ፈር ያሲይዛል” በማለት የህጉ መውጣት አውንታዊ እና ተገቢ እንደሆነ ተናግረዋል። ከግለሰብ እስከ ቡድን እና ባለሀብቶች ሳይቀሩ የተሰማሩበት የህገወጥ የጦር መሳሪያ አዘዋዋሪዎችን እንቅስቃሴን ለመግታት ህግ ብቻውን ፋይዳ እንደማኖረው ይልቁንም የተቀናጀ የጸጥታ እና የፍትህ አካላት ጥረት እና በማህበረሰቡም ዘንድ በጠመንጃ ከማምለክ ለህግ ተገዢ መሆን እና በህገወጥ ተግባር የተሰማሩትን ከመደበቅ ለህግ የማቅረብ አስተሳሰብ መታከል እንዳለበት ብዙዎች ይስማማሉ።

መቀመጫውን በቤልጂየም ብራስልስ ያደረገው የአለማቀፉ የቀውስ አጥኚ የኢትዮጵያ ተመራማሪ የሆኑት ዊሊየም ዳቮስ በበኩላቸው “በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚታየው ፖለቲካዊ ያለመረጋጋት እና የመንግስታዊ የህግ አካላት መዳከም እና መላላት ይታያል የሚል አመለካከት እና ስጋት ያደረባቸው ዜጎች እራስን ለመከላከል በማለት የህገወጥ የጦር መሳሪያዎች ሸማቾች ለመሆን ተገደዋል፣ እርምጃውም በቋፍ ላይ ላለው የሰላም እጦት ላይ ነዳጅ የማርከፍከፍ ያህል ነው” በማለት ትዝብታቸውን ገልጸዋል።

አገሪቱ በውጪ ሀይሎች ወረራ የተቃጣባት እና በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ውስጥ የወደቀች እስኪመስል ድረስ በአሁኑ ወቅት በሁሉም አቅጣጫ የህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውሩ መበራከቱን የፌደራል እና የክልል መገናኛ ብዙሀናት በስፋት ሲዘግቡት ይስተዋላል።

በአለማችን ላይ የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያን አፍቃሪዎች …

በአለማችን ላይ ከሰባት ሚሊዮን በላይ የጦር መሳሪያዎች በግለሰቦች እጅ የወደቁ መሆናቸውን የተለያዩ ዘገባዎች ይገልጻሉ።የአንስተኛ የጦር መሳሪያዎችን የሚቃኘው (Small Arms Survey) እንደሚለው ከሆነ የጦር መሳሪያዎችን በነፍስ ወከፍ በቤታቸው አከማችተው የሚገኙባቸው አገራት ሰንጠረዥ አሜሪካኖች ቁጥር አንዶች ሲሆኑ በ100 አሜሪካዊያኖች ውስጥ 112.6 ወይም አንድ ሰው ከአንድ በላይ የጦር መሳሪያ ባለቤት ነው። በሁለተኛ ደረጃ እኤአ በ1990ዎቹ ከቀድሞው ዩጎዝላቪያ የተገነጠለችው ሰርቪያ(75.6)በመያዝ ዜጎቿ ለጣመንጃ ያላቸውን ፍቅርን ያሳያል። የመን ፣ስዊዘርላንድ ፣ቆጵሮስ፣ ሰውስ አረቢያ ፣ኢራቅ ፣ኡራጓይ ፣ስዊድን እና ኖርዌይ እንደ ቅደማቸው አስሩ የጦር መሳሪያ በነፍስ ወከፍ የበዛባቸው የአለማችን አገራት ናቸው።

የዛሬን አድርገው እና ዜጎቻቸው በነፍስ ወከፍ ለጦር መሳሪያ ብዙም እድል የሌላቸው አገራት ደግሞ ቱኒዚያ፣ የሰለሞን ደሴቶች፣ ኢትዮጵያ፣ጋና፣ኤርትራ፣ ፉጂ፣ሲንጋፖር፣ ባንግላዲሽ ብዙ በጥቂቱ ተጠቃሾች ናቸው።

በጦር መሳሪያ ጦስ ብዙ ህዝብ የሚሞትባቸው አገራት… የማእከላዊዋ አሜሪካዋ ኡንዱራስ፣ ቬንዙዌላ፣ ስዋዚላንድ፣ ጓቲማላ፣ ጃማይካ፣ ኤል ሳልቫዶር፣ ኮሎምቢያ፣ ብራዚል፣ ፓናማ፣ ኡሯጓይ፣ እንደቅደም ተከተላቸው ዋንኛ ተጠቃሾች ናቸው።

LEAVE A REPLY