ምንሽ ናት ጨረቃ…? || ገጣሚ ማሕሙድ እንድሪስ

ምንሽ ናት ጨረቃ…? || ገጣሚ ማሕሙድ እንድሪስ

ትዝ ይልሻል አብረን ሳለን?
እንደዛሬው ሳንላያይ
በስስት እየተያየን በፍቅር ቃል ስንወያይ ?
በችኩል እሳቤ ግፊት
እንደዛሬው ሳንሆን በፊት
በክፉ ምኞት ሽንገላ ደስታችንን ሳንነጠቅ
በብቼኝነት ስቃይ ውስጥ ፀፀት ለብሰን ሳንደበቅ

ያኔ … ያኔ ….
ከጨረቃ ውበት ሰርቀን
በወርቃማው ብርሀን ደምቀን
በተፈጥሮ ግርማ ሞገስ ባምላክ ጥበብ ተመስጠን
በቃልኪዳን ኮረብታ ላይ ጎን ለጎን ተቀምጠን
ልዩ ደስታ ስንቋደስ ያለ ገደብ ያለመጠን …

ዛሬም ብቻየን ሁኜ
ተለያይተን ተራርቀን በትካዜውስጥ መንኜ
እዚያው እቦታችን ላይ ብቻየን እቀመጣለሁ
እተክዝ እተክዝና ወደ ሰማይ ቀና እላለሁ
እናም ድምቡል ቦቃ ውስጥ ውብ ምስልሽን አየዋለሁ
በማራኪ ጥምረታችሁ ቀን በቀን እመሰጣለሁ ።
ከዚያም አስብ አስብና
ምላሽሽን ባላገኝም —ጥያቄየን አቀርባለሁ …

በለስላሳው ልዝብ ውበት በጨለማው ድባብ ደምቃ
ምሽታችንን ልታስውብ ስትወጣ ወቅቷን ጠብቃ
ከ‘ቅፏ የማትነጥልሽ ላንቺ ምንሽ ናት ጨረቃ ?

LEAVE A REPLY