የእንግሊዝ ንግስት የሆኑት ኤልሳቤትን በታሪክ አጋጣሚ ለማግኘት እድሉ ቢገጥሞት በቅድሚያ የሚነገሮት ነገር ቢኖር “ንግሰቲቷን እና ቤተሰቦብቻቸውን እንደ ቆሎ ጓደኛዎ ተጠምጥመው ሰላምታ ማቅረብ ብሎ ነገ በጭራሽ አይሞከርም፣ ይልቁንም ለክብራቸው ሲባል ከአንገቶት ጎንበስ፣ ከጉልበቶም ሸብረክ በማለት ሰላምታ ሊያቀርቡላቸው ይገባል” የሚል ቅድመ የፕሮቶኮል ትእዛዝ ይሰጠቶታል። ንግስቲቱም ቢሆኑ እጅግ ለሚወዷቸው እና ለሚቀርቧቸው ስዎች ካልሆነ በቀር ጉንጫቸውን ሆነ እጃቸውን ለማንም አይሰጡም።
ይሁን እንጂ፣ እንደ ወግ አጥባቂው የእንግሊዞቹ ፣ኤክስፕርስ ጋዜጣ፣ ሰሞነኛ ዘገባ ከስድስት አስርት አመታት በላይ ሞናርኪውን በንግስቲነት በመምራት ላይ ያሉት ንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛዋ ከባለቤታቸው ልኡል ፊሊፕስ ጋር እኤአ 1955 ከአራት ሺህ በላይ እንግዶች በተገኙበት በግርማዊነታቸው የሀያ አምስተኛ የንግስና በዓል /Silver jubilee Celebration ላይ ለመታደም ወደ ኢትዮጵያ ለጉብኝት ከአራት ሺህ በላይ እንግዶች በመጡበት ወቅት በእንግሊዝ ንጉሳዊያን ባህል እና ፕሮቶኮል ባልተለመደ መልኩ “ለግርማዊ ቀዳማዊ ኃ/ስላሴ እና ለባለቤታቸው ለ እቴጌ መነን አስፋው ትንበርክከው እና ጎንበስ ብለው ሰላምታ ሰጥተዋቸው ነበር” የሚል አነጋጋሪ የሆነ አባባልን አስተናግዷል።
በወቅቱ በቤተ መንግስት ተገኝቶ ላይፍ ለተባለው መጽሔት ፎቶግራፍ ያነሳው፣ነገር ግን ለምስሎቹ የግርጌ ማስታዎሻ (ካፕሽን)ያልሰጠው ታዋቂው አሜሪካዊው ፎቶግራፍ አንሺ አል ፍርድ ኢስኢንስትኢድት የስራ ውጤትን በምስል አስደግፎ በትዊተር ገጹ ላይ ከሁለት አመት በፊት የከተበው አፍሪካ ፋክት ዞን “ንግስት ኤልሳቤት እና ልኡል ፊሊፕስ ለግርማዊነታቸው እና ለባለቤታቸው ለእቴጌ መነን ተምበርክከው ሰላምታ ያቀረቡ ብቸኞቹ ንጉሳዊያን ጥንዶች ናቸው” ብሎታል። ትውተሩም በጊዜው ከሶስት ሺህ በላይ በሆኑ ወገኖች መካከል ተሰራጭቷል (Shared)ተደርጓል።
አንዳንድ ወገኖች ንግስቲቱ በወቅቱ” ከሮያል ክብራቸው ዝቅ በለው እና ባህሉን ገሸሽ አድርገው ለአፍሪካዊው፣ለኢትዮጵያው የመጨረሻ ንጉስ ለግርማዊነታቸው እንዴት እጎንብሰው ሰላምታ ሰጡ? “ብለው ሲጠይቁ ሌሎች በበኩላቸው “የዘር ሀረጋቸው በቀጥታ ከንጉስ ሶሎሞን እና ከንግስት ሳባ እንደሚመዘዝ ለሚነገርላቸው፣ የዛሬን አድርገው እና እንግሊዝ በጎርፍ ስትጥለቀለቅ ለብርድ ማስታገሻ ብለው ከእንድ ቶን በላይ ቡና የላኩ፣ ጀርመንም በጦርነት ስትፈራርስ ለታረዙ ዜጎቿ የደ/ብርሃን ብርድ ልብስ የለገሱ፣ በጭቆና ቀንበር ለነበሩ የካሪቢያን አገራት የነጻነት ተምሳሌት የነበሩት፣ የአፍሪካ ህብረት እና የዘመናዊ ኢትዮጵያ አባት ለግርማዊ፣ ለቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ የእንግሊዟ ንግስት እና ባለቤታቸው ቢንበረከኩላቸው ምን ይደንቅ ? “በማለት ለቀኃስ ያላቸውን ልዩ አክብሮት እና የምስሉን ተአማኒነትን ለማሳመን ሲሞክሩ ተስተውለዋል።
በተለያዩ ታዋቂ ሰዎች ህይወት ዙሪያ የሚያውጠነጥነው፣ ላቲን ታይምስ፣ የተባለው ድህረ ገጽ በበኩሉ ንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛዋ በታሪካቸው ጎንበስ በማለት እክብሮታቸውን የሰጡበት ጊዜ ቢኖር የውንድ ልጃቸው የልኡል ቻርልስ ይቀድሞ ባለቤት፣ የልኡል ዊሊየም እና የልኡል ሃሪ እናት የነበሩት፣ የዌልሷ ልእልት ዲያና እኤአ መስከርም 1997 በመኪና አደጋ ፓሪስ፣ ፈራንሳይ፣ ውስጥ በሞቱበት ወቅት በአደጋው ልባቸው የተነካው ንግስት ኤልሳቤጥ ሁለተኛ አስክሬኑን ጎንበስ ብለው የሸኙበት አጋጣሚን እና በአንደኛው የአለም ጦርነት ላይ ለእንግሊዝ እና ለህዝቦቿ ሲሉ መሰዋትነትን ለከፈሉ ወታደርች በህዳር ወር በሚደረገው የመታሰቢያ ስነስርአት ላይ ሁሉም ጎንበስ ብሎ ክብሩን እንደሚገልጥ ሁሉ ንግስቲቷም ተሳታፊ መሆነቸውን ይገልጻሉ።
ከላይ የተጠቀሱት አጋጣሚዎች እና የታሪክ ክስተቶችን ከሚጠቅሱት መካከል አንዱ የሆኑት ጡረተኛው ዲፕሎማት ስታቱ አለን “ንግስት ኤልሳቤጥ እና ባለቤታቸው ልኡል ፊሊፕስ ለኢትዮጵያው ቀኃስ ጎንበስ አሉ መባሉ ሀሰት ነው፣ በወቅቱ የቀኃስን ክብረ በአል ለአሜሪካ መንግስት የዘገበ እና በአሁኑ ወቅት በተ/መ/ድ የምስል ክምችት ክፍል ውስጥ የሚገኝ ፎቶ ላይ ንግስቲቱ ሲያጎበድዱ አይታዩም” በማለት ለማስተባበል ሞክረዋል። አንዳንዶችም እንዲሁ በተባለው ጊዜ ንግስቲቲ እና ባለቤታቸው ወደ ኢትዮጵያ ተጓዙ የሚል መረጃ እና ማስረጃ የለም ባዮች ናቸው።
ታዲያ ይሄ ምስልን እንደ ዘመኑ “የሀሰተኛ ዜና”(የፌክ ኒውስ)፣ የፎቶ ቅንብር (ፎቶ ሾፕ) ውጤት ጋር እናገናኘው ?ወይስ እንዚያ እንግሊዞች ወትሮውንም እንደስማቸው…እንበለው?።