የአንበጣ መንጋ ሀዋሳን ጨምሮ በደቡብ ዞኖች ውስጥ ተከሰተ
ከየመን ከወራት በፊት የመጣው፣ በአማራና ትግራይ ክልል የተወሰኑ ቦታዎች የተንሰራፋው የአንበጣ መንጋ ፊቱን ወደ ደቡብ ክልል አዙሯል:: በደቡብ ክልል ውስጥ የሚገኙ ስድስት ዞኖች የበረሃ አንበጣ መንጋ መከሰቱን የክልሉ የግብር እና የተፈጥሮ ሀብት ቢሮም አረጋግጧል::
ጥአቃት አድራሹ የበረሃ ንበጣ መንጋው ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ ኅብረተሰቡ የተለያዩ ባህላዊ የመከላከያ ዘዴዎችን በመጠቀም ከፍተኛ ርብርብ እያደረገ ነው፡
አርሶ አደሩ የአንበጣ መንጋው ሊያደርሰው የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል የሚያደርገውን ርብርብ አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ያሳሰበው ቢሮ መንግሥት የመከላከያ እርምጃ በፍጥነት እንደሚወስድ ገልጿል፡፡
አሁን ላይ ፊቱን ወደ ደቡብ ክልል ያዞረው የበረሃ አንበጣው ወላይታ ፣ ጌዴኦን ጨምሮ በስድስት ዞኖች የተከሰተ ሲሆን በሀዋሳ እና በሁለት ልዩ ወረዳዎችም ላይም ታይቷል ፡፡
የሙስሊሙ የ60 ዓመት ጥያቄ በመመለሱ ሐጂ ሙፍቲ እንድሪስ መንግሥትን አመሰገኑ
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ሥልጣን ላይ የለው መንግስት ለ60 ዓመታት ገደማ ያቀረበውን ጥያቄ ለመመለስ ውሳኔ በማስተላለፉ መደሰቱን በመግለጽ ይፋዊ ምስጋና አቅርቧል።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ከትናንት በስቲያ ባካሄደው 78ኛ መደበኛ ስብሰባው በስድስት ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፎ ነበር:: ምክር ቤቱ ውሳኔ ካሳለፈባቸው አጀንዳዎች መካከል የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ህጋዊ ሰውነት እንዲሰጠው የተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ዋነኛው ነው።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የረቂቅ አዋጁ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መመራቱንና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል። የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እንድሪስ የምክር ቤቱ የህጋዊ ሰውነት ጥያቄ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግስት ጀምሮ ሲቀርብ መቆየቱን አስታውሰውለዓመታት ሲንከባለል የቆየውና የፍትህና የእኩልነት ጥያቄ የነበረውን በአሁኑ ወቅት መንግስት ለመመለስ ያሳለፈውን ውሳኔም አድንቀዋል።
በተጨማሪም የሙስሊም ባንክ እንዲቋቋም ከመፍቀድ ጀምሮ በርካታ የህዝበ ሙስሊሙ ጥያቄዎች በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ ባለው መንግስት አማካኝነት ምላሽ ማግኘታቸውን ጠቁመው ህዝበ ሙስሊሙን ያስደሰተው ጉዳይ ህዝበ ክርስቲኑንም የሚያስደስት እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል።
ሐጂ ሙፍቲ ረቂቅ አዋጁ በአፋጣኝ ጸድቆ ጥቅም ላይ ይውል ዘንድም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትኩረት እንዲሰጠው መልዕክት አስተላልፈዋል::
ለቀጣዮቹ 4 ወራት 7 ሚሊዮን ዜጎች ሰብኣዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተባለ
በኢትዮጵያ እስከ ሰኔ 2012 ዓ.ም ድረስ 7 ሚሊየን ዜጎች ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ብሔራዊ የአደጋ ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ።
ኮሚሽኑ ከጥር እስከ ሰኔ 2012 ዓ.ም ምግብና ምግብ ነክ ያልሆነ የድጋፍ አቅርቦት የሚያስፈልጋቸው ተረጂዎችን በጥናት መለየቱን ጠቁሞ ፤ በጥናቱ በአሁኑ ወቅት በምግብ ፍላጎት ተረጂ የሆኑት 6 ሚሊየን ሰዎች እንደሆኑና ባለፈው ዓመት ከነበረው 8 ሚሊየን ተረጂ ጋር ሲነጻጻር ቅናሽ ማሳየቱንም አስታውቋል።
ለመሻሻሉ ምክንያት ደግሞ በመኽር ምርት የተሸፈኑ የሰብል አብቃይና አርብቶ አደር አካባቢዎች በመኽር ምርት ግኝት ለማገገም በመቻላቸው ተብሏል፡፡
የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች ቁጥር የሚወሰነው የሰብዓዊ እርዳታና የአደጋ አይበገሬነት ሰነድ በማዘጋጀት እንደሆነ ያመላከተው ኮሚሽኑ ፤ በሀገሪቷ ከቀደመው ጊዜ በተለየ የድርቅ ክስተት እየተደጋገመ በመምጣቱ የህዝቡን አኗኗርና የሀገሪቷን ኢኮኖሚ እየጎዳ መሆኑንም ይፋ አድርገዋል፡፡
በተለይም በዓለም ዐቀፍ ደረጃ የተከሰተው የአየር ንብረት መዛባት በሀገሪቷ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ በማሳረፍ ድርቁን ተደጋጋሚ አድርጎታል ያሉት የኮሚሽኑ ሓላፊ ፤ መንግስት ጉዳቱን ለመከላከልና ለመቋቋምም ከለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመተባበርና ከፍተኛ በጀት በመመደብ እየሰራ መሆኑን እና ለችግሩ ወቅታዊ ምላሽ ከመስጠት ጎን ለጎንም ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር አደጋውን ለመቀነስና ለመከላከል የሚያስችሉ ዘላቂ የልማት ተግባራት በመንግስት በኩል እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ቦይንግ የዓለማችን ግዙፉን ባለ2 ሞተር 777 ኤክስ አውሮፕላን ሙከራ በስኬት አጠናቀቀ
ከማክስ ኤይት አውሮፕላኑ የማሊዢያ እና ኢትዮጵያ አየር መንገዶች አደጋ በኋላ ገበያው የተቀዛቀዘው ግዙፉ አውሮፕላን አምራች ካምፓኒ ቦይንግ 777ኤክስ የተሰኘው የዓለማችን ግዙፉን ባለሁለት ሞተር አውሮፕላን የሙከራ በራራውን በድል አጠናቋል::
የኢትዮጵያ አየር መንገድና የኢንዶኔዢያ አቻው ንብረት የሆኑ ሁለት አውሮፕላኖች በወራት ልዩነት ተከስክሰው በድምሩ 346 ሰዎች ሞተዋል። ከአደጋዎቹ በኋላ የተቀሩትን 737 ማክስ አውሮፕላኖች ከበረራ ያገደው ቦይንግ እነሆ ግዙፍ አውሮፕላን ይዞ ብቅ ማለቱ ተሰምቷል።
ለአራት ሰዓትታ የዘለቀው የሙከራ በረራ ሲያትል የተሰኘችው የአሜሪካ ከተማ አቅራቢያ የተካሄደ ሲሆን የተሳካው በረራ ከመካሄዱ በፊት ሁለት ጊዜ በአየር ፀባይ ምክንያት በረራዎች እንዲቋረጡ መደረጉም ተገልጿል።
252 ጫማ ወይም 76 ሜትር የሚረዝመው አውሮፕላን የዓለማችን ግዙፉ ባለሁለት ሞተር የንግድ አውሮፕላን ነው ተብሏል። ቦይንግ እስካሁን 309 777ኤክስ አውሮፕላኖች ሸጫለሁ የአንዱ ዋጋ ደግሞ 442 ሚሊዮን ዶላር ነው ሲል አስታውቋል:: የድርጅቱ ግብይት ባለሙያ ዌንዲ ሶወርስ ድርጅታችን ትልቅ ነገር ማድረግ እንደሚችል ያሳየ ነው ካሉ በኋላ አውሮፕላኑ 360 ሰዎች የመጫን አቅም ካለው ኤርባስ ኤ350-1000 ጋር ተመሳሳይ ባሕሪ እንዳለውም አብራርተዋል።
ቦይንግ ለአደጋ እየተጋለጡ ያሉትን 737 ማክስ አውሮፕላኖች ሲያመርት ለደህንነት የሰጠው ዋጋ ዝቅ ያለ ነው ተብሎ ብዙ ወቀሳ አስተናግዷል። እንዳይበሩ የታገዱት አውሮፕላኖች እንደገና ተፈትሸው ወደ ሰማይ ይወጣሉ ሲል ድርጅቱ አሳውቆ ነበር።
ማክስ 737 የቦይንግ እጅግ በብዛት የተሸጡ አውሮፕላኖች ሲሆን አውሮፕላኖቹ እንዳይበሩ በመተጋዳቸው ምክንያት እስካሁን ድረስ ቦይንግ 9 ቢሊዮን ዶላር ለሚደርስ ኪሳራ ተጋልጧል።
ከመላው ዓለም የተሰባሰቡ የቻይና መሀንዲሶች በ6 ቀን ሆስፒታል ሊገነቡ ነው
የቻይናዋ ዉሃን ግዛት በ6 ቀናት ውስጥ ደረጃውን የጠበቀ ሆስፒታል ልትገነባ መሆኗን ይፋ ማድረጓ የዓለምን ትኩረት ስቧል።
የውሃን ግዛት ሆስፒታሉን በአስቸኳይ የምትገነባው ቻይና ውስጥ ተከስቶ መዳረሻውን ብዙ የዓለም አገራት እያደረገ ያለውን የኮሮና ቫይረስን ለማከም መሆኑ ደግሞ ዜነው ጆሮ ገብ እንዲሆን አስችሎታል።
ገዳይ ቫይረሱ በግዛቷ ከተከሰተ ወዲህ 830 ሰዎች በቫይረስ መጠቃታቸው እና 41 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሕይወታቸውን አጥተዋል። 11 ሚሊዮን ዜጎች በሚኖሩባት ውሃን ግዛት በቫይረሱ በታመሙ ታካሚዎች ሆስፒታሎች ተጨናንቀው ከፍተኛ የመድኃኒት እጥረት ተከስቷል ።
በ6 ቀናት ውስጥ ግንባታው የሚጠናቀቀው ሆስፒታል 1 ሺህ የመኝታ አልጋዎች እንዲኖሩት ተደርጎ ይገነባል:: የተለቀቁ የተንቀሳቃሽ ምስሎች እንደሚያሳዩት ቆፋሪ ማሽኖች በቦታው የደረሱ ሲሆን በ25 ሺህ ሄክታር ላይ የሚያርፈውን ሆስፒታል መቆፈር ጀምረዋል።
አዲስ የሚሰራው ሆስፒታል በ2003 (እ.አ.አ) የሳርስ ቫይረስን ለማከም በቤጂንግ ከተሰራው ሆስፒታል ጋር ተመሳሳይ ነው መባሉንም ዓለም ዐቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።
“ቻይና እንደዚህ አይነት ወቅታዊ ችግሮችን ለማለፍ ፕሮጀክቶችን በፍጥነት በማጠናቀቅ የምትታማ አይደለችም” በማለት ያንዙንግ ሁዋንግ የተባሉ ዓለም አቀፍ የጤና ሞያተኛ ከወዲሁ ምስክርነታቸውን ሰጥተው ፤በቤጂንግ በ2003 የተሰራው ሆስፒታል በሰባት ቀናት ነበርና የጠተናቀቀው ይህኛውን ሆስፒታል በተባለው ቀን ለማጠናቀቅ የሚያስቸግር ነገር የለም ነው ያሉት።
ውሳኔው ከላይ ካሉት ባለስልጣናት የተሰጠ በመሆኑ የቢሮክራሲና የፋይናንስ ሰንሰለቶች ስለማይኖሩት፣ ሁሉም አቅርቦቶች በበቂ ደረጃ የሚሟላለት በመሆኑ ሆስፒታሉ በተባለው ጊዜ ይጠናቀቃል የሚል እምነት እንዳላቸውም አረጋግጠዋል::
በአሁኑ ወቅት መሃንዲሶቹ ከመላው ቻይና ተሰባስበው ሥራ ለመጀመር ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል:: ቻይና በምህንድስናው ዘርፍ እጅግ የተዋጣላት ነች፤ ምናልባት ምዕራባዊያን ላያምኑ ይችላሉ፤ ነገር ግን ይህ ዕውን መሆኑን ለማረጋገጥ 6 ቀናትን ብቻ ይታገሱ በማለት የቻይናዊያንን የምህንድስና ፍጥነት ማየት ይቻላል እየተባለም ነው:: ከግንባታው በኋላ ዉሃን ግዛት መድሃኒቶችን ከጎረቤት ሆስፒታል ታስመጣለች ወይም ደግሞ ቀጥታ ከፋብሪካዎች ታስለች ተብሎ ይጠበቃል።
በ2003 በቻይና ተከስቶ የነበረውን የሳርስ ቫይረስ ለማከም ሲባል ዢያኦታንግሻን ሆስፒታል በቤጂንግ ተገነባ። የዓለማችን ፈጣኑ ግንባታ በመሆን በሰባት ቀናት ብቻ ነበር የተገነባው። በተባለው ቀን ለማጠናቀቅ 4 ሺ የሚሆኑ ሙያተኞች ሌትና ቀን በስራው ተሳትፈውበታል::