መነሻውን ከቻይናዋ ሁዎንግ ግዛት ያደረገው አደገኛው እና ገዳዩ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎች በበርካታ አገራት እየታዪ ይገኛል። የአፍሪካ ቀንድ አገራቱ ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ እና ሱዳንም የቫይረሱ ተጠርጣሪዎችን እየመረመሩ እና ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ እስከ አሁን ድረስ ሶስት ተማሪዎች የሚገኙበት አራት የቫይረሱ ምልክት ይኖርባቸዋል ብላ የጠረጠረቻቸው ሰዎችን በተለየ ቦታ በማቆየት ምርመራ በማድረግ ላይ መሆኗን ገለጸለች ሲሆን ከሰዎቹ የተወሰደ ናሙና ደ/አፍሪካ ውስጥ በተደረገው ማጣራት ተጠርጣሪዎቹ ከቫይረሱ ነጻ ናቸው ተብሏል ። ለዚሁ ተግባር ይረዳ ዘንድም በቦሌ አውሮፕላን ጣቢያ የመጀመሪያ የምርመራ ማእከል የተቋቋመ ሲሆን ልዩ ሆስፒታሎችም መቋቋሙን መንግስት ሰሞኑን ገልጿል። በቀን ስድስት በረራዎችን ወደ አምስት የቻይና ከተሞች የሚያደርገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ላልተወሰነ ጊዜ ማቋረጡ ለዜና ሮይተርስ የገለጸ ቢሆንም አየር መንገዱ ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ዘገባውን በማስተባበል ሙሉ በረራውን እንደሚቀጥል አስታውቋል። በርካታ አየር መንገዶች እንዲሁ ወደ ቻይና የሚያደርጉትን በረራ አቋርጠዋል ወይም እንደሚያቋርጡ እየገለጹ ይገኛሉ።
ጎረቤት ኬኒያ እንዲሁ አንድ ተማሪን የቫይረሱ ተጠቂ ሊሆን ይችላል በማለት በተለየ ስፍራ አስቀምጣ ምርመራውን ጀምራለች።ናይሮቢ የሚገኘው የቻይና ኢምባሲ በበኩሉ ወደ ኬንያ የሚገቡ ዜጎቹ ላይ ምርመራ እና ቅኝት እንደሚያደርግ አስታውቋል። የኬኒያ አየር መንገድ ባወጣው መግለጫ ማንኛውም ተሳፋሪ ወደ አውሮፕላን ገብቶ ትራንዚት ከማድረጉ በፊት ተገቢው ቅድመ ምርመራ ይደረግለታል ሲል ለደንበኞቹ አስታውቋል።
እንደ ኢትዮጵያ ሁሉ ከቻይና ጋር የጠበቀ ግኑኝነት ያላት እና ብፕርካታ ቻይናዊያኖች የሚረግጧት ሱዳን በበኩሏ በትላንትናው እለት ይፋ እንዳደረገችው ከኢትዮጵያ እና ከግብጽ የገቡ ሁለት የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎች ካርቱም እና ጊዛን ውስጥ በጊዜያዊ ማቆያ ማእከል ምርመራ እየተደረገላቸው ነው ብላለች። ሱዳን የአየር፣የየብስ እና የባህር መስመሮቿ ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንደምታደርግ አስታውቃለች።
የሀይለኛ ትኩሳት፣ሳል፣የማያቋርጥ ፈሳሽ ከአፍንጫ መፍሰስ፣የጉረሮ መታወክ ዋንኛ ምልክቶቹ የሆኑት የኮሮና ቫይረስ በአሁኑ ሰዓት በአለማችን ላይ አሜሪካን፣ካናዳ፣ፈረንሳይ፣ደ/ኮሪያ ፣ህንድ፣ፊላንድ ፣አረብ ኤሜሬት፣ አውስትራሊያ…ወዘተ ጨምሮ በ አስራ ዘጠኝ አገራት ውስጥ በስባት ሺህ ሰዎች ላይ ፍንጮቹ የታየ ሲሆን በቻይና ውስጥ አንድ መቶ ሰባ ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።
በሽታውን ለመከላከል ቻይና ውስጥ ክትባት እየተሞከረ ሲሆን የአለም የጤና ድርጅት(WHO) ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ቴዎድሮስ አድህኖም ማክሰኞ እለት ወደ ቤጂንግ ፣ቻይና በማምራት የአገሪቱ ፕ/ት ቺ ፒንግን ያነጋገሩ ሲሆን ቻይና እያደረገችው ላለው ጸረ ኮሮና ቫይረስ ዘመቻ በትዊተር ገጻቸው ላይ ያደነቁት ዶክተር ቴድሮስ የበሽታውን ስርጭት ከግንዛቤ ውስጥ በመክተት አላማቀፋዊ ስጋት ይሆናል ወይም አይሆንም የሚለውን አቋም ዛሬ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ የተጠበቀ ሲሆን ድርጅታቸው ባወጣው መግለጫው “በሽታው አለማቀፋዊ ስጋትን(Global Public Health Emergency) የሚያሻው ቢሆንም በሽታውን በመቋቋም ደረጃ በቻይና መንግስት ላይ ጽኑ እምነት አለን፣ከዚህ አኳያ በቻይና ላይ ምንም አይነት የጥላቻ አይን ልናሳርፍ አይገባም፣አይመከርም”ብሏል
የኮሮና ቫይረስ ያስከተለው ስጋት እና ቁጣ …..
የቫይረሱ መንሻ የሆነችው የቻይናዋ ሁንዋን ግዛት ነዋሪዎች የሆኑ ከስምንት ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎች እንቅስቃሴያቸው በመገታቱ ስጋታቸውን እና ቁጣቸውን በተለያየ መንገዶች ባመግለጽ ላይ ይገኛሉ። አንድ ዘመዱ የኮሮና ቫይረስ ታማሚ የሆነ ግለሰብ ሰሞኑን ወደ ሆስፒታል በመሄድ የዶክተሩን የአፍንጫ መጋረጃ ( ጭምብል) እና የመከላከያ ልብሶችን አውልቆ እንደቀዳደበት የአገሪው ቴሌቭዥን ሲሲቲቪ ዛሬ ሀሙስ ዘግቧል። በሌላ ሆስፒታል እንዲሁ የተቆጡ የታማሚ ቤተሰቦች የአንድ ዶክተር ጓንቱን አውልቀው እንደቀደዱበት ተዘግቧል።የቫይረሱ ተላላፊነት ያሰጋቸው በርካታ አገራት በሽታው በቶሎ መፍትሔ ካልተገኘለት አለማቀፋዊ የማህበራዊ ኢኮነሚያዊ ቀውስ ሊፈጥር ይችላል ያሙል ስጋት እድሮባቸዋል።