ዶክተር ዐቢይ አህመድ የህዳሴው ግድብ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ጎበኙ

ዶክተር ዐቢይ አህመድ የህዳሴው ግድብ ግንባታ የደረሰበትን ደረጃ ጎበኙ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከግብፅ ጋር ስላለበት ውዝግብ እንጂ ግንባታው ከምን እንደደረሰ ያልተነገረለት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በስፍራው ተገኝተው ጎብኝተዋል።

በመስክ ጉብኝቱ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ጨምሮ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ሓላፊዎች ጭምርተገኝተዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው የግድቡ አጠቃላይ ግንባታ ያለበትን ሁኔታ ተዘዋውረው የተመለከቱ ሲሆን፤ የግድቡ የሲቪል እና ኤሌክትሮ መካኒካል የግንባታ ደረጃ ያለበትን ሁኔታም ገምግመዋል።

በጉብኝቱ ላይ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሥራ ክንውን እና ግንባታው የደረሰበትን ሁኔታ ሪፖርት ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ቀርቧል።

የክንውን ሁኔታውን በመመልከት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ሕልምን እውን ለማድረግ ውጤታማ ሥራ የማከናወንን አስፈላጊነት በዝርዝር ለባለሙያዎቹ አብራርተዋል። ከአያያዝ ጉድለት የተነሣ የተከሠተውን የሥራ መጓተት ያስታወሱት ጠቅላዮ ፤ ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ የህዳሴው ግድብ የግንባታ ሥራ የገጠመውን ችግር ለመፍታት መንግሥት የወሰዳቸውን ርምጃዎች አስረድተዋል።

በፕሮጀክቱ  የሥራ ዘርፍ ላይ ለተሠማሩት ኩባንያዎች “የዛሬው ጉብኝቴ ከዚህ ቀደም ካደረኩት የተሻለ አፈጻጸም ያየሁበት በመሆኑ አስደስቶኛል” ያሉት ዶክተር ዐቢይ አህመድ ፤ የኢትዮጵያ ህዝብ እና መንግሥት ተስፋ የጣለበትን ይህን ፕሮጀክት እውን ለማድረግም በተናጥል ሳይሆን በህብረት እና በጋራል ሊሠራ ይገባል ብለዋል።

በቀጣይ አመት በሚያደርገው ጉብኝት ቢያንስ ሁለቱ ተርባይኖች ኃይል ሲያመነጩ ማየት እንደሚፈልጉም መልእክታቸውን ለኩባንያዎቹ አስተላልፈው ፤ በዚህ የግንባታ ሂደት ላይ የሚያጋጥሙትን ችግሮች ለመፍታትም መንግስታቸው ሌት ተቀን እንደሚሠራም ተናግረዋል።

የታላቁ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጅነር ክፍሌ ሆሮ ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ ችግሮችን በመለየት በጥራትይ እየተሠራ በመሆኑ ፕሮጀክቱ በተቀመጠለት የጊዜ ሰሌዳ እንደሚጠናቀቅ ጠቁመው ፤ በቀጣይ 2013 ዓ.ም ሁለቱ ተርባይኖች ሃይል ማመንጨት ይጀምራሉም ሲሉ ማረጋገጫ ሰጥተዋል።

LEAVE A REPLY