በ1997 ለዲሞክራሲ የሞተው፣ዶ/ር አብይ ስልጣን ሲይዝ “ስልጣን ያዳብር” ሊል ወጥቶ ከቦንብ የተረፈው፣ ግንቦት ሰባት መሪዎች መጡ ሲባል ድንኳን ነቅሎ ስቴዲያም የተገኘው ሰው አማኙ የአዲስ አበባ ህዝብ ሰው የማይወጣለት ነገር… አዲስ አበቤ ካመነው ከዚህ ሁሉ አንድ ሰው አልወወጣለት ብሎ ዛሬ ሌላው ቀርቶ ሰላማዊ ሰልፍ እንዳያደርግ በግዞት ሲያዝ አለሁህ የሚለው ማጣቱ ግርም ይለኛል (ይገርመኛ ልበል እንጅ ከማዘን በላይ የሚያሳዝነኝ ነገር ነው)፡፡
የበለጠ የሚገርመኝ ደግሞ አዲስ አበቤ ሰልፍ አትወጣም የተባለው ከሆነ ሳምንት በኋላ የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ስላለ ነው በሚል ነው፡፡የአፍሪካ ህብረት ሳምነት ሲቀረው ሰልፍ የተከለከለ የሸገር አራዳ የስብሰባው ዕለት ቤቱን ጠርቅሞ ተቀምጦ አዲስ አበባን አንታርክቲካ አስመስሎ መንግስትን ማጋለጥ እንደሚቻል የጠፋው እንዴት ነው? መቼም እንደ መንግስትም/እንደ ህዝብም እንግዳ ነው የምናከብረው፡፡
ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲስ ቢሆን መግለጫ ከመስጠት፣እንቶኔ ይፈረጅልኝ ከማለት፣ኑና አስር ሽህ ፊርማ አስቀምጡ ከማለት፣”አዲስ አበባን ሙሉ በሙሉ ካላሸነፍኩ ዲሞክራሲ በግሪክም አልነበረም ማለት ነው” ከማለት(ስየ አብርሃ ስታይል! ስየ ሃርቫርድ ከመሄዱ በፊት “እኔ ተንቤን፣ገብሩ በመቀሌ ካላሸነፈ ዲሞክራሲ የለም” ብሎ ነበር ) ውጭ ዲሞክራሲያዊ ትግል ማድረጊያ መንገድ የሌለ የሚመስለው ነገር…
በነገራችን ላይ ከዚህ በፊት አዲስ አበቤ ሰልፍ ሲከለከል የባልደራስ መኳንንት ጋ ደውየ “ሰላዊ ትግል እኮ ሰልፍ ብቻ አይደለም፣ቤት ውስጥ መቀመጥም ያው ነው፤መጮህም ዝምታም እኩል መልዕክት አላቸው” በየ ወትውቼ ነበር… ማን ቢሰማ!
ይህ ሁሉ …. “ወይ አዲስ አበባ! ባሰብኩሽ ጊዜ አለቀስኩ” አስብሎኛል፡፡ የምር የአዲስ አበባን ነገር ባሰብኩ ቁጥር አሁን አሁን በተለይ ልቤ የሚያርፍበት አካል እያጣሁ፣ልቤ እያዘነ መጥቷል! የጠ/ሚ አብይን መንግስት አጥብቄ የማዝንበትም አዲስ አበባ ላይ በሚያራምደው ወልጋዳ አቋም ነው፡፡