“ለልጆቼ ስል ጽጉሬን ለሁለት ዶላር ሸጥኩት…”እናት || “ለልጆቼ ስል ጽጉሬን ለሁለት ዶላር...

“ለልጆቼ ስል ጽጉሬን ለሁለት ዶላር ሸጥኩት…”እናት || “ለልጆቼ ስል ጽጉሬን ለሁለት ዶላር ሸጥኩት…”እናት

የሶስት ልጆች እናት የሆነችው ህንዳዊቷ ፐሪማ ሰልቫም ከባለቤቷ ጋር በመሆን የቤተሰባቸውን ጉረሮ ለመድፈን በሸክላ ጡብ ስራ ላይ ተሰማርተው ቢታገሉም ባለቤቷ የራሱን ስራ ለመጀመር ወጥኖ የተበደረው ገንዘብን ለመክፈል ስለተሳነው እና ተስፋው ስለጨለመበት እንደ ምርጫ የወሰደው ነገር ቢኖር ባለፈው አመት የራሱን ህይወት ማጥፋት ነበር።

ከባለቤቷ ሞት በሁዋላ የኑሮ ጫና በሙሉ በትከሻዋ ላይ የወደቀው ፣በቀን ሁለት ዶላር ከሰማኒያ ሳንቲም(ስልሳ የኢትዮጵያ ብር አካባቢ )ተከፋይ የነበረችው ፐሪማ ሌላው ቀርቶ ልጆቿን እንኳን መመገብ ባልቻለችበት ወቅት በደረሰባት ህመም ለሶስት ወራት ከቤት በመዋሏ ያቺ ከእጅ ወደ አፍ ያልደረሰች ኑሮዋ መታወኩን ሰሞኑን ለቢቢሲ ተናግራለች።

አንድ ቀን ወደ ት/ቤት ሄዶ የነበረው የሰባት አመት ልጇ ወደ ቤተ ሲመለስ ምግብ እንደትሰጠ ወላጅ እናቱ ፐሪማን ቢጠይቅ “ምንም ምግብ የለም” የሚል ምላሽ ሲሰጠው አምርሮ ማልቀሰን የምታወሳው ወላጁ በጊዜው ከጥቂት የፕላስቲክ ቅርጫት ውጪ እንደ ወርቅ የመሳሰለ ዋጋ ያለው ጌጣጌጥ እና እቃ በቤቷ ውስጥ ታጣለች። በዚህ ብርቱ የመከራ ወቅት ከአይምሮዋ ውስጥ ዘልቆ የገባው ብቸኛ ሀሳብ ቢኖር በአቅራቢዋ ከሚገኘው የሴቶች እህቶች ጸጉርን አየላጨ ለተለያዩ ሴቶች በኤክስቴንሽንነት መልክ ለሚሸጠው መደብር ዞማ ጸጉሯን በሙሉ ለሁለት ዶላር መሸጥ እና ልጆቿም ሩዝ መመገብ ነበር።

ፐሪማ የኑሮ ውጣውረዱ ሲከፋባት እርሷም እንደ ባለቤቷ ህይወቷን ለማጥፋት በመሞከር ላይ ሳለች በአቅራቢያዋ የምትኖረው እህቷ በድንገት ደርሳ ታስጥላታለኝ።በዚህ መካከል እንደ እርሷ በታለያዩ ውጣ ውረድ ውስጥ አልፎ ህይወቱ ከተቀየረው ብላ ሙርጋህን የተባለ የኮምፒውተር ባለሙያ ጋር ተዋወቁ ። ሶስት ልጆቿን ለማሳደግ ስትል በደረሰባት ችግር፣እንደ እናትነት የተጓዘቻቸውን መከራዎቿን የተረዳው የኮምፒውተር ባለሙያው ሙርጋህን ለጊዜው የተወሰነ ገንዘብ በመስጠት አሳዛኙ ታሪኳን በወዳጆች መገናኛ መረብ (ፌስ ቡክ)ላይ ከለጠፈው ከአንድ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አንድ ሺህ ስድስት መቶ ሰባ ዶላር(መቶ ሀያ ሺህ የህንድ ሩፒ) ማግኘቱን አበስራት።

ባልጠበቀችው አጋጣሚ በእጅጉ የተደሰተችው እና ለተደረገላት ሰብአዊ እገዛም ያመሰገነችው ፐሪማ ለእራሷ እና ለልጆች የእለት ጉርስ መግዣ፣ ከፊል እዳዋምን ማቃለያ ገንዘብ ካገኘች በሁዋላ የተቀረው እዳዋን ቀስ በቀስ ( በእየወሩ አስር ዶላር) ለመክፈል እንደምትሞክር በመወሰን ፣ የፌስ ቡክ እርዳታው እንዲቋረጥ በመጠየቅ “ከዚህ በሁዋላ ኑሮ የቱንም ያህል ቢከብድብኝ እንደ ባለቤቴ ተስፋ በመቁረጥ ህይወቴን ለማጥፋት መሞከር ትልቅ ስህተት መሆኑን ተምሬያለሁ፣የቀረብኝ እዳንም ለመክፍል ድፍረት አግኝቻለሁ” በማለት ብሩህ ተስፋ መሰነቋን እና ሰው ለሰው መደሐኒትነቱን መግለጿን ቢቢሲ በአስተማሪነት ዘገባው አቅርቦታል።

እዚህ ላይ ህንዳዊቷ ፐሪማን የመሳሰሉ ስለልጆቻቸው ሲሉ መካራዎችን የሚጋፈጡ ፣ አሳዛኝ እና አስተማሪ ገድል ያላቸው ፣ነገር ግን ብዙ ያልተወራላቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን እናቶች መኖራቸውን አሌ አይባልም ።
(ታምሩ ገዳ)

LEAVE A REPLY