ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ በቦሌ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ፪፬ ቀበሌ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በኃይማኖት ቦታ መነሻነት በተፈጠረረው ችግር፣ ህይወታቸውን ያጡ ወጣቶችን ቤት ለመጎብኘት ወደ ሥፍራው ዛሬ ከሰዓት በኋላ ሲያቀኑ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል፡፡
ም/ከንቲባው ወደ ሥፍራው በመሄድ ድንኳን ጥለው ለቅሶ የተቀመጡት የሟች ቤተሰቦችን ለማጽናናት ወደ አካባቢው ሲደርሱ በእሳቸው ቀጥተኛ ትዕዛዝ የሚመራው አፍራሽ ግብረ ኃይል በቤተክርስቲያንና በምእመናን ላይ በወሰደው ፀያፍ እርምጃ የተበሳጩ የአካባቢው ነዋሪና በስፍራው የነበሩ ወጣቶች አስፋልቱን በድንጋይ ከመዝጋቱ ባሻገር የአካባቢው ነዋሪ ቁጣውን መግለፁን በቦታው የተገኘው የኢትዮጵያ ነገ የአዲስ አበባ ዘጋቢ መታዘብ ችሏል፥፥
በነዋሪዎቹ ዘንድ የነበረው ከፍተኛ ተቃውሞ ያስደነገጣቸው ታከለ ኡማ በከፍተኛ የፀጥታ ኃይል ታጅበው የነበረ ቢሆንም ሀዘኑ የተከሰተበት ሥፍራ ሳይቆዩ ለመመለስ መገደዳቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በተጓዳኝ የባላደራ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ሊቀመንበት እስክንድር ነጋ ከሌሎች አባላቶች ጋር በመሆን ህይወታቸውን ያጡ ሰማእታትን ቤተሰቦች ለቅሶ በመድረስ አጽናንተዋል