ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአውሮፕላን ቁሳቁስ ጥገናን በጋራ መሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ከሳርድ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ጋራ ተፈራረመ፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም የአየር መንገዱ የጥገና ሥራዎችን በአቪየሽን ኩባኒያጋራ በትብብር ለመሥራት መስማማቱን ገልፀዋል፡፡
ለቀጣዮቹ ፩፭ ዓመታት የሚቆየው ይህ ስምምነት እየተካሄደ ያለው የአፍሪ አቪየሽን ኮንፈረስ ውጤት መሆኑን የገለፁት አቶ ተወልደገ ብረማርያም የጣምራ ጥገና ትብብሩ የአየር መንገዱን ቴክኖሎጂና ልምድ ለማሳደግና ለማሻሻል እንደሚያግዝም ጠቁመዋል፡፡
የሳርድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ መንኩር ጃንሀዲ በበኩላቸው ኩባኒያቸው በአፍሪካ የመጀመሪያው በሆነው ትብብር ስምምነት መደሰታቸውን በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ተናግረዋል፡፡