ኦ.ኤም.ኤን ቴሌቪዥን እንዲከሰስ ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ አስሩ መንፈሳዊ ማኅበራት ጠየቁ

ኦ.ኤም.ኤን ቴሌቪዥን እንዲከሰስ ማኅበረ ቅዱሳንን ጨምሮ አስሩ መንፈሳዊ ማኅበራት ጠየቁ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በጃዋር መሐመድ የተቋቋመው ኤም ኤን ቴሌቪዥን ጣቢያ በሕግ እንዲጠየቅ ማኅበረ ቅዱሳንን ያካተተው ጴጥሮሳውያን የካህናት እና ምዕመናን ኀብረትጠየቀ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ጴጥሮሳውያን የካህናት እና የምዕመናን ኅብረት .ኤም.ኤን የተባለው ቴሌቪዥን ጣቢያ በክርስቲያኖች ላይ ጥቃት እንዲፈፀም የሚያደርግ ዝግጅት በማሰራጨቱ በሕግ እንዲጠየቅ ለኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን ጥያቄ አቅርቧል፡፡

በባለስልጣን /ቤቱ ፍቃድ የተሰጣቸው ጣቢያዎች የሚያስተላልፏቸው መርሃ ግብሮች የአገራችንን ሕግ እንዲያከብሩ እና ሕብረተሰብን የሚጎዳ ዝግጅት እንዳያስተላልፉ የመቆጣጠር ሥልጣን እና ሓላፊነት የተሰጠው በመሆኑ ቴሌቪዥን ጣቢያውን በሕግ እንዲጠየቅለት ማኅበሩ አሳስቧል፡፡

.ኤም.ኤን ቴሌቪዥን ጣቢያ ጥር 9 ቀን 2012 . ኦፌኮየተባለው ፖለቲካዊ ፓርቲ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ሰሜን ሸዋዞን ፍቼ እና ገብረ ጉራቻ (ኩዩ) ከተሞች የምርቻ ቅስቀሳ ሲያደርግ ኃይለሚካኤል ታደሰ የተባሉ ግለሰብ ያደረጉት ንግግር ከሕገ መንግሥቱ እና ከአገራችን የምርጫ ሕግ ተፃፃሪ መሆኑን የገለፀው ጴጥሮሳውን ኅብረት ቤተ ክርስቲያንን እና ምዕመናንን ለተጨማሪ ጥቃት የሚደረግ፣ ምዕመናን የሚከፋፍል እና በሐሰት የሚወነጅል መሆኑ እየታወቀ በቴሌቪዥን ጣቢያው ከተላለፈ ጀምሮ ምዕመናን ለችግር ዳርጓቸዋል ሲል ከሷል፡፡

በባለስልጣ አዋጅ ቁጥር 533/199 አንቀጽ 7(5) “ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ሕገ ወጥ ስርጭቶችን በሚመለከት ቁጥጥር እንደሚያደርግእንደሚደነግግ እንዲሁም በአዋጅ አንቀጽ 30/4/ ለስርጭት የሚቀርብ ፕሮግራም የሌሎችን እምነት የማይወነጅል፣ ብሔረሰብን ከብሔረሰብ የሚያጋጭ ወይም በሕዝቦች መካከል የእርስ በርስ ግጭት የማያነሳሳ ወይም ጦርነት የሚቀሳቀስ መሆን የለበትምየሚለውን ፍፁም የተፃረረ ንግግር በጣቢያው ስለተሰራጨ በሕግ እንዲጠየቅ ጭምር አሳስቧል፡፡

LEAVE A REPLY