በፀጥታ ሃይል ጥይት የቆሰለው ሦስተኛው ሰማእትና የ17 ዓመቱ ወጣት ሕይወቱ ማለፉ ተረጋገጠ

በፀጥታ ሃይል ጥይት የቆሰለው ሦስተኛው ሰማእትና የ17 ዓመቱ ወጣት ሕይወቱ ማለፉ ተረጋገጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ በ24 ቀበሌ የሚገኝ የማምለኪያ ሥፍራን ለማፍረስ በመጡ የጸጥታ ኃይሎች በጥይት ተመትቶ የነበረው ሦስተኛው ሰማእት ዛሬ ከሰዓት በኋላ ሕይወቱ ማለፉ ተረጋገጠ::

የ17 ዓመት ወጣት የሆነው ወጣት አብርሃም አበራ ከትናንት በስቲያ ሌሊት የጸጥታ ኃይሎች ከአፍራሽ ግብረ ኃይል ጋር የቤተ ክርስቲያኑን ቅፅር ለማፍረስ መምጣታቸውን በመስማቱ እርሱም ቤተ እምነቱን ከጥፋት ለመታደግ ነበር ከእንቅልፉ የተነሳው:: ሆኖም ሃሳቡን እውን ሳያደርግ በር ከፍቶ እንደወጣ ቤቱ ደጃፍ ላይ ብልቱ አካባቢ በጥይት ተመትቶ ሊወድቅ ችሏል። 

በግሬግሩ መሀል ቤተሰቦቹና የአካባቢው ነዋሪዎች አፋፍሰው ወደ ምንሊክ ሆስፒታል የነበረ ቢሆንም በጥይት ከተመታበት ሰዐት ጀምሮ ራሱን ስቶ የቆየው ወጣት የአብሮ አደግ ሰማአቶቹ አስከሬን ወደ ማረፊያው እየተሸኘ ባለበት ቅጽበት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል::

የአብርሃም አበራ ቤተሰቦች ሕይወቱ ከማለፉ በፊት ትናንት ከሰዓት በኋላ ወደ ቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ በልጃቸው ላይ ለደረሰው አደጋ ክስ ለመመስረት ጠይቀው ነበር:: ሆኖም የጣቢያው አዛዥ ፖሊስ ማንንም ሰው በጥይት አልመታም ፣ ክስ መመስረት አትችሉም የሚል ምላሽ ስለሰጧቸው በግራ መጋባት ስሜት ውስጥ ባሉበት ሁኔታ ልጃቸውን በሞት መነጠቃቸውን ለኢትዮጵያ ነገ ገልጸዋል። 

            

LEAVE A REPLY