ኢትዮጵያና ጅቡቲ የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት አባል ሆኑ

ኢትዮጵያና ጅቡቲ የአፍሪካ ሕብረት የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤት አባል ሆኑ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የአፍሪካ ሕብረት የሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት አባላት ሆነው ተመረጡ። ሁለቱ አገራት ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት የምክር ቤቱ አባል ሆነው እንደሚያገለግሉ ተነግሯል።

የሰላምና ፀጥታ ምክር ቤቱ የአፍሪካ ህብረት ግጭት መከላከል፣ መቆጣጠር እና አፈታት ላይ ውሳኔ ሰጭ አካል ነው። በተጨማሪም በአፍሪካ ለሚከሰቱ ግጭቶች እና ቀውሶች ወቅታዊ እና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል የደህንነት እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ተቋም ነው።

ይህም በአፍሪካ ሰላምና ፀጥታን ለማስከበር ለሚሠራው ተቋም ምሰሶ ያደርገዋል ነው የተባለው። ምክር ቤቱ እኩል ድምፅ ያላቸው 15 አባላት ያሉት ሲሆን፥ አምስት አባላት ለሦስት ዓመት እንዲሁም 10 አባላት ደግሞ ለሁለት ዓመታት ያስመርጣል። ጠቅላላ አባላት በአፍሪካ ህብረት ሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ሲመረጡ፤ በአፍሪካ ህብረት መደበኛ ስብሰባ አባልነታቸው የሚፀድቅበት አሠራር ነው ያለው።

LEAVE A REPLY