ገደዩ የኮረና ቫይረስ መከሰቱን ለአለም ያስታወቀው ዶ/ር ሊ በዚዚሁ በሽታ ተይዞ...

ገደዩ የኮረና ቫይረስ መከሰቱን ለአለም ያስታወቀው ዶ/ር ሊ በዚዚሁ በሽታ ተይዞ ሞተ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || በውሃን ቻይና የተከሰተውን ኖቭል ኮረና የሚባለውን የዘመኑን ተዛማች ቫይረስ ለአለም ማህበረሰብ ያጋለጠው ሐኪም በዚሁ በሽታ ተይዞ መሞቱ የመገናኛ ብዙሃንን ትኩረት ስቧል።

ዶክተር ሊ ዊንሊያንግ የቫይረሱን አደገኛነት እና ፈጥኖ ተላላፊነት ቢያሳውቅም የቻይና ባለስልጣናት የሃገር ገጽታን የጠለሻል በማለት አፍነውታል።

ችግሩን ለአለም ማህበረሰብ ያስተዋወቀው ዶ/ር ሊ ዊንሊያንግ ግን በሚሰራበት የውሃን ከተማ ሆስፒታል ውስጥ ህሙማን በተቻለ መጠን ጥንቃቄ እንዲያደርጉና ሌሎች ሰዎችም ስለበሽታው እንዲያውቁ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል።

በዚህም ሳብያ የቻይና መንግስት መኖሪያ ቤቱ ድረስ በመሄድ ድርጊቱን እንዲያቆሙ ከፍተኛ ጫና ሲያደረግበት እንደነበር ተዘግቧል።
ቻይናዊው ዶክተር ሊ በርካቶችን ሲያስጠነቅቅ እና ስለበሽታው አደገኛነት በድፍረት ቆይታ በኮረና ቫይረስ ተያዘ ነው በ34 ዓመቱ ህይወቱን ያጣው።

LEAVE A REPLY