ጠ/ሚ/ትር ጀስቲን ትሩዶ የካናዳ ባለሃብቶች ጋር ነው አዲስ አበባ የገቡት

ጠ/ሚ/ትር ጀስቲን ትሩዶ የካናዳ ባለሃብቶች ጋር ነው አዲስ አበባ የገቡት

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ለይፋዊ ራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጀስቲን ትሩዶ በቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል። በአገራቱ መካከል ሊኖር በሚችለው የኢንቨስትመንት እና ሌሎች የኢኮኖሚ ትብብሮች ዙሪያ ውይይት ይደረጋል ነው የተባለው።

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋርም የካናዳ ባለሀብቶችም አብረው አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን በነገው እለት በሚካሄደው የቢዝነስ ፎረም ይካፈላሉ ተብሎም ነው የሚጠበቀው። የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ከፈረንጆቹ የካቲት 6 ጀምረው እስከ የካቲት 14 ቀን 2020 በሚቆየው ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ወደ ሴኔጋል ያቀናሉ።

በጉብኝታቸው በየአገራቱ በሚኖራቸው ቆይታ የኢኮኖሚ እድልና ብልፅግና፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ዴሞክራሲ እና የሴቶች እኩልነት ጉዳዮችን አብይ አጀንዳቸው ያደርጋሉ ተብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ አበባ በሚካሄደው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ጉባኤ ላይ በመሳተፍ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር እንደሚወያዩ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ገልጿል።

LEAVE A REPLY